ፈልግ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ  

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም.

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

ለአገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ የስራ ዘርፎች በተለይም ላለፉት ዓመታት የግልገል ጊቤ ግድብ III ግንባታን በመምራት እና የኢትዮጰያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ በመሆን በታታሪነት ታላቅ አገልግሎት ሲያበረክቱ የቆዩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ቤተክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ነፍስ እግዚአብሔር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም፣ በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና በቅዱሳን ሁሉ መካከል በሰላም እንዲያሳርፍልን እንማጠናለን፡፡ ለኢንጂነር ስመኘው ቤተሰብ፣ የስራ ባልደረቦችና ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከየኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ

አባ ሐጎስ ሕይሽ

27 July 2018, 14:49