ፈልግ

9ኛ የዓለም የቤተሰብ ጉባሄ በደብሊን 9ኛ የዓለም የቤተሰብ ጉባሄ በደብሊን 

ቤተሰብ በዓለም ውስጥ መልካም ዜና ሆኖ መኖሩን ቀጥሉዋል”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቤተሰብ በዓለም ውስጥ መልካም ዜና ሆኖ መኖሩን ቀጥሉዋል”

“በየደረጃው ለሕይወት ራሱን ክፍት ያደረገ፣ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት ኅብረት ላይ የተመሰረተ ቤተሰብ፣ በዓለም ውስጥ መልካም ዜና ሆኖ መኖሩን ቀጥሉዋል” በማለት ከነሐሴ 21-26 2018 ዓ.ም በደብሊን ከተማ ለሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን ዝግጅት ይሆን ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጋቢት 21/2009 ዓ.ም. መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

አንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 21-26 2018 ዓ.ም በደብሊን ከተማ የሚካሄደው ዓለማቀፍ የቤተሰብ ጉባሄ “የቤተሰብ ወንጌል ለዓለም ደስታ ነው” በሚል መርህ ቃል እንደ ሚከበረ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የቤተሰብ ቀን ለማክበር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እይተደረጉ መሆኑን ከደረሰን መረጃ ለመገንዘብ ተችሉዋል።

ይህ ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን የቤተሰብ ሕይወት ይበልጡኑ ይጠናከር ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም. በላቲን ቋንቋ “አሞሪስ ላይቲሲያ” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በዚህ በዓለማቀፍ ደረጃ በሚከበረው የቤተሰብ ቀን በግባዐትነት በመጠቀም በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር የሚተነትን ቃለ ምዕዳን በመሆኑ የቤተሰብ አባላት በዚህ ቃል ምዕዳን ውስጥ የተጠቀሱትን ቁምነገሮች በመጠቀም የቤተሰብ ሕይወትን ለማጠናከር ጥረት እንደ ሚደረግ ተገልጹዋ

ይህ በዓለማቀፍ ደረጃ በአየርላንድ ዋና ከተማ በደብሊን የሚከበረው የቤተሰብ ቀን ምክንያት በማድረግ ላለፉት በርካታ አመታት አዲስ ቤተሰብ የሚመሰርቱ ጥንዶችን በማዘጋጀት ሥራ ላይ የተጠመደው እና የፎኮላሬ ማኅበር በመባል የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ማኅበር አባል የሆኑት ጥንድ ባለትዳር የሆኑት ሀና ፍሪዞ እና አልቤርቶ ለብዙ አመታት በተለያዩ አከባቢዎች የተካሄዱት የቤተሰብ ጉባሄዎች ላይ ተሳታፊ የነበሩ ከሬዲዮ ቫቲካን ከጣሊያነኛው የስርጭት ክፍል ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ገለጹት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅርቡ በደብሊን የሚካሄደው የቤተሰብ ቀን በጣም አስፈላጊ እና ወቅታዊ የሆነ ጉዳይ በመሆኑ መደሰታቸውን ገለጸዋል።

ሀና ፍሪዞ እና አልቤርቶ እ.አ.አ ከ1994 ጀምሮ በዓለማቀፍ ደረጃ የተካሄዱትን የቤተሰብ ጉባሄዎችን መካፈላቸው ከሬዲዮ ቫቲካን ጋር በነበራቸው ቆይታ መገለጻቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም ቤተሰብን በተመለከተ ያላቸው ሐዋሪያዊ ግንዛቤ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር እንዳስቻለ ጨምረው ገልጸዋል።

ሀና ፍሪዞ ኣና አልቤርቶ በፎኮላሬ ማኅበር ውስጥ ቤተሰብን የሚመለከት ሐዋሪያዊ እንቅስቃሴን በበላይነት እየመሩ እንደ ሚገኙ መናገራቸውን ለመገንዘብ የተቻለ ሲሆን በተለይም ደግም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም. “አሞሪስ ላይቲሲያ” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር የሚተነትን ቃለ ምዕዳን በመሆኑ አዲስ ተጋቢ ጥንዶች ፍቅር የሁሉም ቤተሰብ መሰረት መሆኑን በመረዳት በተቸላቸው መጠን ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ እንዲደራጅ ሊሰሩ እንደ ሚገባ በማስተማር ላይ መሆናቸውን ገለጸዋል።

