ፈልግ

የመቁጠሪያዋ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት መቶኛው አመት  በግንቦት 05/2010 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ የመቁጠሪያዋ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት መቶኛው አመት በግንቦት 05/2010 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ  (ANSA)

የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት መቶኛው አመት በግንቦት 05/2010 ዓ.ም ተከበረ

የመቁጠሪያዋ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት መቶኛው አመት በግንቦት 05/2010 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

የመቁጠሪያዋ የፋጢማ ማሪያም የተገለጸችበት መቶኛው አመት

በግንቦት 05/2010 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

ይህ አሁን የምንገኝበት ወር የግንቦት ወር እንደ ሆነ ይታወቃል። ይህ የግንቦት ወር በወር ደረጃ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ “የማሪያም ወር” በመባል የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም የግንቦት ወር ውስጥ የክርስቶስ፣ የቤተክርስቲያን፣ የምዕመናን እናት ለሆነችው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለየት ባለ መልኩ ጸሎት የሚደርግበት፣ አማልጅነቷን የምንማጸንበት፣ በተለይም ደግሞ በውስጣችን፣ በቤተሰባችን፣ በማኅበረሳባችን፣ በሀገራችን እና በአጠቃላይ በዓለም ውስጥ የጥል እና የክርክር ግድግዳ ተደርምሶ በአንጻሩ የሰላም እና የብልጽግና መንፈስ ይወርድ ዘንድ በእርሷ አማካይነት ወደ ልጇ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመማጸኛ ጸሎት እንድታቀርብልን እርሷን በተለየ ሁኔታ በመቁጠሪያ ጸሎት አማልጅነቷን የምንማጸንበት ወር ነው የግንቦት ወር።

ይህ የያዝነው የግንቦት ወር ለእናታችን ለቅድስት ማሪያም ለየት ባለ ሁኔታ ጸሎት የምናቀርብበት ወር እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት በ1917 ዓ.ም የዛሬ አንድ መቶ ዓመት ገደማ ማለት ነው በፖርቹጋል ሀገር ፋጢማ በሚባል መንደር ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ሦስት እረኛ ሕጻናት የመቁጠሪያዋ እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የተገለጠችበት ቀን መቶኛ አመቱ በነገው እለት ማለትም በግንቦት 05/2010 ዓ.ም በመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል።

በወቅቱ እረኞች ለነበሩ ሦስት ሕፃናት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የዛሬ 100 ዓመት ገደማ 1917 ዓ.ም. በፖርቱጋል ሀገር በሚገኘው ፋጢማ በሚባለው አከባቢ ልዩ ስሙ ኮቫ ዳ ኢራ በተባለው ሥፍራ ለሦስት ታዳጊ የከብት ጠባቂ እረኞች ለነበሩ ሕፃናት ፍራሲሽኮ፣ ዣሺንታ ማርቶ እና ሉሲያ ለተባሉ ሦስት ታዳጊ ለነበሩ ልጆች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ የተገለጸችላቸው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒዮስ ሰባተኛ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/1946 ዓ.ም. የእዚህን ግልጸት ትክክለኛነት ከመረመሩ ቡኃላ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሥም የንግደት ሥፍራ ይሆን ዘንድ ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ፈቃድ መስጠታቸውና እስከ ዛሬም ድረስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመናን በሥፍራው ንግደት በማድረግ እንደ ሚገኙም ይታወቃል።

በወቅቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለእነዚህ 3 ሕፃናት በመገለጽ ከጥቂት ዓመታት ቡኃላ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት እንደ ሚነሣ በመተንበይ ሁሉም ክርስቲያኖች ሰላም ይሰፍን ዘንድ በእየለቱ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማሪያም የመቁጠሪያ ጸሎት እንዲያደርጉ ከእመቤታችን ትዕዛዝ መቀበላቸው ይታወቃል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለ3 እረኛ ለነበሩ ሕጻናት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/1917 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ተገልጻ እንደ ነበረ ቀደም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን የመቁጠሪያይቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በቀዳሚነት የተገለጸችው ለሐብታም፣ ለባለስልጣናት ወይም ደግሞ ተጽኖ ፈጣሪ ለሆኑ ሰዎች ሳይሆን ነገር ግን በወቅቱ በማሕበረሰቡ የተናቀ ስፍራ ለነበራቸው እና በእረኝነት ለሚተዳደሩ ሕጻናት ነበር።

