ፈልግ

poveri poveri 

ቤተ ክርስቲያን በሕያው ትምህርቶችዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገች መሆኗ ተገለጸ።

ቤተ ክርስቲያን በ2000 ዓመት የክርስትና ጉዞዋ፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት ባደረገ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ባሕል በመታገዝ፣ እምነት በሚሰጣት ጥበብ በሕያው ትምህርቶችዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቤተ ክርስቲያን በ2000 ዓመት የክርስትና ጉዞዋ፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት ባደረገ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ባሕል በመታገዝ፣ እምነት በሚሰጣት ጥበብ በሕያው ትምህርቶችዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ።

በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህረተ ክርስቶስ ላይ ስለ ሞት ቅጣት ፍርድ የተጠቀሰው ሃሳስብ ተሻሽሎ መቅረቡ በዓለም ደረጃ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። በየጊዜው በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ላይ የሚደረጉ ተሻሽሎዎች ገንቢ አስተያየቶችን እንድትቀበል ከማድረግ በተጨማሪ ቅሬታዎችንም ሳያስከትል አልቀረም። የፍቅር ሐሴት በሚል ርዕስ በቤተ ሰብ ዙሪያ ባቀረቡት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን የሞት ቅጣት ፍርድን በተመልከተ ቤተ ክርስቲያን ያላት አቋምን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ቤተ ክርስቲያን ያለፈችባቸውን 2000 ዓመታ መለስ ብለን ያየን እንደሆነ በአስተምሮዎቿ መካከል ብዙ ተሻሽሎዎች መደረጋቸውን እንረዳለን። እያንዳንዱ ለውጥ ወይም ተሻሽሎ ክርክሮችን ፈጥሮ ነበር።

የሞት ቅጣት ፍርድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣

ምን ያህል መሻሻል እንደተደረገ ለመረዳት ከተፈለገ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማንበብ በቂ ይሆናል። በዛሬው ዘመን ላይ ሆነን፣ በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ ዘሌዋውያን ምዕ. 20ን ብናነብ፣ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጣቸው ትዕዛዛት በጣም ልንደናገጥ እንችላለን። ጣዖት አምላኪዎች፣ አመንዝራዎች፣ ሰዶማዊያን፣ አባቶችንና እናቶችን የሚበድሉ ሰዎች እንዲገደሉ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት ነበር። ሙሴ በዚህች ምድር ከ3000 ዓመታት በፊት የኖረ ቢሆንም፣ እነዚህ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱ ቢሆንም ዞሮ ዞሮ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ናቸው።

በቀደምት ክርስቲያኖች ወቅት የታዩ የአስተምህሮ እድገቶች። 

በጥንት ዘመን ከአይሁድ እምነት ወደ ክርስትና የተቀየሩት ክርስቲያኖች አሰቃቂ ሁኔታ ብናስብ፣ መሠረታዊ የሆነውን የሕዝባቸውን ሕግ ትተው ለመሄድ ምን ያህል ቆራጥ ድፍረት ነበራቸው። ህገወጥ መሆኑን እያወቁ በክርስቲያናዊ ማህበር ውስጥ አረማውያንን ለመቀበል ምን ያህል የአዕምሮና የመንፈስ ክፍትነት ነበራቸው። በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እንደተገለጸው ሐዋርያው ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን አስቀድሞ የተቀበለ መሆኑን አልተረዳም ነበር። በኋላ ላይም ተገልጦለት በሮማዊው መቶ አለቃ በቀርኔሌዎስና በቤተሰቡ ፊት ቀርቦ እንዲህ አለ፦ በእውነት እግዚአብሔር በሰዎች መካከል ምርጫን እንደማያደርግ እያወቅሁ ብመጣም፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ፍትህን የሚያደርግ፣ የማንም ሕዝብ ወገን ይሁን፣ እርሱን ብቻ እቀበለዋለሁ በማለት ለእስራኤል ልጆች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን በማለት መልካም ዜናን ላከ። በዚህ መልዕክት ውስጥ ጴጥሮስ፣ እግዚአብሔር በሰዎች መካከል ምርጫን እንደማያደርግ እያወቅሁ ብመጣም የሚለውን ስንመለከት፣ እኛም የእግዚአብሔርን እውነትነት ለማወቅ ያለን ችሎታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፣ እያደገ የሚመጣ መሆኑን እንገነዘባለን። ቤተ ክርስቲያን እስካለች ድረስ፣ የእምነታችንም እውቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያድግ በመሆኑ ይህ ጉዞ የሚቆም ወይም የሚያበቃ አይደለም።

የመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤዎች፣

የክርስቲናን መሠረታዊ እውነቶችን ለመያዝ ተብሎ በቅድስት ሥላሴ እና በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ላይ የተደረጉ የመጀመሪያዎቹን የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤዎች የተመለከትን እንደሆነ “ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ምንም መዳን የለም” የሚለው እልህ አስጨራሽ ክርክር ብንወስድ፣ ያልተጠመቁት በሙሉ ይፈረድባቸዋል ማለት ነው። በተቃራኒው፣ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ፣ ካርዲናል በነበሩበት ጊዜ ያጸደቁትን ሰነድ የተመለከትን እንደሆነ፣ የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በመንፈስ ቅዱስ በኩል፣ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ምስጢራዊ ግንኙነትን በመፍጠር ክርስትያን ያልሆኑትንም ጭምር፣ በእግዚአብሔር ማዳን ተካፋይ ያደርጋቸዋል። በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንደተጠቀሰው፣ እግዚአብሔር የመዳኑን ጸጋ  እርሱ በሚፈልገው መንገድ ለሁሉም ያድላል። በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የእግዚአብሔር እቅድና ፍላጎት ምን እንደሆነ እያወቅን እንመጣለን።