አሁን በምንኖርበት ዓለማችን በቤተሰብ ደረጃ ሁለት ዋና ዋና ችግሮች ወይም ተግዳሮቶች እንደ ሚታዩ የገለጹት ጥንዶቹ ሀና ፍሪዞ እና ሮቤርቶ እነዚህም አሁን በዘመናችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተነጸባረቀ የሚገኘው የራስ ወዳድነት መንፈስ ዋነኛው እና ተቀዳሚው ተግዳሮት መሆኑን ገለጸው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ነገሮችን በንጽጽር የመመልከት አባዜ ደግሞ አሁን በሚገኘው ዓለማችን ውስጥ ባሉ ቤተሰቦች ውስጥ እይተከሰተ የሚገኝ ሁለተኛው ተግዳሮት መሆኑን ጨምረወው ገለጸዋል።

እነዚህ ቀደም ሲል የተጠቀሱት ተግዳሮቶች በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ቤተሰብ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመንጸባረቅ በባል እና በሚስት መካከል መናበብ እንዳይኖር እንቅፋት በመፍጠር በቤተሰብ ሕይወት ላይ ጫና እየፈጠሩ የሚገኙ ጉዳዮች መሆናቸውን ጨምረው ገለጸው በተለይም ደግሞ እኛ ክርስቲያን የሆን የማኅበርሰብ ክፍሎች የእግዚኣብሔርን የደኅንነት ምስጢር በጥልቀት በመረዳት እርሱ የፈጠረን እና የጠራን በእርሱ በራሱ መልክ እና አምሳል በመሆኑ የተነሳ ይህንን በመረዳት ይህንን መገለጸ በሚችል መልኩ በመቻቻል እና በፍቅር ልንኖር የገባል ብለዋል።

በተለይም ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ “አሞሪስ ላይቲሲያ” በአማሪኛው የፍቅር ሐሴት በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ቃለ ምዕዳን በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር፣ በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ ተግዳሮቶች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለቤተሰብ ማድረግ ሰለሚጠበቅባቸው ሐዋሪያዊ እንክብካቤ የሚያወሳ ድህረ ሲኖዶስ አዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በመሆኑ የተነሳ በአሁኑ ወቅት በቤተሰብ ውስጥ እየተከሰቱ የሚገኙ ተግዳሮቶች ለመፍታት ከፍተኛ እገዛ እንደ ሚያደርግ ጨምረው ገለጸዋል።

በእዚህ ቃለ ምዕዳን በተለይም የሐይማኖት አባቶች በቤተሰብ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በጥንቃቄ እና ብስለት በተሞላበት መልኩ፣ በጥንቃቄ በመመርመር በቤተሰብ ውስጥ የሚያግጥሙ ችግሮችን በችኮላ ከማውገዝ ይልቅ በእግዚኣብሔር ምሕረታዊ ጸጋ በመታገዝ የመፍትሄ ሐሳቦችን መጠቆም እንደ ሚገባቸው እና ይህንንም ክህሎት ማዳበር እንድችሉ ቤተሰብን የተመለከተ ትምህርቶች ከዘረዓ ክህነት ጀምሮ መስጠት አስፍላጊ መሆኑን የሚገልጽ ቃለ ምዕዳን በመሆኑ የተነሳ የሐይማኖት አባቶች በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን በጥንቃቄ እንዲፈቱ የሚመክር ቃለ ምዕዳን በመሆኑ ውስብስብ የቤተሰብ ጉዳዮችን ለመፍታት የሚያስችል ቃለ ምዕዳን በመሆኑ መደሰታቸውን ጨምረው ገለጸዋል።

11 August 2018, 15:47