ፋጢማ በሚባል ልዩ ስፍራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለእነዚህ 3 ሕጻናት እረኞች የተገለጸችበት ወቅት ዓለማችን በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እየታመሰች በምትገኝበት ወቅት እንደ ነበረ ይታወሳል።  በወቅቱ የነበረው የጥላቻ፣ የክህደት፣ የጠላትነት ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ይታይ ነበር። የቀድሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በበኔዴክቶስ 16ኛ እንደ የውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13/2010 ዓ.ም. ይህንን የመቁጠሪያዋ ቅድስት ድንግል ማሪያምን ቤተ መቅደስ በጎበኙበት ወቅት እንደ ገለጹት የመቁጠሪያዋ ማሪያም በግልጸቱ ወቅት ለ3 እረኞች ያስተላፈችው መልእክት  የወቅቱን አስቸጋሪ ሁኔታ ከመገንዘቧ የተነሳ ፍቅር እንዲኖር፣ ይቅርታ መደራረግ እንዲለመድ፣ ራስን ለሌሎች መስዋዕት ማድረግ እና ራሳችንን ለሌሎች ስጦታ አድርገን ማቅረብ እንደ ሚገባ ለሦስቱ እረኛ ለነበሩ ሕጻናት አሳስባ እንደ ነበረ መግለጻቸውን ይታወሳል።

እመቤታችን ይህንን የፍቅር፣ የሰላም፣ እና የመስዋዕትነት መልእክት ያስተላለፈችው ታላላቅ ለሚባሉ የማሕበረሰብ ክፍል አባላት ሳይሆን በጊዜው በማሕበረሰቡ በጣም መጨረሻ የተባለ ስፍራ ተሰጥቶዋቸው ለነበረው እረኞች እንደ ነበረም ይታወቃል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም እራሱዋ ከመልአኩ ገርኤል ብስራት ቡኃላ እግዚኣብሔር በእርሷ ባከናወነው ታላቅ ነገር ስለተደነቀች “እኔን ዝቅተኛይቱን አገልጋዩን ተመልክቱዋል እና ስሙ ለዘልዓለም ቅዱስ ነው” ብላ የምስጋና መዝሙር ለእግዚኣብሔር አቅርባ እንደ ነበር ሁሉ ይህም እግዚኣብሔር በዘመናት ሁሉ ውስጥ ዝቅተኛ የተባሉ ሰዎችን ከፍ እንደሚያደርጋቸው፣ የተናቁትን እንደ ሚጎበኛቸው ለዓለም መልእክት የሚያስተላለፊያ መንግድ ነው።።

ሁላችንም እንደ ምናውቀው ሁሉም መንፈሳዊ ጉዞ የሚደረግባቸው ቤተ መቅደሶች መንፈሳዊ ህክምና የመስጫ ስፍራዎች ናቸው። በተለይም ደግም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ስም የተሰየሙ መንፈሳዊ ጉዞ የሚደረግባቸው ስፍራዎች ለዚህ አባባል በማሳያነት መጠቀስ የሚችሉ መንፈሳዊ ህክምና መስጫ ተቋማት ናቸው፣ ምክንያቱ በእነዚህ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አሁንም ቢሆን መልአኩ ገብርኤል ማሪያምን ባበሰራት ወቅት “ለእግዚኣብሔር የሚሳነው ነገር የለም” በማለት  የተናገረው ድምጽ አሁንም በማሪያም ቤተ መቅደሶች ውስጥ በድጋሚ ስለምያስተጋባ ነው።

የማሪያም ቤተ መቅደስ የሰው ልጆች ሁሉ በመንፈስዊ ሕይወታቸው የሚያድጉበት ስፍራ ነው፣ ምክንያቱ ምዕመናንም እንደ ማሪያም “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” ብለው እንዲመልሱ ስለሚረዳቸው ነው። በዚህም ስፍራ “ለእግዚኣብሔር የሚሳነው ምንም ነገር የለም” የሰው ልጆች ሁሉ በእግዚኣብሔር በሚተማመኑበት ወቅቶች ሁሉ ምንም የማይሳነው እግዚኣብሔር ያቀዱትን ነገሮች ሁሉ ያጎጽፋቸዋል። በእግዚኣብሔር የተማመነ ሰው በመከራዎች ውስጥ ቢገባም እንኳን ምንም የማይሳነው እግዚኣብሔር በፍቅሩ ይጎበኘዋል ለእግዚኣብሔር ርኅራኄ፣ ምሕረት፣ ፍቅር ምስጋና ይግባውና እግዚኣብሔር ከማንኛውም ዓይነት መከራ ነጻ የማውጣት ብቃት እንዳለው የምንማርበት ስፍራ ነው የማሪያም ቤተመቅደስ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም እግዚኣብሔር ላቀረበላት ጥሪ “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” በማለት መልስ ስጥታ እንደ ነበረ ሁሉ የመቁጠሪያዋ የቅድስት ማሪያም ቤተ መቅደስ ይህንን የእግዚኣብሔር እቅድ እንድንረዳ ያግዘናል፣ “ለእግዚኣብሔር የሚሳነው ነገር የለም” የሚለው ሀረግ ምላሽ በምንሰጥበት ወቅቶች ሁሉ በሕይወታችን ውስጥ ታላላቅ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ።

13 May 2018, 11:34