ፈልግ

የሎዮላው እግናሽዬስ ከኢየሱስ ጋር የጠበቀ ፍቅር መስርቶ ነበር

የሎዮላው እግናሽዬስ ከኢየሱስ ጋር የጠበቀ ፍቅር መስርቶ ነበር

የኢየሱሳዊያን ማኅበር መስራች የነበረው የሎዮላው እግናሽዬስ ከእግዚኣብሔር ጋር ፍቅር ይዞት እንደ ነበረ ተገለጸ። እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1491 ዓ.ም በሎዮላ በእስፔን ሀገር እንደ ተወለደ የሚታወቅ ሲሆን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ውስጥ ከሚገኙ በተለያዩ ቅዱሳን አማካይነት ከተመስረቱ እና የተለያየ ዓይነት መንፈሳዊነትን ከሚያነጸባርቁ የካቶሊክ ቤተክርስትያን መንፈሳዊ ማኅበራት ውስጥ አንዱ የሆነውን የኢየሱሳዊያን ማኅበር በመባል የሚታወቀውን ማኅበር የመሰረት ቅዱስ እንደ ሆነ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ውስጥ በተነሳው የለውጥ ሂደት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመሳተፍ አዎንታው የሆነ ለውጥ በቤተክርስትያኗ ውስጥ እንዲመጡ ካደርጉ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ቅዱስ ነው ቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ።

የዚህ የኢየሱሳዊያን ማኅበር መስራች የሆነው የታላቁ ቅዱስ የቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ አመታዊ በዓል የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ምዕመናን ዘንድ በዛሬው እለት ማለትም በሐምሌ 24/2010 ዓ.ም ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህንን አመታዊ በዓል በምናከብርበት ወቅት ቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ በዘመኑ የነበረውን በተለይም ያደርጋቸው የነበረውን መንፈሳዊ ልምምዶች በሕይወቱ ከፍተኛ መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጣ ካስቻሉት መንፈሳዊ እሴቶች መካካለ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሲሆን ይህ መልካማ የሆነ መነፈሳዊ ተመክሮ ከኢየሱሳዊያን ማኅበር ባሻገር በተለያዩ በካቶሊክ ቤተክርስትያን ጥላ ሥራ በሚተዳደሩ መንፈሳዊ ማኅበራት ውስጥ በአሁኑ ወቅት በሰፊው የሚንዘባረቅ መንፈሳዊነትን የማጠናከሪያ ዘዴ እንደ ሆነ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኋይሌጊዮርጊስ- ቫቲካን

የቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ አመታዊ በዓለ ባለፈው አመት በተከበረበት ወቅት የካቶሊክ ቤተክርስትያን የመጀመሪያው ኢየሱሳዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ፍርናቸስኮስ በወቅቱ በቲውተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት እንደ ገለጹት “የቅዱስ እግናሽዬስን አብነት በመከተል ሌሎችን ለማገልገል ራሳችንን እናዘጋጅ” የሚል ይዘት ያለው መልእክት በቲውተር ገጻቸው ላይ አስፍረው እንደ ነበረ ይታወሳል።

ይህ መልእክት ቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ በሕይወቱ በቅድሚያ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት በመንፈሳዊ ልምምዶች አማካይነት በማጠናከር፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጸሎት በማድረግ እና የእግዚኣብሔር ቃል በውስጡ ሰርጾ እንዲገባ በማስተዋል ጥበብ በተሞለው መልኩ የእግዚኣብሔር ቃል ላይ አስተንትኖ በማድረግ እነዚህን መንፈሳዊ እሴቶችን በግባትነት በመጠቀም ሌሎችን ለማገልገል ራሱን አዘገጅቶ እንደ ነበረ ይታወሳል። ቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ ከጌታ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ከመመስረቱ በፊት ምደራዊ  ስልጣንን እጅግ በጣም በሚባል መልኩ የሚወድ እና ቀጥሎም ይህንን ምኞቱን እውን ለማድረግ ጠንክሮ ይሰራ እንደ ነበረ ከሕይወት ታሪኩ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ነገር ግን መንፈሳዊ ልምምዶችን በማድረግ  ከእግዚኣብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፣ በጸሎት እና የእግዚኣብሔር ቃል ጠንቅቆ በማደመጥ እነዚያን ምድራዊ የሆኑ ምኞቶቹን ልያሸናፋቸው ችሉዋል።

ተራማጅ መንፈሳዊ ተጓዥ

የቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ ቅዱስ አጽም በሮም ከተማ በኢየሱስ ስም በተሰየመ ቤተክርስትያን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይህንን በተመለከተ የሬዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ የሆነችው በኔዴታ ካፔሊ ከአባ ጂን ፓውል ሄርናዴዝ ጋር ባደረገቺው ቆይታ አባ ጂን ፓውል እንደ ገለጹት ቅዱስ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ “የታሪክ ሂደቶች እና ለውጦችን በጥንቃቄ የሚከተተል” ሰው እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አዘውትረው እንደ ሚናገሩት . . .

“ቤተክርስትያን ከጊዜው ጋር እኩል መራመድ ይኖርባታል” የሚል አቋም እንደ ነበረ ጨመረው ገለጸዋል። የኢየሱሳዊያን ማኅበር ቁልፍ ከሆኑ መንፈሳዊ እሴቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነው “ማነኛው ተዐዝዞ - ነጻ ከሆነ ልብ ሊመነጭ የገባዋል”የሚለው እንደ ሆነ ይታወቃል። አንድ የኢየሱሳዊ ማኅበር አባል የሆነ ሰው በቅድሚያ ራሱን ለእግዚኣብሔር አገልግሎት በመስጠት ከእዚያን በመቀጠል ደግሞ ነባርዊ የሆኑ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ በመመርመር፣ ይህንንም ጥልቅ በሆነ መንገድ በማሰላሰል በጸሎት ኃይል በመታገዝ ወይም በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔዎችን በማድረግ ለወቅታዊ ሁኔታዎች ወቅታዊ እና ተመጣጣኝ የሆነ መፍተሄ ማስቀመጥ ተቀዳሚው ተገባሩ ነው።

የዛሬው ዘመን የኢየሱሳዊያን ማኅበር አባላት ምን እየሠሩ ይገኛሉ

ይህንን በተመለከተ ከሬዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኛ የሆነችው በኔዴታ ካፔሊ ከአባ ጂን ፓውል ሄርናዴዝ ጋር ባደረገቺው ቆይታ አባ ጂን ፓውል እንደ ገለጹት “በዛሬው ዘመን የሚገኙ የኢየሱሳዊያን ማኅበር አባላት ሁሉም በተፍጥሮ የተሰጠውን መክሊት እና ልዩ ስጦታ ሳይናሳዊ በሆነ መልኩ ወይም ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ ማዳበር ተቀዳሚ የሆነ ተግባር እንደ ሆነ” መግለጻቸው የታወቀ ሲሆን በመቀጠልም በትምሕርት ያገኙትን ክህሎት በመጠቀም ቤተክርስትያን በአሁኑ ወቅት ባለው ዓለማችን እያደርገች የምትገኘውን አዲስ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል በማገዝ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሰፊዊ ከሚታዩ የዓለማችን ተግዳሮቶች መከከል በዋነኛነት የሚጠቀሰውን የስደተኞች ፍልሰት በተቀናጀ መልኩ ለማስተናገድ የሚደርገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እያገዙ ይገኛሉ” በማለት ጨምረው ገለጸዋል።

 

Photogallery

ቅዱሱ እግናሽዬስ ዘ ሎዮላ
31 July 2018, 16:01