Russia to send S-300 missile system to Syria Russia to send S-300 missile system to Syria 

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኒውክለር ጦር መሣሪያን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

የኒውክለን ጦር መሳሪያዎችን ለማስቀረት የሚደረገዉን እንቅስቃሴ ኣብዛኛው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአንድ ሓሳብ ቢያጸድቀውም ይህ ሥምምነት በተገቢው ሰዓትና ጊዜ ባለማለቁ ዓላማዉን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የማድረግና የማስወገዱ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ አለ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ዛሬ ሃሙስ መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ. ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ የኒውክለር ጦር መሳሪያን ማስወገድ እንደሚያስፈልግና ይህም እንደ ኣንድ ትልቅ ግብ መወሰድ እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን ይህንንም አስመልክተው ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ተዊተር በሚባለው የግል ማኅበራዊ መገናኛ ድህረ ገጻቸው ላይ በዓለም ላይ የመበልፀግና የዕድገት ዕቅዶች እንጂ የጦር መሣሪያዎችን ለማዘመን ወይም ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት መቆም እንዳለበትና ለዚህም የሁላችን ትብብርና ጸሎት እንደሚያስፈልግ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኒውክለር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ በሚል የሚከበረውን ዓለም አቀፍ ቀን ምክንያት በማድረግ አስተላልፈዋል። በዚህም ኣጋጣሚ ሕዝቡ በጦር መሣሪያ ቅነሳና አደገኛነት ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲጨብጥ የሚያስከትለዉን ከፍተኛ ጠባሳ እንዲያወግዝና በማምከኑም ረገድ እንዲተባበር ዛሬ በዚህ ዙሪያ ውይይት መጀመሩን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ክላውዲያ ቫለንቲንን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

በዚሁም ወቅት መስከረም 26 ቀን 1983 ዓ.ም. እ.ኤ.አ ስታኒስላቭ ጴትሮቭ የሩሲያ ከፍተኛ የጦር መኮንን የኒውክለር ሲዲ ኮምፒተር ስርዓት ውስጥ በተፈጠር ችግር ዓለምን ከጥፋት መታደጉ የታወሰ ሲሆን በጊዜው ኮምፒተሩ ባሰማው የኣደጋ ጊዜ ጩኸት ተደርሶበት ችግሩ ባይቀረፍ ኖሮ የሚወነጨፉት የኒውክለር ሚሳይሎቹ በቀጥታ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና ኒውዮርክ ያቀኑ እንደነበር ተብራርቷል።

ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኒውክለር የጦር መሣሪያን ማስወገድ በሚል መሪ ቃል የሚታወሰው ወይም የሚከበረው በዓል እ.ኤ.አ. በ2013 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመሰረተ ሲሆን በየዓመቱ የሚከበረው ይህ በዓል በኒውክለርና የጦር መሣሪያ ምክንያት የሚከሰተውን የህዝብ ስጋት ግንዛቤን ለማጠናከርና ሙሉ በሙሉ እንዲወገዱ አስፈላጊነቱን እንዲያምንበት ለማድረግ ብሎም በዚህም ዙሪያ እንቅስቃሴ በማድረግ ዓላማዉን ለመደገፍ እንዲያስችል በተጨማሪም የኒውክሌር የጦር መሣሪያን ከዓለማችን ለማስወገድ በዓለም ዓቀፍ ኣንድ ወጥ እንቅስቃሴ ለመፍጠር ነው።

የኒውክለር እንቅስቃሴዎችን ከወዲሁ ማስቆሙ አስቸኳይ ግብ ነው፣

ይህ የዓለም አቀፍ የኒውክለርና የጦር መሣሪያ የማምከን ሥራ ዕቅድ የተባበሩት መንግስታት ኣስፈላጊነቱን በመገንዘብ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያና ትኩርት ሊሰጠው ከሚገባ አጣዳፊ ግብ አንዱ መሆኑ የተብራራ ሲሆን በመቀጠልም የዓለም አቀፍ የኑክሊየርና የጦር መሣሪያ ቅነሳ ምርምር መድረክ ፕሬዝዳንት ሞሪዚዮ ሲሞንቼሊ ለቫቲካን ዜናዎች እንዳብራሩት በኑክሊየር የጦር መሣሪያ ድርድር ውስጥ አሁንም ግልጽ ችግሮች አሉ መቋጫ ያልተበጀላቸው በርካታ ችግሮች ኣሉ ብለዋል።

