ፈልግ

19ኛ የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ጉባኤ 19ኛ የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ጉባኤ  

ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ፡ የአፍሪካ ልማት ሊገነባ የሚገባው በአፍሪካዊያን አቅም ላይ ተመስርቶ ነው

በእግዚአብሔር የተመሠረተ ሕያው ብዝሃነት፣ ሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (በአመሰያ) ሀገራት

ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ፡ የአፍሪካ ልማት ሊገነባ የሚገባው በአፍሪካዊያን አቅም ላይ ተመስርቶ ነው

በአሁኑ ወቅት “በእግዚአብሔር የተመሠረተ ሕያው ብዝሃነት፣ ሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (በአመሰያ) አገራት” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 6-16/2010 ዓ.ም በሀገራችን በኢትዮጲያ መዲና በአዲስ አበባ 19ኛ የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ጉባኤ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ይታወቃል።

በእዚህ 19ኛ የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባሄዎች ኅብረት ጉባኤ ላይ ከዘጠኙ የምስራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ኅብረት ጉባሄ ሀገራት የተውጣጡ በርካታ እንግዶች መታደማቸው የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አጋር ድርጅቶች እና ከተለያዩ ሀገራት የተጋበዙ የክብር እንግዶች የተሳተፉበት ጉባሄ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። በእዚህ ጉባሄ ላይ በተጋባዥነት የተገኙት በትውልድ ታንዛኒያዊ የሆኑና በአሁኑ ወቅት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና በስብከተ ወንጌል ስርጭት ላይ የሚሰራው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) አገራት ተዕድሶ እንደ ሚያስፈላጋቸው በአጽኖት መግለጻቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና በስብከተ ወንጌል ስርጭት ላይ የሚሰራው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ ባለፈው እሁድ ሐምሌ 08/2010 ዓ.ም ምሽት ላይ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጳጳሳት ድክመታቸውን አስወግደው ራሳቸውን በማደስ በመካከላቸው የላውን ኅበረት ማጠናከር እንደ ሚገባቸው ገልጸዋል።

“በምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጳጳሳት በአስተዳደራዊ መዋቅሮቻቸው ውስጥ ያለውን ድክመት በመገምገም በአሁኑ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቤተክርስቲያንን ለማደስ ከሚያደጉት ጥረት ጋር ሳይዘገዩ መተባበር እንዳለባቸው” ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የአሰተዳደር መዋቅሮቻችሁን በሚገባ በመገምገም እና በመከለስ ለሥራው ሂደት እንቅፋት የሆኑ መዋቅሮችን ለይቶ በማውጣት የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) ያቀዳቸውን የክንውን እቅዶች እውን ማድረግ የሚያስችለውን መንገድ መቀየስ እንደ ሚገባ ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ አሳስበዋል።

“ለአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ ፍቅር ከነበራቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ አንደኛው የሆኑት ብጹዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ እንደ ነበሩ” በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ ብጹዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ በሚቀጥለው አመት በጥቅምት ወር ላይ የቅድስና ማዕረግ እንደ ሚሰጣቸው አስታውሰው የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) አሁኑ ያለውን ይዘት እንዲኖረው ከፍተኛ ጥረት ያደጉት እርሳቸው እንደ ነበሩ ጨምረው ገለጸዋል።

ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ አፍሪካዊያን የራስቸውን እድገት በራሳቸው እንዲወስኑ ከፍተኛ አስተዋጾ አድርገው እንዳለፉ የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ የአፍሪካ ሀገራት በሀገሮቻቸው ውስጥ የሚካሄደውን የወንጌልዊ ተልዕኮ አገልግሎት በራሳቸው አቅም እና በራሳቸው የሰው ኃይል ማከናወን እንደ ሚገባቸው ይናገሩ እንደ ነበረ ጨምረው ገለጸዋል።

ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) ሀገረት መጻይ እድላቸው ከሌላ ሀገራት በሚመጡ የወንጌል ልዑካን ድጋፍ እና እርዳታ ላይ መመስረት እናደ ሌለበት፣ በአንጻሩ በራሳቸው የሰው ሐብት ልማት እና በራሳቸው አቅም ላይ የተገነባ መሆን እንዳለበት ያምኑ እንደ ነበረ በድጋሚ ያስታወሱት ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ መጻይ የአፍሪካ ሕልውና ሊገነባ የሚገባው በራሳችን በአፍሪካዊያን አቅም እና ጉልበት ላይ ተመስርቶ መሆን እናደ ሚገባው ጨምረው ገለጸዋል።

የምስራቅ አፍሪቃ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት (አመሰያ) ሀገረት ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የምድር ጨው እና የዓለም ብርሃን የመሆን ግዴታቸውን መወጣት እንደ ሚኖርባቸው ያሳሰቡት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና በስብከተ ወንጌል ስርጭት ላይ የሚሰራው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፕሮታዜ ሩጋምባዋ ይህንንም እውን ለማድረግ የትብብር መንፈስ ማጠናከር እና የታደሰ የልማት መንፈስ በመጎናጸፍ በተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙትን ሀብቶች እና የሰው ኃይል መጋራት እንደ ሚያስፈልግ ጨምረው ገለጸዋል።

16 July 2018, 13:59