ፈልግ

manifesto Rimini Meeting 2018 manifesto Rimini Meeting 2018 

የሰው ልጅ እውነተኛ ደስታን ለማግኘት በእግዚአብሔር ሃይል ማመን ያስፈልጋል።

“ታሪክ ቀጣይነት እንዲኖረው እና የሰው ልጅም እውነተኛ ደስታን እንዲያገኝ የሚያደርግ አንድ ሃይል ብቻ ነው።”

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሰሜን ምስራቅ ኢጣሊያ ከተማ በሆነችው በሪሚኒ በዛሬው ዕለት የተጀመረውን ዓመታዊ ስብሰባን በማስመልከት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጉባኤው ተከፋዮች መልዕክት መልካቸው ታውቋል። ቅዱስነታቸው ለስብስወባው ተሳታፊዎች በላኩት መልዕክት እንዳስታወቁት፣ ክርስቲያን የተሻለ ዓለምን ለመገንባት ያለውን ምኞት ማቋረጥ ወይም መተው የለበትም ብለው፣ የክርስትና እምነትም የሚያግዘው ይህን ለማድረግ የሚያስችል ፍላጎት በቀጣይነት ቀጣይነት እንዲኖር ለማድረግ ነው ብለዋል።

ዘንድሮ በሪሚኒ ከተማ ለሚካሄደው ጉባኤ መንደርደሪያ ርዕስ “ታሪክ ቀጣይነት እንዲኖረው እና የሰው ልጅም እውነተኛ ደስታን እንዲያገኝ የሚያደርግ አንድ ሃይል ብቻ ነው።” የሚል እንደሆነ ብጹዕ አቡነ ጁሳኒ ገልጸዋል። ብጹዕ አቡነ ጁሳኒ ለሰው ልጅ እውነተኛ ደስታን የሚሰጥ እና ታሪክም ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደረግ ሃይል የቱ እንደሆነ ከአንድ ወጣት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ወጣቱ በ1960 ዓ. ም. በሕይወቱ ለውጥን ለማምጣት ያስቻለውን መንገድ እንደጠቆመው፣ አንድ ትውልድ ባለፉት የታሪክ ዘመናት መልካም ለውጦችን ለማድረግ ያገዙትን ተቋማትን ሳይዘነጋ፣ እውነተኛ ሕይወትን ለመገንባት እየጣሩ ተስፋ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ለጉባኤው አስተባባሪዎች እና ለስብሰባው ተካፋዮች፣ በሪሚኒ ሀገረ ስብከት ጳጳሳት በሆኑት በብጹዕ አቡነ ላምቢያሲ በኩል በላኩት መልዕክታቸው እንዳስገነዘቡት፣ በርካታ ምዕመናን የተሻለ ዓለምን እውን ለማድረግ ከእምነታቸው በሚያገኙት ጸጋ እንደሚተማመኑ ገልጸዋል። ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በመልዕክታቸው፣ ዓለም ለሰው ልጅ የተሻለ የመኖሪያ ስፍራ ለማድረግ የነበረው ምኞት፣ በሰዎች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር የሚያግዝ ድልድይ ከመገንባት ይልቅ ዓለምን የሚከፋፍል ግድግዳን መገንባት ስለመረጠ የሚመኘውን የተሻለ ዓለም ማግኘት አልቻለም ብለዋል። ከሌላው ዓለም ጋር በመቀራረብ፣ መተጋገዝ የተሻለ ዓለም ለመገንባት ራስን ዝግጁ ከማድረግ ይልቅ ተለያይቶ መኖር ስለተመረጠ በሕዝቦች መካከል የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ አልቻለም። ይህም በወደፊቱ ተስፋ ላይ ፍርሃት እንዲነግስ አድሮታል። ይህን ስንመለከት ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ዓለማችን የሰው ልጅ ከተለያዩ ማሕበራዊ ችግሮች ተላቆ ለኑሮ ተስማሚ ዓለም መገንባት ችሏል ወይስ አልቻለም ብለን እንድንጠይቅ አደርጎናል። ይህ ሁኔታ በኢጣሊያ የተካሄደውን የ1968 የለውጥ ሂደትን የኖርን እኛን ክርስቲያኖችን የሚመለከት በመሆኑ ከሌሎች የለውጡ አራማጆች ጋር በመሆን ከዚህ ለውጥ ምን ተምረናል በማለት ራሳችንን እንድንጠይቅ ያስፈልጋል። ስለዚህ እንዴት