ፈልግ

BULGARIA BELIEF HONEY DAY BULGARIA BELIEF HONEY DAY 

በቡልጋሪያ የሐይማኖት መሪዎች በተሻሻለው የሃገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገለጹ።

የቡልጋሪያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ብጹዕ አቡነ ክርስቶ ፕሮይኮቭ በበኩላቸው፣ ፓርላማው ያደረገው ማሻሻያ የኮሚኒስት ስርዓትን የሚከተል ፣ በሐይማኖቶች መከከል መበላለጥን የሚያመጣ፣ የእምነት ነጻነቶችን የሚጻረር፣ ቡልጋሪያ በአባልነት የፈረመችውን የዓለም አቀፉን ደንብ የሚቃረን መሆኑን አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቡልጋሪያ ፓርላማ፣ የእምነት ደንቦችን በሚመለከት ሕግ መንግሥት ላይ ማሻሻያ መደረጉን በሙሉ ድምጽ መስማማቱን ቢገልጽም፣ መንግሥት በሐይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባቱን ያመለክታል በማለት የአገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ የኦርቶዶክስ ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና የእስልምና እምነት አባቶች ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የእምነቶቹ አባቶች በጥቅምት ወር 2011 ዓ. ም. በአገሪቱ ፓርላማ በሙሉ ድምጽ የጸደቀ የማሻሻያ ሕገ መንግሥት እንዳለ አስታውሰው፣ ለአገሪቱ ፓርላማ ያቀረቡትም የእምነቱ አባቶች እንደሆኑ በቡልጋሪያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተወካይ ክቡር አባ ፔትኮ ቫሎቭ ሲር ለተባለ የቤተክርስቲያን የዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

ካቶሊኮችን ምን አሳሰባቸው?

ክቡር አባ ፔትኮ ቫሎቭ በአገሪቱ ሕገመንግሥት እንዲሻሻል የተደረገው ሕግ በሌሎች የእምነት ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለውና የእምነትን ነጻነት የሚገድብ መሆኑን አስረድተዋል። አባ ፔትኮ በማከልም የአገሪቱን ጸጥታ ለማስከበር የቆሙ ሌሎች ሕጎችና መንገዶች መኖራቸውን አስረድተው፣ የዜጎች የእምነት ነጻነትን የሚገድብ ወይም የሚጻረርን ሕግ መኖር የለበትም ብለዋል። የቡልጋሪያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ብጹዕ አቡነ ክርስቶ ፕሮይኮቭ በበኩላቸው፣ ፓርላማው ያደረገው ማሻሻያ የኮሚኒስት ስርዓትን የሚከተል ፣ በሐይማኖቶች መከከል መበላለጥን  የሚያመጣ፣  የእምነት ነጻነቶችን የሚጻረር፣ ቡልጋሪያ በአባልነት የፈረመችውን የዓለም አቀፉን ደንብ የሚቃረን መሆኑን አስረድተዋል። ተሻሽሎ የቀረበው ሕግ የውጭ አገር ካህናት ወደ ቡልጋሪያ መጥተው ሐዋርያዊ ተልዕኮን እንዳያበረክቱ የሚያግድ፣ ከውጭ አገር የሚላክ የማንኛውም ሐይማኖት የቁሳቁስና የሰው ሃይል እገዛ ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚጠይቅ እንደሆነ ገልጸው፣ ይህን መጠነ ሰፊ የሆነ የሥራ ዘርፍ እንዲከታተል የተሰየመው የመንግሥት ክፍል ብቃት እንደሚያንሰው ክቡር አባ ፔትኮ አስረድተዋል።

