ፈልግ

MALAWI-POLITICS-INDEPENDENCE-ANNIVERSARY MALAWI-POLITICS-INDEPENDENCE-ANNIVERSARY 

የማላዊ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሀገሯን ብሔራዊ ምርጫ በቅርብ ሆና እንደምትከታተለው አስታወቀች።

የሃገሪቱ ዜጎች በሙሉ ቁጣን እና አመጽን የሚቀሰቅሱ ቃላትንና ተግባራትን በማስወገድ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል። ብጹዓን ጳጳሳት ማላዊ ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጊዜ ወዲህ የሰላምን ጸጋ የተቸረች አገር እንደሆነች አስታውሰው ይህን ጸጋ ዘላቂ የሚያደርገው የማላዊ ሕዝብ ተከባብሮና ተፋቅሮ በሰላም አብሮ በመኖር ስለሆነ ይህም ከእግዚአብሔርና ከሃገር የተላከ ግዴታ እንደሆነ አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የማላዊ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እንዳስታወቀችው፣ ለየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ተወዳዳሪ ግለ ሰብ ሳትወግን፣ ነገር ግን የሃገሪቱ ካቶሊካዊ ምዕመናን በሙሉ፣ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ. ም. በሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ በንቃት እንዲሳተፉ እነደምታደርግ ገልጻለች።

የማላዊ ብጹዓን ጳጳሳት በካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን ካህናት፣ ገዳማዊያንና ገዳማዊያት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ማሕበራዊ እና መንፈሳዊ ተቋማት ውስጥ በሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች በሙሉ ከማንኛውም ዓይነት የወገንተኝነት ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስበው ቤተ ክርስቲያኒቱ በወገናዊነት መፈረጅ የለባትም ብለዋል።  በማከልም የሃገሪቱ ዜጎች በሙሉ ቁጣን እና አመጽን የሚቀሰቅሱ ቃላትንና ተግባራትን በማስወገድ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል። ብጹዓን ጳጳሳት ማላዊ ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጊዜ ወዲህ የሰላምን ጸጋ የተቸረች አገር እንደሆነች አስታውሰው ይህን ጸጋ ዘላቂ የሚያደርገው  የማላዊ ሕዝብ ተከባብሮና ተፋቅሮ በሰላም አብሮ በመኖር ስለሆነ ይህም ከእግዚአብሔርና ከሃገር የተላከ ግዴታ እንደሆነ አስረድተዋል። በተለይም ይህ ሰላም ሃገሪቱ በምታካሂደው ብሔራዊ ምርጫ ወቅት የተጠበቀ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ጳጳሳቱ በማከልም በሃገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ላይ መሳተፍ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም እንደሆነ አበክረው አሳስበዋል። ይህን በመገንዘብ የምርጫ አስተባባሪ አካላትም ትክክለኛና ፍትሐዊ የሆነ ምርጫ መካሄዱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ማላዊ ከብሪታኒያ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ከ1956 ዓ. ም. ወዲህ የመጀመሪያ የሆነውን ነጻ ምርጫን ያካሄደችው፣ በካሙዙ ባንዳ ዘመነ መንግሥት፣ በ1986 ዓ. ም. እንደሆነ ታውቋል። ማላዊ ከሌሎች አጎራባች አገሮች በተቃራኒ፣ አምባ ገነናዊ ሥርዓትን ያለፈች፣ አሁን ደግሞ በሙስና፣ በድርቅ፣ በረሃብ እና እያደገ በመጣው የኤይድስ በሽታ የምትሰቃይ ደሃ አገር መሆኗ ታውቋል።                 

18 September 2018, 17:16