ፈልግ

የቻይና ምዕመናን በጸሎት ላይ  የቻይና ምዕመናን በጸሎት ላይ  

በቻይና፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን ለማከናወን የሚያስችላት ምቹ መንገድ

በቻይና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን እንድታከናውን ማስፈለጉ ቢታመንበትም ተግባራዊ ለማድረግ አስቀድማ ከቻይና መንግሥት ጋር ገንቢ ውይይቶችን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ታውቋል።

በቻይና፣  ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን ለማከናወን የሚያስችላት ምቹ መንገድ፣ የጋራ ውይይት እንደሆነ ተነገረ።

በቻይና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን እንድታከናውን ማስፈለጉ ቢታመንበትም ተግባራዊ ለማድረግ አስቀድማ ከቻይና መንግሥት ጋር ገንቢ ውይይቶችን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ታውቋል።

ቤተ ክህነት፣ እንዲሁም ምዕመናን በሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናቸው፣ የወንጌል መልካም ዜናን ለሌሎች የመመስከር ተልዕኮ ጥሪ አለባቸው። የዓለም ብርሃን እና የዓለም ጨው በመሆን፣ ምቹ ጊዜን ሳይጠብቁ እንዲሁም ምቹ ቦታን ሳይመርጡ በቻይና ሕዝብ መካከል ተሰማርተው መልካም ሥራቸው በሁሉም ሥፍራ በማከናወን ከእግዚአብሔር የሚሰጠውን የጸጋ በረከት የሚቀበሉበት ይሆናል። ይህ ከታመነበት ታዲያ፣ በቻይና የሚደረገውን የወንጌል አገልግሎት ልዩ የሚያደርገው ምንድር ነው? የሚል ጥያቄ ይነሳል።

የዚህ ዜና አዘጋጅ ዮሐንስ መኰንን

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቻይና መንግሥት ተረጋግቶ ከሌሎች መንግሥታት ጋር መግባባትን ከመፍጠር ይልቅ ለምዕራባዊያኑ ዓለም ልቡን እያጠበበ መምጣቱ ይስተዋላል። በሌላ ወገን “ቅድስት መንበር በዚህ መልኩ ከቻይና ጋር የምታደርገውን ውይይት እምነት በተሞላበት መንገድ፣ በዘላቂነት ልታካሂድ የምትችለው እንዴት ነው?” የሚሉም አልታጡም።

ቅድስት መንበር እስከ አሁን ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካካሄዳቸው ውይይቶች ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በተለይም በግጭቶችና በማሕበራዊ ቀውሶች መካከል ውይይቶችን ለመቀጠል እንቅፋት ፈጥረው የቆዩባቸው ቦታዎች የትኞቹ ናቸው ብለን ስንጠይቅ፣ ውይይቱ ያጋጣሚ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን። ከሁሉ በላይ፣ በዚህ ሂደት መካከል ቤተክርስቲያን የምዕመናኖቿን ደህንነት በመከታተል፣ በተለይም በከባድ ስቃይ ውስጥ ሲገኙ እንክብካቤን የመስጠት አደራ እና ሃላፊነት እንዳለባት ታውቃለች። በእርግጥ ይህ ሁኔታ ለአንዳንድ ተቋማት እንቆቅልሽ ሆኖ ቢገኝም ለቤተ ክርስቲያን ግን ሞራላዊ የሆነ የወንጌል ተልዕኮ ግዴታ በመሆኑ፣ በተግባር እንድታሳይ የሚያስችላት መንፈሳዊ ሃይል አላት።

በቻይና የወንጌል አገልግሎት ተልዕኮ ግዴታን ለመወጣት፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከቻይና መንግሥት ፈቃድ መጠበቅ የለባትም። በቆመችበት ዓላማ ቆራጥ እና እውነተኛ የወንጌል መልዕክተኛ መሆን ብቻ ይጠበቅባታል። በእርግጥ እስከ ዛሬ ሲያጋጣማት እንደቆየው ሁሉ፣ መሠረታዊ ነጻነትን የምትወሰድበት ወቅት ቢያጋጣማትም፣ ምን ጊዜም ቢሆን የወንጌል አገልግሎት ተልዕኮዋን የምታከናውንበትን መንገድ ማግኘት ትችላለች።