ብናደርግ ነው የሚበጀንን እና የሚጠቅመንን ማድረግ የምንችለው ብለን ስንጠይቅ፣ የሰውን ልጅ የሚፈታትኑ ሁለት ነገሮች እንዳሉ ማወቅ መልካም ነው። የሰው ልጅ ራሱን የሚጠቅም፣ የሚኖርበትን ዓለም የተሻለ የመኖሪያ ስፍራ እንዳያደርግ እንቅፋት ሆነው የቆዩ ሁለት ነገሮች እንዳሉ ተገንዝበናል። የመጀመሪያው የሰው ልጅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየ የመጣውን የማሰብ ችሎታ ማደግ ተከትሎ ዓለምን በቁጥጥሩ ሥር ለማድረግ ካለው ፍላጎት የተነሳ፣ ከሌላ ሃይል ጋር ከመተባበር ይልቅ ብቻውን ተወስኖ መቅረትን በመምረጡ ሲሆን ሁለተኛው እንቅፋት፣ ማንኛውንም ለውጥ ሆነ ተግባር ለማከናወን የሚረዳ አቅም፣ ጉልበት እና ጥበብ በእጁ እንዳለ በማመኑ ነው ብለዋል። ክርስቲያን እነዚህን ሁለት እንቅፋቶች ለማስወገድ ከፈለገ ለእድገት፣ ለለውጥ ያለውን ምኞት እና ፍላጎት መተው ያስፈልጋል ወይ ለሚለው ጥያቄ መልሱ፣ ክርስቲያን የተሻለ ዓለምን ለመገንባት ያለውን ምኞት ማቋረጥ ሳይሆን ከእምነት የሚያገኘውን ጸጋ ሳይጠቀምበት ቀርቶ ወደ ስህተት መንገድ እንዳሄድ  መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ምክንያቱም እውነተኛ እምነት ለለውጥና ለእድገት ያለን ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲሄድ ስለሚያደርግ መገደብ አይቻልም ብለዋል። የለውጥ ፍላጎት መነሻውን ያገኘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰዎች መካከል በመመላለስ፣ የፍቅርና የወንድማማችነት ስሜት እንዲያድግ ምሳሌ በመሆኑ፣ ዓለም ወደ መልካም የመኖሪያ ስፍራ እንዲለወጥ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።  ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን ሃሳብ በመልዕክታቸው ሲገልጹ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ያለፈ ታሪክ ሳይሆን፣ የሞተና  ሁሉ ያበቃለት ይመስል የነበረ ዓለም ሕይወት የዘራበት ወደር የሌለው ሃይል የተገለጠበት ነው በማለት አስረድተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለስብሰባው ተካፋዮች በላኩት መልዕክታቸው፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሚገኝ፣ ወደር ካማይገኝለት መለኮታዊ ሃይል በቀር የሰውን ምኞት ሊያረካ የሚችል ሌላ ሃይል የለም ብለዋል። ከማያቋርጥ ምኞት ጋር የፈጠረን እግዚአብሔር፣ የራሱን ዘለዓለማዊነት ሊገልጥልን የፈለገው ሰው ሆኖ በመገለጡ ነው  ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሰኔ ወር 2009 ዓ. ም. ወደ ላቲን አሜርካ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ወቅት፣ አምስተኛ ጉባኤያቸውን ላካሄዱት የላቲን አሜርካ እና የካረቢያን ብጹዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደገለጹት፣ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ሰው ሆኖ የተገለጠበት ምክንያት ለሰዎች ድህነትና ሰዎችም በመካከላቸው የፍቅርን፣ የደስታንና የአንድነት ፍላጎት በማሳደግ፣ የሚኖሩበትም ዓለም ለሕይወት መልካም ስፍራ እንዲሆን ለማድረግ ያላቸውን ምኞት እውን ለማድረግ በመፈለጉ ነው ብለዋል።   

20 August 2018, 15:15