ቤተክርስቲያን እና ሴቶች መካከል ያለው ጥያቄ ሁሉም ክፍት የሆነ ወሳኝ ጥያቄ ነው!
እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ1968 ዓ.ም. የሴቶች መብት ተሟጋቾች ለሚያቀርቡዋቸው ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎች መልስ በጥብቅ ይጠባበቁበት የነበረ ጊዜ እንደ ሆነ ይታወሳል። ይህ ጥይቄ ከተነሳበት ከ50 ዓመታት በኋላ ይህንን ጥያቄ በድጋሚ በማንሳት ይህ ጥያቄ ያስገኘውን መልካም ነገር እና የገጠመውን ተግዳሮት ግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ ጉዳይ ላይ ማሰላሰል ተገቢ የሆነ ሓሳብ ነው። ሴቶች በተለይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ሚና በተመለከተ በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ባለው 15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በተለየ ሁኔታ ለእምነት፣ ለወጣቶች እና ለሴቶች ትኩረት በመስጠት በመካሄድ ላይ እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን በተመለከተ በነገረ መለኮት ትምህርት ሊቅ የሆኑት ማሪኔላ ፔሮኒ በተለይ ከቫቲካን ዜና ጋር በነበራቸው ቆያታ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊኖራቸው ሰለሚገባ ሚና በስፋት ማብራርያ ሰጥተዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ
በምዕራቡ ዓለም ቢያንስ በ 1968 ዓ.ም። የዛሬ 50 ዓመት ገደማ ማለት ነው በተለይም ደግሞ በምዕራቡ ዓለም ውስጥ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ታሪካዊ ጊዜን ያስታውሰናል። ይህም በሁሉም በሲቪል፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ ዕለት ተዕለት በነበረው የአኗኗር ዘይቤ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ወይም ክስተት የታየበት ወቅት ነው። በአጠቃላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ የታየበት ወቅት እንደ ሆነ የሚታወስ ሲሆን ወጣቶች ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ መሆን ያለበት መብት እንደ ሆነ የሞገቱበት፣ ሴቶች ከወንዶች በእኩል መብት እንዲኖራቸው የጠየቁበት ወቅት በመሆኑ የተነሳ ይህ ጉዳይ በቤተሰብ ውስጥ ለረጅም ጊዜያት ይህል የጠብ መንስሄ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። ይህ በወቅቱ የተደርገው የወጣቶች እና የሴቶች ንቅናቄ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን እና እንዲሁም ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን ያነቃነቀ ጉዳይ ነበር። በዚህም የተነሳ ብዙ ቀሳውስት አጣብቂኝ ውስጥ የገቡበት፣ ሃይማኖታዊ ተግባራት እና የእምነትን በተወሰነ ደረጃ ተቀባይነት ያጡበት ወቅት ነበር።
ሴቶች እና ቤተ ክርስቲያን እ.አ.አ. 1968 ዓ.ም
ዛሬ በርካታ ዓመታት ካለፉ በኋላ ዛሬውኑ በተጨባጭ እና በተጨባጭ ግንዛቤ ላይ ተመርኩዘን ይህንን ጉዳይ ማየትና የተከሰተውን አሉታዊ እና አዎንታዊ የሆኑ ሁኔታዎችን በመገምገም፣ የተከሰቱ ግጭቶችን
በዘመናት ውስጥ የተነሱ የሴቶች ጥያቄ