ከዚህም በላይ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዘመናት መካከል፣ የወንጌል ተልዕኮ አገልግሎቷን ለማከናወን በምትሰማራበት ሥፍራ ሁሉ ችርግ፣ ስደት እና መከራን ሳትቀበል የዘለቀችበት አጋጣሚ የለም። በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ወደ ደህና ደረጃ ደርሰዋል በሚባሉ አግሮችም ሳይቀር የተለያዩ ችግሮች ማጋጠሟ አልቀረም።

ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥማትም፣ እምነትን ያጣችበት፣ የቸርነት ሥራዋን ያጓደለችበት እና አንድነቷን ያጣችበት ጊዜ ወይም ዘመን የለም። እስካሁን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ አንድነቷ እና የበጎ አገልግሎት ሥራዋ ዘላቂ ሊሆን የበቃውም በሮማው ጳጳስ በሆኑት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የበላይነት በሚካሄደው ሐዋርያዊ አገልግሎት አማካይነት ነው።

በቻይና የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሕዝቦች መካከል አንድነቷን የጠበቀች እና እምነት የተጣለባት መሆን ነው። ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቻይና ሕዝብ መካከል የምትገኘው፣ በማንኛውም ጊዜ እና አጋጣሚ፣ በማንኛውም ሥፍራ፣ በዘመናት ሁሉ ከቻይና ሕዝብ ጋር በመኖር፣ ይህም ማለት ደስታቸውን እና ሐዘናቸውን አብራቸው በመካፈል፣ ችግራቸውን በሙሉ በመጋራት፣ ትህትና ያለበትን ክርስቲያናዊ ተስፋን በመጋራት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩትን የጸጋ ስጦታዎች ለሁሉ እንዲዳረስ ለማድረግ ነው።

ዛሬ በዘመናችን ያሉትን ታላላቅ ተግዳሮችን ስንመለከታቸው፣ ለምሳሌ በበርካታ አገሮች መካከል የሚደረገው የኤኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነቶች፣  የሰላም፣ የመልካም ሕይወት አኗኗር እና የአካባቢ ጥበቃ ሁኔታ እና  የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ የሚሉት ጥቂቶቹ ሲሆኑ፣ በሌላ ወገን ደግሞ በዓለም ላይ ባለው የፍጆታ መጠን የዓለማዊነት አስተሰሰብ ተስፋፍቶ የዕድገትን አቅጣጫ ማጨለሙ፣ አንዳንድ አገሮች ከሌሎች አገሮች ጋር ሊኖር የሚገባውን ግንኙነት በማጥበብ ወይም ጨርሰው በመዝጋት የሚፈጥሩት የግለኝነት አዝማሚያ፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች በአካባቢያቸው ወይም በሕዝቦቻች መካከል ለሚፈጠሩት ችግሮች ግድ የለሽ ሆነው መገኘት፣ በድህነት የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙትን እና አቅመ ደካማ የሆኑትን የሕብረተ ሰብ ክፍል መናቅ እና ማግለል፣ ቤተ ክርስቲያንም እነዚህ ማሕበራዊ ችግሮች ተስፋፍተው በሚገኙበት በዚህ ዓለም ውስጥ በመገኘት፣ ለዓለም መዳን ራሱን ለሞት አሳልፎ የሰጠውን፣ በመለኮታዊ ሃይሉ ከሞት ተለይቶ የተነሳውን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመስበክ ተጠርታለች።

