ፈልግ

ዶክተር ጳውሎ ሩፊኒ በቅድስት መንበር የኮምንኬሽን ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ጳውሎ ሩፊኒ በቅድስት መንበር የኮምንኬሽን ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ 

ጳጳሳዊ የመገናኛ ጽሕፈት ቤት እና የምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባኤ ሕብረት አገሮች ትብብር

የቅድስት መንበር የመገናኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት ክቡር አቶ ፓውሎ ሩፊኒ፣ በአዲስ አበባ ውስጥ በመካሄድ ላይ ላለው 19ኛው የምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ሕብረት ጉባኤ በላኩት መልዕክት፣ በቅድስት መንበር የመገናኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት እና በምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ መካከል ትብብር ሊኖር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በቅድስት መንበር የመገናኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና በምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሕብረት መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ተነገረ።

የቅድስት መንበር የመገናኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት ክቡር አቶ ፓውሎ ሩፊኒ፣ በአዲስ አበባ ውስጥ በመካሄድ ላይ ላለው 19ኛው የምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ሕብረት ጉባኤ በላኩት መልዕክት፣ በቅድስት መንበር የመገናኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት እና በምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ መካከል ትብብር ሊኖር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ክቡር አቶ ፓውሎ ሩፊኒ በመልዕክታቸው፣ በእነዚህ ሁለት ግዙፍ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተቋማት መካከል የሚኖረው ጠንካራ ግንኙነት፣ አፍሪቃ በቅድስት መንበር የመገናኛ ተቋም በኩል የወንጌልን መልካም ዜናን ለማብሰር የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን መልዕክት ለአፍሪቃ ሕዝብ ለማሰማት ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም ዙሪያ በስፋት ከሚነገርለት የፍሪቃ ጦርነት፣ በሽታ፣ ድህነት እና እርዛት ሌላ፣ ስለ አፍሪቃ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት እና ፍሬያማነትም መመስከር ይቻላል ብለዋል። ክቡር አቶ ፓውሎ ሩፊኒ፣ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤታቸው ለምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሕብረት ያላቸውን ወዳጅነት እና በጎ አመለካከት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ. ም. የተከፈተው የጳጳሳቱ ሕብረት አገሮች ጉባኤ፣ በ1986 ዓ. ም. የተካሄደው የጳጳሳት ሲኖዶስ ካበረካታቸው በርካታ ውጤቶች መካከል በምስራቅ አፍሪቃ በሚገኙ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከቶች ውስጥ በርካታ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲከፈቱ መልካም ዕድልን ያመቻቸ እንደነበር፣ የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ የመገናኛ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ክቡር አቶ ፓውሎ ሩፊኒ አስታውሰው የእነዚህ ሬዲዮ ጣቢያዎች በምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከቶች እንዲከፈቱ መወሰኑ፣ ትንቢታዊ፣ ድፍረት የተሞላበት እና የመጭውን ጊዜ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እንደሆነ፣ እንዲሁም ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ሆኗል ብለዋል። ዋና ተጠሪው ይህን ካሉ በኋላ ቅድስት መንበር በጳጳሳዊ ማሕበርዊ መገናኛ ተቋሟ እያደረገች ያለችው ተሃድሶ ከሌሎች ካቶሊካዊ ሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር ሊኖር የሚገባዉን መተጋገዝ የበለጠ እንዲሆን ከማድረጉ በላይ እየተደረገ ያለው ተሃድሶ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስደሳች ውጤቶችን አስገኝቷል ብለዋል። በተጨማሪም ቅድስት መንበር በመገናኛ ዘርፍ የወሰደችው ተሃድሶ፣ ከሌሎች የመገናኛ አውታሮች ጋር ያላትን ግኑኝነት እና ትብብርን ከፍ ካማድረጉ በተጨማሪ፣ የቫቲካን ሬዲዮም አድማሱን ሰፋ በማድረግ በዓለም አቀፉ የመገናኛ ዘርፍ ተርታ እንዲገባ አድርጊታል ብለዋል።

በቅድስት መንበር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ጳጳሳዊ መገናኛ ተቋማት እንዲዋዱ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልካም ምኞት መሆኑብ በሌሎች አገሮች ውስጥ የሚታየውን የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች እጥረት በማስወገድ የዕድሉ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል። በቫቲካን ጳጳሳዊ መገናኛዎች የተደረገው ተሃድሶ በቴክኖሎጂ ወደ ኋላ የቀሩትን፣ በተለይም የአፍሪቃ አገሮች በማስተባበር በመካከላቸው የተጠናከረ ሕብረት እንዲፈጠር ያደርጋል ብለዋል። ዋና ተጠሪው እንደገለጹት የቫቲካን ሬዲዮ ዘመኑ ባፈራቸው የዲጂታል መሣሪያዎች እና የአጠቃቀም መንገዶች ከመታገዝ በተጨማሪ የቆዩ ዜዴዎችንም በመጠቀም ገና በማደግ ላይ ያሉትንም አገሮች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የስርጭት                                                                                                                  አድማሱን አስፍቷል ብለዋል።

በየቅድስት መንበር ጳጳሳዊ የመገናኛ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት ክቡር አቶ ፓውሎ ሩፊኒ በመጨረሻም የምስራቅ አፍሪቃ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሕብረት ስብሰባ እና የሁለቱ አገሮች ማለትም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንገሥታት በመካከላቸው አዲስ ግንኙነትን በመፍጠር ለሰላም፣ ለፍቅር እና ላሕዝባቸው ብልጽግና በጋራ ለመሥራት ቆርጠው የመነሳታቸው አጋጣሚ በተመሳሳይ ወቅት መሆኑ የብጹዓን ጳጳሳትጉባኤ ሕብረት ስብሰባን ልዩ ያደርገዋል ካሉ በኋላ፣ አፍሪቃ አሁን በምትገኝበት በርካት ግጭቶች መካከል የሁለቱ አገሮች ለሰላም ቆርጠው መነሳታቸው ከአገሮቹ አልፎ ተርፎ ለአፍሪቃ ቀንድ እንዲሁም ለመላው አፍሪቃ የተስፋ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ያደርጋል ያሉትን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የደስታ መልዕክትን አስታውሰዋል።  

Photogallery

19ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት ጉባኤ በኢትዮጵያ
17 July 2018, 08:58