ፈልግ

SYNOD-2018 SYNOD-2018 

15ኛው ሲኖዶስ፡ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቁልፍ የሆነ ሚና አላቸው።

ከባለፈው መስከረም 23/2011 ዓ.ም እስከ ሚቀጥለው እሁድ ጥቅምት 18/2011 ዓ.ም “ወጣቶች፣ እምነት እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል 15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በዕየለቱ ከሚደረገው ሲኖዶስ በመቀጠል የዕለቱን ውሎ የተመለከተ መግለጫዎች በተለያዩ የሲኖዶሱ ተካፋዮች አማካይነት መገለጫ እንደ ሚሰጥ ይታወቃል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዚህ መሰረት በጥቅምት 14/2011 ዓ.ም የዕለቱን ውሎ በተመለከተ መገለጫ የሰጡት የሞናኮ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ሪቻርድ ማርክስ መሆናቸውን በተለይ ለቫቲካን ዜን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በጣም ቁልፍ የሆነ ሚና” እንዳልቸው መገለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በካቶሊክ በቤ ተክርስቲን ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ፣ ስነ-ጾታን እና በአሁኑ ወቅት የተሻለ ዓለም ለመገንባት በሚደርገው ጥረት ውስጥ ወጣቶች ሊያበረክቱት የሚችለውን አዎንታዊ አስተዋጾን በተመለከተ የተናገሩት ካርዲናል ሪቻርድ ማርክስ እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ባለው ሲኖዶስ ላይ ትኩረት ተስጥቶዋቸው ውይይት እየተደረገባቸው የሚገኙ ሐሳቦች እንደ ሆኑም ጨምረው ገለጸዋል።

“ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ቁልፍ የሆነ ሚና አሳንሰን የምንመለከት ከሆነ ሞኝነት መሆኑን” የገለጹት ካርዲናል ሪቻርድ ማርክስ ሴቶች ከነገ ጀምሮ ሳይሆን ነገር ግን ዛሬውኑ ቤተ ክርስቲያን በአንድ አንድ ጉዳዮች ላይ በምታደርጋቸው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ሴቶችን በበቂ ሁኔታ ማሳተፍ እንደ ሚገባ ገለጸው “ሴቶችን በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በበቂ ሁኔታ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ በጣም አስፈላጊ እና ይህንንም ተጋባራዊ ለማድረግ ስር ነቀል የሆነ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

በፖላንድ የሎዴዝ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ዬኔታ ግሬዝጎርዝ ሬይስ በበኩላቸው እንደ ገለጹት ወጣቶች ክርስቶስን በሚገባ እንዲያውቁ ለማስቻል ከፍተኛ የሆነ ሥራ መሰራት እንዳለበት የገለጹ ሲሆን ይህ አሁን በመደረግ ላይ የሚገኘው 15ኛው አጠቃላይ መደበኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ለየት ባለ መልኩ ለወጣቱ ትውልድ ትኩረት በመስጠት መደርጉ ቤተ ክርስቲያን ለጉዳዩ ከፍተኛ የሆን አትኩረት እንደ ሰጠች ያሳያል ብለዋል።

26 October 2018, 16:10