ይህን በምንልበት ጊዜ፣ ሁሉም የተመቻቸ እና በጣም ቀላል ይመስላል። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንን የሚያጋጥሟት ችግሮች መጠነ ሰፊ ናቸው። ዞሮ ዞሮ አንድ ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ክርስቲያኖች መልካም አስተያየቶችን ቢያቀርቡ እና ቅን አካሄድ እንዳላቸው በተግባር እያሳዩ ቢሆንም የቻይና መንግሥት ግን በፍርሃትና እና በጥርጣሬ በመሞላቱ የተነሳ በርካታ እንቅፋቶችን ይደቅንባቸዋል፣ ያስራቸዋል ወይም ያንገላታቸዋል። የቻይና መንግሥት በሕዝቦቹ ላይ ይህን የመሰለ ግፍ ለምን ይፈጸምባቸዋል? በእውነቱ ቤተ ክርስቲያን የምትገኝበትን ሁኔታ በጥልቀት ማየት እና መረዳት ያስፈልጋል። የክርስትና ሕይወት መውደቅ እና  መነሳት ያለበት ነው። በውድቀታችን ጊዜ ሃጢአት እንሠራለን። ነገር ግን በቻይና ውስጥ ያሉት ክርስቲያኖች ቢያንስ መልካም ስራዎቻቸው ሙሉ ለሙሉ ሊዘነጋ አያስፈልግም።

የቻይና መንግስት ባለስልጣናት፣ ሃይማኖቶች ከኤኮኖሚያዊ መሻሻል እና ከማኅበራዊ ፍትህ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ለሰው ልጅ ማሕበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ የቆሙ እና ከዚያም በኋላ የሚከስሙ ክስተቶች እንዳልሆኑ ተገንዝቧል። ለዚህም ነው፣ እውነተኛ የሃይማኖት ተሞክሮ የሰውን እና የህብረተሰቡን ሰላማዊ የጋራ እድገት ለማምጣት ወሳኝ የሚሆነው። በሦስተኛው ሚሊኒየም፣ በተራቀቀና ውስብስብ በሆነ ማህበረ ሰብ ውስጥ እንኳን የቤተ ክርስቲያን መገኘት ለእድገት፣ ለሰላም እና ለማሕበራዊ ፍትህ ታላቅ ጥንካሬ እና ዋስትና ሆኖ ይኖራል። 

በቻይና ውስጥ መልካም ሥራን ሰርቶ ማለፍ፣ ጓደኝነትን መፍጠር፣ በትምህርት የግል ዕውቀትን ማሳደግ፣ ለባለሥልጣናት ታዛዥ ሆኖ መገኘት እንደ ባህላዊ ፍልስፍናቸው በሆነው እንደ ኮንፊሽየም የሚታይ ሲሆን መንግስት ደግሞ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ መብቱን በመጠቀም፣ ማንኛውንም ዓይነት ሃይማኖት ለመቆጣጠር እንዲችል  በጣም ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ ይሞክራል። በሌላ በኩል የቻይናውያን ታሪክ፣ የ19ኛውን እና የ20ኛውን ክፍለ ዘመን ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ገጠመኞች ያሉት በመሆኑ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አመለካከቶች እርስ በርስ የሚጋጩበት የመንግሥት ስርዓት ያለበት ነው።

በእነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል ከፖለቲካ አካሄዳቸው ባሻገር ቻይናውያን በጠቅላላው የሃይማኖት እውነታ ላይ ግራ መጋባታቸውን እና ጭፍን ጥላቻ እንዳላቸው መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ በሀይማኖታዊ ትውፊቶች ላይ እንቅፋትን የሚፈጥር እንጂ ሃይማኖታዊ አካሄድን ወይም አቋምን ከፖለቲካ ጉዳይ ጋር የሚያገናኝ አይደለም።

በመሆኑም የቻይና ህብረተሰብ እና ባህል፣ የካቶሊክ እምነት፣ በመሠረቱ የሰዎችን ተጨባች የሆነ ማሕበራዊ እድገትን፣ ሰላምን እና ፍትሕን እንዲሁም መንፈሳዊ እድገትንም ጭምር ሙሉ በሙሉ የተረዳ  መሆኑን  መገንዘብ ያስፈልጋል።

19 July 2018, 09:17