ፈልግ

2018.08.11 Incontro Giovani al Circo Massimo 2018.08.11 Incontro Giovani al Circo Massimo  

የካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት 15ኛው ጠቅላላ መደበኛ ሲኖዶስ ወጣቶችን በተመለከተ እንደሚነጋገር ተገለጸ።

ኣሁን በምንገኝበት በወጣቶች ጉባዔ ዋዜማ ይህ የካቶሊክ ሥልጣኔ ወይም ቺቪልታ ካቶሊካ የሚለው ሰነድ ለዚህ ወጣቶችን በተመለከተ ለሚደረገው ጉባዔ ዓይነተኛ ኣስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታሰባል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ከኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

በጥቅምት ወር የሚካሄደው የካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት 15ኛው ጠቅላላ መደበኛ ሲኖዶስ ወጣቶችን በተመለከተ እንደሚነጋገር ተገለጸ።

ይህ 4 ክፍል ያለው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ በሚል የወጣው ሰነድ ኣንዱ ክፍል ወጣቶችን በተመለከተ እንደሆነና በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሚደረገው የጳጳሳት ጉባዔም ትልቅ ቦታ እንደሚኖረው የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ኣሌክሳንድሮ ጂሶቲን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ኣሁን በምንገኝበት በወጣቶች ጉባዔ ዋዜማ ይህ የካቶሊክ ሥልጣኔ ወይም ቺቪልታ ካቶሊካ የሚለው ሰነድ ለዚህ ወጣቶችን በተመለከተ ለሚደረገው ጉባዔ ዓይነተኛ ኣስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታሰባል። ይህ ባለ 4 ክፍል የወጣው መጽሓፍ ወጣቶችን በተመለከተ የሚደረገው ጉባዔ ኣስፈላጊ እንደሆነ ይጠቅሳል። በዚህም ዙሪያ ካህናቶች በቤተክርስቲያን ውስጣዊ ሳይሆን ወንጌልን በማሰራጨትና በማስተማር ረገድ ስለሚገጥማቸው ችግር ይዳስሳል።

ይህን በተመለከተ በኣንድ የእይሱሳዉያን ማኅበር ላይ በወጣ መጽሔት ይህ በወንጌል ሥርጭት ዙሪያ ያለ ለውጥ ባዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ይላል። ይህ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስን ኣመላክቶ ሰለ ወጣቶች የሚናገረው ክፍል ወጣትነትና ውሳኔ በሚል በሁለት ነገሮች ላይ በተለየ ሁኔታ ያጠነጥናል ። እነዚህ ነገሮች እንደ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ኣገላለጽ ሁል ጊዜ በኣንደነት ይጓዛሉ የተቀረዉንም ነገር ሁሉ ያንጻሉ ይላሉ። እነዚህን ነገሮች ወደ ሲኖዱ ከመግባት በፊት በደንብ መረዳትና ማስተንተን እንደሚያስፈልግ ተተቅሷል። መጽሔቱ በመቀጠል ይህ የጉባዔው ዝግጅት ላይ የሚቀርቡት ሓሳቦች ጠለቅ ያለና በስተመጨረሻም ኣንድ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ እንደሆነ ያሰምርበታል።

የዚህ ሰነድ የመጀመሪያ ክፍል 3 ኣርስቶችን የያዘ ሲሆን በኣጠቃላይ የሰነዱን ገጽታ በወጣቶች ላይ ሰለሚደረገው ጉባዔ ወይም ሲኖድ ያትታል። የዚህ ሰነድ ሁለተኛ ክፍል ስል መጽሓፍ ቅዱስና ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የወጣትነት ጊዜ ይናገራል። የዚህ ሰነድ ሦስተኛ ክፍል ማኅበረሰባዊ ሳይንስን ባቀፈ መልኩ ወጣቱ በእምነት ላይ ያለዉን ባሕሪና ዳግም ተነሳሽነቱን የሚዳስስ ሲሆን ይህም በኣብዛኛው በዚህ በጣሊያን ውስጥ ያሉትን ይዳስሳል። የዚህ ሰነድ ኣራተኛ ክፍል ወጣቶችን በማስተማርና በማሰልጠን ዙሪያ ሲተነትን በተለይ ደግሞ የኣስተማሪዎችን ወይም የኣሰልጣኞችን የሥራ ድርሻ የተለየ ትኩረት እንደሚሰጠው በተመለከተ ነው። የዚህ ሰነድ ኣምስተኛ ክፍል በወጣጦችና በጎልማሶች መሓል ስለሚኖር ግንኙነት ሲሆን የዚህ ሰነድ ስድስተኛ ክፍል የዚህ የዘመናችንን ወይም የወቅቱን ወጣቶች በተመለከተ ነው። የመጨረሻውና ሰባተኛው ሰነድ ወጣቶች ስሜታቸውን የሚረዱበትና የሚቀርጹብት ጉዳይን በተመለከተ ነው።

እነዚህ በመጽሓፉ የተካተቱት ሰነዶች የቀረቡትና የተፈረሙት በኣባ ኣንቶኒዮ ስፓዳሮ ሲሆን ከሳቸዉም ጋር ኣብረው ቁጥራቸው በርከት ያሉ ካህናት ኣሉ።

07 September 2018, 17:26