መናፍቅነት እና አመጽ

ከመናፍቃንና በተለየ መንገድ ከሚያስቡ ተቃዋሚዎች ጋር የተደረገ ትግል በሃይማኖቶች መካከል ጦርንርትን በማነሳሳት ምን ያህል ጉዳት እንዳስከተለ ከታሪክ እንረዳለን። ብዙ የጸረ ካቶሊክ እምነት ቅስቀሳዎች በታሪክ ተመራማሪዎች በኩል እንዲወገዱ ቢደረግም እዉነትን መሰወር አይቻልም። ቤተ ክርስቲያን የጊዜውን አስተሳሰብ ስትጋራ ኖራለች። በ1244 ዓ. ም. በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ኢኖሴንሲዮ የታወጀው እና በ1251 ዓ. ም. በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት አሌሳንድሮ 4ኛ እና በ1257 ዓ. ም. በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቀለሜንጦስ 4ኛ የጸደቀው ሰነድ፣ በዘመናችን ታሪክ ጸሐፊዎች እጅግ በጣም የተወሳሰበ ቢሆንም፣ ተጠርጥረው የተያዙ መናፍቃን ለሞት ሳይዳረጉን እና የአካል ክፍልን ሳያጎድሉ እንዲገረፉ እና ለስቃይ እንዲዳረጉ ያደርግ ነበር። ይህ የሆነበትም ምክንያት የነፍስ ድነትን ጉዳይ ግንዛቤ ውስጥ በማካተት ነበር። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ስንት ለውጦች ተካሂደዋል።

ቀስ በቀስ የመጣው የሂሊና ነጻነት፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 16ኛ፣ ከ200 ዓመት በኋላ በ1824 ዓ. ም. የጻፉትን “ሚራር ቮስ” ወይም “በእናንተ ላይ” የተሰኘን የሐዋርያዊ መልዕክት አስተምሮን ስንመለከት ብዙ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ተሻሽሎ የቀረበበትን ምክንያት እንገነዘባለን። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 16ኛ፣ የሂሊናን ነጻነት ቤተ ክርስቲያንንና መንግሥትን ወደ ጥፋት ጎዳና እንደመራ ያስረዳሉ። ከዚህ መልዕክታቸው ቤተ ክርስቲያን የሂሊና ነጻነት፣ በጊዜው በነበረው አስተሳሰብ ሲገለጽ ቤተ ክርስቲያንን ሆነ መንግሥትን በጣም እንደጎዳቸው ተገንዝባለች።

በሚለዋወጠው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ምክንያት የሚሰማ ሃፍረት

የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሻሻል በእምነት መካከል ሊከሰት የሚችለውን ችግር ለመሸፈን መንገድ ከፍቷል። የማይሻር ወይም የማይለወጥ ሕግ ለሕዝቡ እርግጠኝነትን እና ድጋፍን በመስጠት ሌላ መንገድ እንዳያስቡ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን የሚሻር ወይም የሚለወጥ ሕግ የሕዝቡን መብት ከመርገጥ ይልቅ የተለያዩ መንገዶችን ያስቀምጥላቸዋል። ይህም በኢየሱስ እና በፈሪሳዊያን መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጎላ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ያስቀመጣቸው ሕጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያድገውን የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ የተመለከተ ሲሆን የፈሪሳዊያን ሕግ ደግሞ በጽሁፍ የሰፈረ የማይፋቅ የማይደለዝ ነበር። ሕግ ነጻነት ያለበት ከሆነ የሕዝቡን የመናገር ሃሳብ የመስጠት መብት አይገድብም። ፍቅር የታከለበት ሕግ ግን ድፍረትን በመስጠት ለራስ ብቻ ከሚለው አመለካከት ውጥቶ ለሌላውም እንድናስብና እንድንጨነቅ ያደርጋል።

እውነትን መቀበል

ወደ ጴጥሮስ ታሪክ ስንመለስ በአሕዛብ መካከል የእውነት ባለቤት እርሱ ራሱ እንዳልሆነ ነገር ግን የእውነት ወገን ብቻ እንደሆነ በሚገባ አውቋል።  ይህ የእውነት ባለቤት የሆነው መንፈስ ቅዱስ የእርሱን ትምህርት ያዳምጡ በነበሩ ሰዎች ላይ በወረደ ጊዜ በአህዛብም ላይ በወረደ ብለው ተመኝተው ነበር።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮ ሐንስ ጳውሎስ 2ኛን እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስን ለሚቃወሙት በሙሉ አጽናኝ የሆነውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በሚያዚያ ወር 1998 ዓ. ም. በክራኮቪያ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሕይወታችሁን መሠረት በቤተ ክርስቲያን ላይ ለመመስረት ፍርሃት አይዛችሁ፣ ለቅዱስ ጴጥሮስ በምታሳዩት ፍቅር እና ለእርሱ አደራ በተሰጣት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላላችሁ ኩሩዎች ናችሁ። ለኢየሱስ ክሶትስና እርሱ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን በሚቃወሙት ሰዎች ምክንያት ጥርጣሬ አይግባችሁ። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛን ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ፣ ከጸባኦት በመሆን እናንተን የሚመለከታችሁን ጴጥሮስን በሚገባ ታውቁታላችሁ ብለው አሁን ያለው ጴጥሮስም ቢሆን ወደ ፊት የሚመጣው ጴጥሮስም ቢሆን ማንም ሊቃወማችሁ አይችልም። በጽኑ ዓለት ላይ ሕይወታችሁን በኢየሱስ እና ከኢየሱስ ጋር ሆናችሁ ለምትገነቡት ቤታችሁ ድጋፍ ይሰጧችኋል ብለዋል።

06 August 2018, 15:50