በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት እንግሊዝ ከቀሪው ዓለም እየተገለለች መሆኑ ተገለጸ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት እንግሊዝ ከቀሪው ዓለም እየተገለለች መሆኑ ተገለጸ 

በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት እንግሊዝ ከቀሪው ዓለም እየተገለለች መሆኑ ተገለጸ

ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ወይም ብዙ አገራት የበረራ ግኑኝነታቸውን ከታላቅዋ ብሪታኒያ እያቋረጡ መሆኑ ተገለጸ። ምክንያቱ ደግሞ በአዲስ መልክ እየሰፋ እና እየበረከተ በፈጣን ሁኔታ እየተሰራጨ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ መሆኑም ተገልጿል። የብርታኒያ ጠቅላይ ሚንስቴር ቦሪስ ጆንሰንም እንዲህ በማለት ስለ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ተናግረዋል.. . “አዲሱ ቫይረስ ከቀደመው በ70% የበለጠ የሚራባ ወይም ተዛማጅ ነው።እንዲሁም የመራባት አቅሙ ከፍተኛ ነው።በመሆኑም በደቡቡ የሀገራችን ከፍልም እየጨመረ ነው” በማለት ገልጸዋል።

ፈረንሳይ፣ጀርመን፣ኢጣሊያ፣አየርላንድ፣ቤልጂየም፣ሕንድ እና ካናዳም ከታላቅዋ ብሪታኒያ ጋር የትራንስፖረት ግኑኝነትን በማቋረጥ የቀደመውን ቦታ ይይዛሉ።ይሕ የሆነውም ጠቅላይ ሚንስትሩ አዲሱ ወረርሽኝ ለሀገራችን አደጋ አለው በማለት ከተናገሩ በኋላ ነበር።በባለፈው እሁድም፥የኮሮኖ ቫይረስ ስርጭትም ወደ 36 ሺህ አሻቅቧል።ይሕም ወረርሽኙ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ ትልቅ ቁጥር የተመዘገበበት ቀን ነው።

በዚህ ወቅትም በለንደን ከተማ የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስቴር ጆንሰን ለአስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል።የስብሰባው ዋና ዓላማም በታላቅዋ ሀገራቸው ላይ የታገደው የበረራ ሁኔታ ላይ ለመምከር ነው።በባለፈው እሁድ ምሽት ፈረንሳይ ለ 48 ሰዓታት ያህል ከታላቅዋ ብሪታኒያ ለሚመጡ መንገደኞች ድንበሯን እንደምትዘጋ አስታውቃለች።

ይሕ የእገዳ እንቅስቃሴም አስፈላጊ የሆኑ ግብይቶችን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን አስተጓጉሏል ተብሏል።እንዲሁም እገዳው በዚህ ከቀተለም የምግብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል በብሪታኒያ ያሉ የምግብ ገበያ ማዕከላት ገልጸዋል።

የጉዞ እገዳው ታላቅዋ ብሪታኒያ ከአውሮፓውያኑ ሕብረት ለመውጣት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት ወቅት ላይ መሆኑ ችግሩን አባብሶታል።ለንደን እና ብረስልስም በመንገድ ትራፊክ እንቅስቃሴ ተጨናንቋል።

ሳይንቲስቶችም እስካሁን አዲሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መባዛት ይችላል ተብሎ የተፈራው በእንግሊዝ የተገኘው ቫይረስ አስከፊነቱ ላይ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።ነገር ግን ወረርሽኙ የዓለም ዓቀፉን ማሕበረሰብ አንቅቷል።እንዲሁም ታላቅዋ ብሪታኒያንም በብዙ አግሏታል።

21 December 2020, 12:09