ለኦርቶዶክስና ለሙስሊሞች የተሰጠው ድጎማ፣

የቡልጋሪያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ብጹዕ አቡነ ፕሮይኮቭ በንግግራቸው እንደገለጹት መንግሥታቸው ሌሎች ሐይማኖቶችን ለይቶ፣ ለኦርቶዶክስና ለእስልምና እምነቶች የተሻለ ድጎማ ለማድረግ መወሰኑ በሐይማኖቶች መካከል ልዩነትን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው፣ ቤተክርስቲያናቸው ከመንግሥት የሚያገኘው ድጎማ ለቤተክርስቲያን እድሳት ብቻ እንጂ ለሌላ የአገልግሎት ዘርፍ እንደማይበቃ ገልጸዋል።

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አቋም፣

የቡልጋሪያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንግሥት በሐይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ የሚከለክል ሕግ እንዳለ የገለጹት አባ ቫሎቭ ነገር ግን የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሐይማኖቶችን ጨምሮ ሌሎች ሐይማኖቶች በምዕመናኖቻቸውና በእናት ቤተክርስቲያኖች እንደሚደጎሙ ገልጸው ይህም በቡልጋሪያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ዘንድ መልካም ተቀባይነትን እንዳላገኘ አስረድተው ምዕመናን ቤተክርስቲያናቸውን መርዳትና መደገፍ ክርስቲያናዊ ግዴታ እንጂ ከመንግሥት የተሰጠ ግዴታ አለመሆኑን አባ ቫሎቭ አስረድተዋል።

የእስላማዊ አክራሪነትን የሚቃረን ሕግ፣

የእምነት ተቋማትን አስመልክቶ ተሻሽሎ የቀረበውን ሕግ መንግሥት በማርቀቅ ሥራ ላይ የተሳተፉት እንዳስረዱት፣ ሕጉ ተሻሽሎ እንዲቀርብ የተደረገበት ዋናው ምክንያት እስላማዊ አክራሪነትና አሸባሪነት ከውጭ አገሮች እየገቡ መሆናቸው ስለተረጋገጠ ነው ቢባልም በቡልጋሪያ የእስልምና ሐይማኖት ታላቁ ምክትል ሙፍቲ ቢራሊ ቢራሊ እንዳስረዱት በቡልጋሪያ በሐይማኖቶች በኩል የተሰነዘረ የሽብር ወንጀል እንዳልተፈጸመ ገልጸው በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ምንም ዓይነት ክስ እንዳልቀረበ አስረድተዋል።  በቡልጋሪያ የሐይማኖት ጉዳዮችን በቅርብ የሚከታተሉ አቶ ሚሃኤል ኢቫኖቭ እንዳስረዱት አክራሪነትን በጥብቅ የሚቃወሙት የእስልምና እምነት ተከታዮች መሆናቸውን አስረድተው ለአገሪቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሰላምንና ጸጥታን ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል ብለዋል። ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ሕዝብን ማስተማርና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ማደራጀት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። የአገሪቱ ከፍተኛ የእስልምና ሐይማኖት መሪ ሙፍቲ ሙስጠፋ ሃድዚ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦይኮ ቦሪሶቭ ባቀረቡት ማሳሰቢያቸው በቡልጋሪያ በሚገኙ ከፍተኛ የእስልምና እምነት የትምህርት ተቋማት ውስጥ  የመምሕራን እጥረት በመኖሩ መምሕራንን ከውጭ አገር ለመጋበዝ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ከምሁራን የቀረበ ደብዳቤ፣

ተሻሽሎ የተደረገበትን ሕገ መንግሥት አስመልክቶ የቡልጋሪያ ምሑራን ባቀረቡት አስተያየት በሕገ መንግሥቱ የተደረጉት ማሻሻያዎች የዜጎችን መብት የሚገድብ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትንም የሚቃረን እንደሆነ፣ የሃይማኖት ነጻነትንም የሚከለክል እንደሆነ አስረድተዋል። ምሑራኑ በማከልም በሕገመንግሥቱ ማሻሻያ ወቅት የእምነት አባቶች የተሳተፉበት ሕገመንግሥት ወደ ፓርላማው ቀርቦ ድምጽ እንዲሰጥበት ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
06 November 2018, 17:22