Vatican News
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ነው፣ በዕየለቱ ልንመገበው ይገባል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ እርሳቸው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን አስተንትኖ ለመከታተል ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ የአገር ጎብኚዎች እና መንፈሳዊ ነጋዲያን በነሐሴ 02/2013 ዓ.ም ያደረጉት አስተንትኖ በእለቱ ከዮሐንስ ወንጌል 6፡41-51 ላይ ተወስዶ በተነበበውና “ነገር ግን ሰው እንዳይሞት ይበላው ዘንድ ከሰማይ የሚወርድ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው” በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ነው፣ በዕየለቱ ልንመገበው ይገባል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ አምስት ሺህ ሰዎችን የመገበበት ተአምር ሁኔታ ላይ መስበኩን ቀጥሏል። እናም እነዚያን ሰዎች ጥራት ያለው መንደርደሪያ ነጥብ እንዲወስዱ ይጋብዛቸዋል -በረጅሙ የበረሃ ጉዞ ውስጥ እግዚአብሔር አባቶቻቸውን በመና አማካይነት እንደ መገበ ካስታወሰ በኋላ አሁን ደግሞ የእንጀራውን ምልክት ራሱ ይተገበራል። “እኔ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” (ዮሐ 6፡48) በማለት በግልጽ ይናገራል።

የሕይወት እንጀራ ማለት ምን ማለት ነው? ለመኖር እንጀራ ያስፈልገናል። የተራቡ ሰዎች እንጀራን እንጂ እጅግ ውድ የሆነ ሌላ ዓይነት ምግብ አይመኙም። ሥራ የሌላቸው ሰዎች የሥራ ደሞዝ ሳይሆን የሚጠባበቁት ነገር ግን የእለት እንጀራቸውን ብቻ ነው የሚመኙት። ኢየሱስ እራሱን እንደ እንጀራ ማለትም ለዕለት ተዕለት ሕይወት አስፈላጊ መሆኑን ገልጧል። በሌሎች የእንጀራ ዓይነቶች ውስጥ የሚገኝ አንድ የእንጀራ ዓይነት ሳይሆን እርሱ የሕይወት እንጀራ ነው። በሌላ አነጋገር እኛ በእርሱ ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንኖራለን፣ ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነፍሳችንን ይመግባል ፣ እኛ ብቻችንን ልናሸንፈው የማንችለውን ያንን ክፉ ነገር ይቅር ብሎናል ፣ በእኛ ላይ ሁሉም ተስፋ ቢቆርጡብንም እኛን እንድንወደድ የሚያደርገን እርሱ ብቻ ነው። በችግሮች ውስጥ ለመውደድ እና ይቅር ለማለት ጥንካሬን ይሰጠናል ፣ እሱ የሚፈልገውን ሰላም ለልባችን ይሰጣል ፣ የእዚህ ምድር ሕይወት ሲያልቅ ለዘላለም ሕይወትን ይሰጣል።

የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። በዚህ በኢየሱስ ውብ ምስል ላይ እንኑር። እሱ ክርክር ፣ ማሳያ ማድረግ ይችል ነበር ፣ ግን - እኛ እናውቃለን - ኢየሱስ በምሳሌዎች እና በዚህ አገላለጽ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” ብሎ ተናገረ ፣ እሱ በእውነት መላውን ፍጥረቱን አጠቃልሏል። እናም ይህ የእርሱ አጠቃላይ ተልእኮ ነው። ይህ ጉዳይ በመጨረሻው እራት ፣ በመጨረሻው ላይ ሙሉ በሙሉ ይታያል። አብ ኢየሱስ ለሰዎች ምግብ እንዲሰጥ ብቻ ሳይሆን የላከው ነገር ግን ራሱን እንዲሰጥ ፣ ሕይወቱን ፣ ሥጋውን ፣ ልቡን እንዲሰብር እንደሚጠይቀው ኢየሱስ ያውቃል። እነዚህ የጌታ ቃላት በቅዱስ ቁርባን ስጦታ መደነቅን በእኛ ውስጥ ይቀሰቅሳሉ። በዚህ ዓለም ውስጥ ማንም ሰው ፣ የቱንም ያህል ቢወደንም ራሱን ግን ምግብ አድርጎ አዘጋጅቶ ሊያቀር አይችልም። እግዚአብሔር ለእኛ አደረገ ፣ ያደርጋልም። እስቲ ይህን መደነቅ እናድስ። የሕይወትን እንጀራ በማምለክ አድናቆታችንን እንግለጽለት፣ ምክንያቱም ስግደት ሕይወትን በሚያስደንቅ ሁኔታ ይሞላል።

በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ግን ሰዎች ከመደነቅ ይልቅ ሰዎች መሰናክል ውስጥ ገብተዋል። እነሱ ያስባሉ - “እኛ ይህንን ኢየሱስን እናውቃለን ፣ ቤተሰቦቹን እናውቃለን ፣ እንዴት ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ?” (ዮሐንስ 6፡41-42) ይለናል ተባባሉ። ምናልባት እኛ በዚህ ውዥንብር ውስጥ ተዘፍቀን ልንሆን እንችላለን፣ እኛ እዚህ ምድር ላይ ያሉትን ጉዳዮች ያለ ማንም የሰማይ አምላክ ጣልቃ ገብነት ማስተዳደር አመቺ ሊመስለን ይችል ይሆናል። ይልቁንም እግዚአብሔር ወደ ዓለም ለመምጣት ፈልጎ ራሱን ዝቅ አደረገ፣ ሰው ሆነ። እናም በሕይወታችን ውስጥ ሁሉም ነገር እሱን ይመለከተዋል። ስለ ፍቅር ፣ ሥራ ፣ ስለቀናችን ፣ ሁሉም ነገር ልንነግረው እንችላለን። ኢየሱስ ይህንን ቅርበት ከእኛ ጋር ይፈልጋል። እሱ የማይፈልገው ምንድን ነው? በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ ማተኮር፣ እርሱ የሕይወት እንጀራ መሆኑን መዘንጋት፣ የሕይወት እንጀራ የሆነውን እርሱን ችላ ማለት እና ወደ ጎን መተው፣ ወይም ችግር ሲገጥመን ብቻ ወደ እርሱ መሄድን ማቆም ይኖርብናል።

የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ አብረን ምግብ በመመገብ ላይ እናገኛለን። ምናልባት ምሽት ፣ ከቤተሰብ ጋር ፣ ከሥራ ወይም ከጥናት በኋላ ከቤተሰብ ጋር ምግብ እንቋደሳለን። እንጀራውን ከመቁረሳችን በፊት፣ የሕይወት እንጀራ የሆነው ኢየሱስ በመጋበዝ እኛ ልናደርገው ያልቻልነውን ነገር እንዲባርክልን መጠየቁ መልካም ይሆናል። ወደ ቤታችን እንጋብዘው “በቤት ውስጥ” ዘይቤ እንጸልይ። ኢየሱስ ከእኛ ጋር በማዕድ ይሆናልና በታላቅ ፍቅር እንመገባለን።

ቃል ሥጋ የሆነባት ድንግል ማርያም የሕይወት እንጀራ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር ያለን ወዳጅነት ዕለት ዕለት እንድናሳድግ ትርዳን።

 

08 August 2021, 12:22

የገብርኤል ብሥራት ጥንታዊ መሠርት የያዘና የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን በማስታወስ በቀን ሦስት ጊዜ ማለትም በንጋት (በአስራሁለት ሰዓት) በቀትር (በስድስት ሰዓት) እንዲሁም በማታ (በአስራሁለት ሰዓት) የሚደገም የጸሎት ዓይነት ሲሆን ጸሎቱ በሚደገምበት ሰዓት ቤተ ክርስቲያንም የመልኣከ እግዚኣብሔርን ደወል በዚሁ ሰዓት ትደውላለች። ይህ ጸሎት መልኣከ እግዚኣብሔር የሚለውን ስያሜ ያገኝው ከጸሎቱ ከመጀመሪያ ስንኝ የእግዚኣብሔር መልኣከ ማርያምን አበሠራት ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ጸሎቱ ስለ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ይናገራል። ጸሎቱ በሦስት የተከፈሉ አጫጭር ስንኞች ሲኖሩት በእነኚህ በሦስት አጫጭር ስንኞች መሓል ጸጋን የተሞላሽ የሚለው የማርያም ጸሎት ይደገማል። ይህ ጸሎት በሰንበትና በበዓላት ዕለት ልክ በእኩለ ቀን ላይ በዕለቱ ወንጌል ላይ ትንሽ አስተምሮና ገለፃ ከሰጡ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ ይህንን ጸሎት ይመራሉ። በመቀጠልም በአደባባዩ ላይ የተገኝው ከተለያየ ቦታ ለንግደት የመጣውን ሕዝብ ሰላምታ ይሰጣሉ።በየትኛውም ጊዜ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ በመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ፈንታ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚዘክረውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለው ጸሎት የሚደገም ሲሆን በመሓል በመሓሉ ጸጋን የተሞላሽ ማርያም ሆይ የሚለው ጸሎት ይታከልበታል።

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >