ፈልግ

2018.09.29 Angelo 2018.09.29 Angelo 

ጠባቂ መላእክት የሕይወታችን ጉዞ ረዳቶች ናቸው።

መላእክት በአፈጣጠራቸው ንጹሕ በመሆናቸው የእግዚአብሔርን አምሳያነት ተላብሰዋል፣ ንጽሕናቸውም ሥጋ ለባሽ ስለሆኑ ሳይሆን ከሰው ልጅ በላይ ጥብበን፣ ነጻነትንና በጎ ፈቃድን ስለተቸሩ ከሌሎች ፍጥረታት የተለዩ ናቸው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአውሮጳውያኑን ዘመን አቆጣጠር በሚከተሉ ካቶሊካውሊካውያን ዘንድ ዛሬ የጠባቂ መልአክት በዓል የሚከበርበት ዕለት ነው። ይህ በዓል በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር መሠረት ጥቅምት 2 ቀን እንዲከበር ተብሎ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቀለሜንጦስ 10ኛ እ. አ. አ. በጥቅምት 2 ቀን 1670 ዓ. ም. ተውስኗል። በዚህ መሠረት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ጠባቂ መላእክት ከክፉ ነገር እንደሚከላከሉን አስረድተዋል።

እ. አ. አ. ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ. ም. የጠባቂ መልአክት በዓል የሚከበርበት ዕለት እንደሆነ የላቲን የአምልኮ ስርዓት የቀን አቆጣጠር ያስገነዝባል። በሮም የቅዱስ ልብ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ፣ የነገረ መለኮት መምህር የሆኑት አባ ሳልቫቶሬ ቪቴሎ ስለ ጠባቂ መልአክት ማንነት ሲያስረዱ፣ እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ፍጥረታት በሙሉ ጥበቃና ከለላ እንዲደረግላቸው በማለት ጠባቂ መላእክትን አስቀመጣቸው ብለዋል።

ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን፣ የቤተክርስቲያን አባቶችና ቅዱሳን በሙሉ ስለ ጠባቂ መልአክት አገልግሎት በጥልቀት ተናግረዋል ያሉት አባ ሳልቫቶሬ ሁለት ነገሮችን ለይተን መመልከት ይኖርብናል ብለዋል። ስለ ጠባቂ መላዕክት ስንናገር በሐዋርያት ጸሎት እንደተጠቀሰውና እኛም ክርስቲያኖች ይህን ጸሎት ስናቀርብ እግዚአብሔር የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ እንደፈጠረ እናምናለን። መላዕክት በማይታዩት የእግዚአብሔር ፍጥረታት ውስጥ ይጠቃለላሉ። ይህም በኒቂያውና ቁንስጥንጥኒያው የቤተክርስቲያን ጉባኤ የተወሰነ፣ በሐዋርያት ጸሎተ ሐይማኖት የተጠቀሰና በምዕመናን የሚደገም፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ ጳውሎስ ስድስተኛም እ. አ. አ. በሰኔ 30 ቀን 1968 ዓ. ም. ያስታወሱት እንደሆነ አባ ሳልቫቶሬ አስረድተዋል።

አባ ሳልቫቶሬ በማከልም እኛ የሚታየውን፣ ለምሳሌም የምንኖርበት ግዙፍ ዓለምን በፈጠረ፣ እንደዚሁም የማይታየውን ለምሳሌም ንጹሐን መናፍስትን፣ ከእነዚህም መካከል መላእክትን በፈጠረ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን ብለዋል። ንግግራቸውን በመቀጠል እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ፍጥረታት በሙሉ ጥበቃና ከለላ እንዲኖራቸው በማለት ጠባቂ መላእክትን ወደ ፍጥረቱ እንደላካቸው ቤተክርስቲያን በማመን ከመላዕክት መካከል ጠባቂ መልአክት እንዳሉ ታስተምረናለች ብለዋል። ርዕሠ  ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስም ወደ ጠባቂ መልአክት ዘንድ ባቀረቡት ጸሎታቸው የእግዚአብሔር መልዕክተኛና የእኛ ጠባቂ ከሆነው መልአክ ድጋፍንና ከለላን ማግኘት እንድንችል እግዚአብሔር በጸጋው ይርዳን በማለት ጸሎታቸውን አቅርበዋል።

እግዚአብሔር መልአክትን በመፍጠሩ ፍጥረታቱ ሙሉ አድርጎታል። መላእክት በአፈጣጠራቸው ንጹሕ በመሆናቸው የእግዚአብሔርን አምሳያነት ተላብሰዋል ያሉት አባ ሳልቫቶሬ ንጽሕናቸውም ሥጋ ለባሽ ስለሆኑ ሳይሆን ከሰው ልጅ በላይ ጥብበን፣ ነጻነትንና በጎ ፈቃድን ስለተቸሩ ከሌሎች ፍጥረታት የተለዩ ናቸው ብለዋል።

እኔን የሚመክረኝ መንፈስ ቅዱስ አለ፣ የሚመክረኝ መልአክ አለ። ይህን በምልበት ጊዜ ስለ መላእክት የሚሰጥ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አይደለም። በቅዱስ ቃሉ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እግዚአብሔር ራሱ ያለው ነው። “ከስሕተት ይጠብቅህ ዘንድ፣ በጉዞህም ከለላና መሪ ይሆንህ ዘንድ መልአክን እልክብሃለሁ” ማለቱን ርዕሠ ሊቃነ ፍራንችስኮስ አስታውሰዋል።                           

02 October 2018, 17:36