ፈልግ

ቅድስት ሞኒካ በዛሬ ዘመን ለሚገኙ እናቶች መልካም ምሳሌ ናት

“ውድ እናቶች ልክ እንደ ቅድስት ሞኒካ ፈጽሞ ተስፋ ሳትቆርጡ ለልጆቻችሁ ያለማቋረጥ ጸልዩ”

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በነሐሴ 21/2010 ዓ.ም የቅድስት ሞኒካ ዓመታዊ በዓል ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል። ቅድስት ሞኒካ እ.አ.አ ከ331-287 ዓ.ም በአልጄሪያ የኖረች ቅድስት ስትሆን እኝህ ቅድስት በወቅቱ አንድ ልጅ ነበራቸው፣ ይህ ወጣት ልጅ በወቅቱ መናፍቅ የነበረና ምንም ዓይነት እምነት ያልነበረው ሰው በመሆኑ የተነሳ እናቱ በጣም ታዝን ነበር።

የዚህ ዜና አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

መላክም ሚስት እና መላክም እናት

ቅድስት ሞኒካ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የኖረች፣ አማኝ የነበረች እና በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያላትን ሚና በከፍተኛ ሁኔታ የተረዳች፣ በሕይወቷ ዘመን ሁሉ ለእግዚኣብሔር ታማኝ ሆና የኖረች እናት ነበረች። ለልጆቿ የወደፊት ሕይወት የሰመረ እንዲሆን በከፍተኛ ሁኔታ የምትመኝ እናት የነበረች ሲሆን በተለይም ደግሞ ታላቅ ልጇ የሆነው አጎስጢኖስ በትምሕርቱ ይበረታ ዘንድ ከፍተኛ ጥረት ታደርግ ነበር። ነገር ግን ነገሮች ሞኒካ እንዳሰበችሁ አልሆኑም። ሞኒካ ቀስ በቀስ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ላይ መተማመን ለመደች፣ ነገር ግን ይህ በእግዚኣብሔር ላይ ያላት ከፍተኛ መተማመን የእናትነት ሚናዋን የሚተካ ሳይሆን ነገር ግን ልዑል እግዚኣብሔር በእናትነት ሚናዋ እንዲረዳት እና የእናትነት ሚናዋን በሚገባ ማከናወን ትችል ዘንድ ከጎኑዋ እንዲቆም አጥብቃ ትመኝ እና ለዚህም ትጸልይ ነበር። በተለይም ደግሞ የበኩር ልጇ አጎስጢኖስ በወቅቱ መናፍቅ በመሆኑ የተነሳ በእግዚኣብሔር ያምን ዘንድ በለቅሶ እና በጸሎት እግዚኣብሔርን ትማጸን ነበር።

የክርስትናን እምነት ይቀበል ዘንድ ጌታ እንዲረዳው ቀን ከሌሊት እያለቀሰች ወደ እግዚኣብሔር ጸሎቱዋን ታቀርብ የነበረቺው ቅድስት ሞኒካ እንባዋ እና ጸሎቱዋ በከንቱ አልቀረም፣ እግዚኣብሔር የልቧን መሻት ሰጣት ልጇም የክርስትና እምነት ተቀበል፣ የእግዚኣብሔር ቤት አገልጋይ ሆነ፣ በመጨረሻም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ ካደርጉ ታላላቅ ቅዱስ መካከል ሊመደብ የሚችል ቅዱስ ለመሆን በቃ። ይህ ቅዱስ ቅዱስ አቆስጢኖስ ይባላል።

27 August 2018, 09:49