ከእነዚህም ውስጥ የሰሜን ኮሪያ የኒውክለር ማምከን ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ኣሁንም ቁርጥ ያለ መልስ ያላገኘበት ሁኔታ አለ። በኢራን በኩልም ለተለያዩ መልካም ተገባሮች ለመጠቀም ሁሌ ለምርመራና ለቁጥጥር ክፍት በሆነ መልኩ የኒውክለር ኃይል ለማመንጨት ከኣሜሪካን ጋር ተስማምታ የነበረች ቢሆንም ኣሁን ግን መልሰው ከኣሜሪካን ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ እንደገቡ ያለው ሁኔታ እንደሚያመላክት ያሳያል ሲል ሞሪዚዮ ሲሞንቼሊ ኣብራርቷል።

የተባበሩት መንግስታት ስምምነቶች እና የኒውክለር የጦር መሣሪያዎችን እገዳ፣

ምንም እንኳን የተባበሩት መንግስታት ስምምነቶች የኑውክሌር የጦር መሣሪያዎችን አጠቃቀም ላይ እገዳ መጣል ዓለም አቀፋዊ ስጋት ቢያስከትልም የኒውክለር መከላከያ አስተምህሮ አሁንም በብዙ አገሮች ውስጥ የደህንነት ፖሊሲዎች አካል ነው። ይህንንም ሲሞንቼሊ እንዲህ በማለት ያብራራሉ ባለፈው ዓመት የኒውክለር የጦር መሣሪያ መጠቀምን ለማስቆም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወጣውን ስምምነት ለመተግበርና ለመፈረም የሚፈልጉ ሀገራት 2/3 ብቻ ናቸው። ብዙዎች አሁንም ፊርማውን አላፀደቁም ሌሎች ደግሞ ኣመርቂ ተነሳሽነት አላሳዩምም ብለዋል።

የኒውክለን ጦር መሳሪያዎችን ለማስቀረት የሚደረገዉን እንቅስቃሴ ኣብዛኛው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአንድ ሓሳብ ቢያጸድቀውም ይህ ሥምምነት በተገቢው ሰዓትና ጊዜ ባለማለቁ ዓላማዉን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የማድረግና የማስወገዱ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ እንዳለ ገልጸዋል።

የጣልያን ወታደራዊ ወጪዎች፣

ጣሊያን የጦር መሣሪያ በመግዛት በዓለማችን በ9ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች በማለት ያስረዳሉ በመቀጠልም ይላሉ ሲሞንቼሊ በተለይም ከኣውሮፓ ህብረት ኣገሮች እና ከሜዲትራኒኣን ዙሪያ ካሉት ሃገሮች ውጪ በተለይም ለመካከለኛው ምሥራቅ ሃግሮቸ ማሣሪያዎችን ትልካለች በዚህም ምክንያት የጦር መሣሪያዎችን ለማምረት የሚወጣው ወጪ እጅግ በጥም ከፍተኛ ነው በዚህም ረገድ ከላይ የተቀመቱትን 15 ሃገራት ጠቅሰው ይህ የኒውክለርና ጦር መሣሪያ ፖሊሲ ለምድራችን ሰላም ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት ያለው ልማትም ለመጎናጸፍ ምቹ ሁኔታ ፈታሪ ነው ብለዋል። የኒውክለር የጦር መሣሪያን ማስወገድ በእርግጥ ጣሊያንም በምትሳተፍበት እስከ 2030 ተግባራዊ በሚሆነው መርሃግብር ውስጥ በዘላቂነትና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማመቻቸት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለው ሓሳባቸውን ደምድመዋል።

27 September 2018, 17:03