ኢንዶኔዢያ-አካባቢ ጥበቃ-ሥነ ምዳር ኢንዶኔዢያ-አካባቢ ጥበቃ-ሥነ ምዳር   (AFP or licensors)

ደረቃማ የአየር ጸባይ ድንበር ተሻጋሪ ጭጋጋማ አካባቢዎችን ሊጎዳ እንደሚችል ባለሙያዎች አስጠነቀቁ

ድንበር ተሻጋሪ ጭጋጋማ ወቅት ምንም እንኳን የሚጠበቅ ደረቃማ ወቅት ቢሆንም ከአሁን በኋላ የሚያሳስብ አለመሆኑን የኢንዶኔዢያው ሚኒስትር በስናጋፖር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ገለጹ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የኢንዶኔዢያ የባሕር ጉዳይ እና ኢንቨስትመንት አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ ሉሁት ቢንሳር ፓንጃይታን ሀገሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ጥሩ ዝግጅት ማድረጓን አረጋግጠዋል። ሚኒስትሩ ከዚህም ጋር አያይዘው ለደረቃማው ወቅት ለመዘጋጀት የኢንዶኔዢያ ባለስልጣናት የአየር ንብረት ማሻሻያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰው ሠራሽ ዝናብ ለመፍጠር ማሰባቸውን እና ይህም የአፈር ቃጠሎን ለመከላከል ያስችላል ብለዋል።

የኢንዶኔዢያ የባሕር ጉዳይ እና ኢንቨስትመንት አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ ሉሁት ቢንሳር በሥነ ምህዳር ሳምንት ጉባኤ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት፣ ፓንጃይታን የኢንዶኔዢያ ጭጋግ ችግር በ2016 ከደረሰው ከባድ ጭጋግ በኋላ እየቀነሰ መምጣቱን ጠቅሰው፥ ይህም በሱማትራ እና በካሊማንታን የሚገኙ የዘይት ዘንባባ እርሻዎችን በማቃጠል ከፍተኛ መጠን ያለውን ጥቃቅን ቁሶችን ካወደመ ወዲህ የአየር ጥራት እያሽቆለቆለ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት የደቡብ ምሥራቅ እስያ መንግሥታት ኅብረት (ASEAN) በሲንጋፖር ከግንቦት 30 - ሰኔ 1/2015 ዓ. ም. ድረስ ለመደራደር ከተያዘው ቀን በፊት በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። የኅብረቱ አባል አገራት ብሩኔ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ እና ታይላንድ ድንበር ተሻጋሪ ጭጋግ ብክለትን ለመከላከል ሁለተኛ ፍኖተ ካርታ ያዘጋጃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የድንበር ተሻጋሪ ጭጋግ የሚከሰተው ከሚቃጠሉ ደኖች ጭስ እና የአፈር ብናኞች በነፋስ ወደ ጎረቤት አገራት ሲወሰዱ፣ ይህም የአየር ጥራትን በማጓደል የመተንፈሻ አካላት በሽታን እና ሌሎች ችግሮችን እንደሚያስከትል ታውቋል።

'ሁሉም ሰው ተጨንቋል' ኢንዶኔዥያ በመካከለኛው እና ምሥራቃዊ ትሮፒካል ፓስፊክ የውሃ ሙቀት (El Niño) ምክንያት ለከባድ ደረቅ ወቅት እየተዘጋጀች መሆኗን እና ይህም የደን ቃጠሎ አደጋን እንደሚጨምር የብሔራዊ የአየር ንብረት ኤጀንሲ ኃላፊ ተናግረዋል። የአየር ንብረት ኤጀንሲ ሃላፊው አክለውም (El Niño) በሰኔ ወር የጀመረ ሲሆን በሁሉም ኢንዶኔዥያ ከሞላ ጎደል እስከ መስከረም ድረስ እየተባባሰ እንደሚሄድ ተናግረው፣ በሀገሪቱ ያለው ከፍተኛ የአየር ሙቀት እና ደረቅ ወቅቶች በደቡብ ምሥራቅ እስያ ደቡባዊ አካባቢዎች ለድንበር ተሻጋሪ ጭጋግ አስተዋጽኦ ስለሚያደርጉት የአፈር ቃጠሎ ስጋትን እንደሚፈጥር አስረድተዋል።

በግንቦት ወር የሲንጋፖር ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ “ደረቅ እና ሞቃታማ የአየር ጸባይ ለእርሻ መሬት እና ለእፅዋት ቃጠሎ መስፋፋት ምቹ ነው” ሲል ከማስጠንቀቁ በተጨማሪ ሲንጋፖርውያን በጭጋጋማ ወቅት  N95 ጭንብል እንዲኖራቸው ይገባል ሲል መክሯል። “እሳቱ ብዙውን ጊዜ ከሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ወቅቶች በጭጋግ ክብደት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን መረዳት አስፈላጊ ነው” ሲሉ በማሊያ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሄለና ቫርኪ ለቫቲካን ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።ተባባሪ ፕሮፌሰሯ ሄለና፥ "አሁን ጊዜው በጣም አሳሳቢ የሆነበት ምክንያት ወደ መካከለኛው እና ምሥራቃዊ ትሮፒካል ፓስፊክ የውሃ ሙቀት ወቅት እየመጣን በመሆኑ ነው” ስትል አክላለች።

በተጨማሪም ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሄለና ቫርኪ፥ የአፈር ላይ እሳት በተደጋጋሚ እየተባባሰ እንደሚሄድ እና ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የከፋ እሳት እንደሚያስከትል ጠቅሰዋል። ጭጋጋማው አየር እየተባባሰ ከመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተዳምሮ የበለጠ እንዲስፋፋ እና በደቡብ ምሥራቅ እስያ አቅራቢያ ያሉ ክልሎችን ሊጎዳ እንደሚችል አስረድተው፥ “ይህም ሊታሰብበት የሚገባ ነው” ብለዋል።

 

07 June 2023, 18:04