በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ተወካዮች በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ተወካዮች 

በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሚገኙ ስደተኞች ተመልሰው ወደ ሊቢያ መወሰድ እንደሌለባቸው ተገለጸ።

በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሊቢያ መልሶ መወሰድ ተገቢ እንዳልሆነ ገለጹ። ምክንያቱን ሲገልጹ ሊቢያ ለስደተኞች ሕይወት አስተማማኝ አገር አይደለችም ብለዋል።

የዚህ ዘገባ አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሚገኙ ስደተኞች ተመልሰው ወደ ሊቢያ መወሰድ እንደሌለባቸው ተገለጸ።

በባሕር ላይ ለስደተኞች እርዳታን በማቅረብ የሚታወቁ ሁለት መንግሥታዊ ድርጅቶች እነርሱም ኤስ ኦ ኤስ ሜዲተራኒያንና ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በትናንትናው ዕለት በሮም ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሜዲተራኒያን ባሕር፣ በጉዞ ላይ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሊቢያ መልሶ መወሰድ ተገቢ እንዳልሆነ ገለጹ። ምክንያቱን ሲገልጹ ሊቢያ ለስደተኞች ሕይወት አስተማማኝ አገር አይደለችም ብለዋል። የባሕር ላይ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች መርከባቸው ለአንድ ወር ያህል ከፈረንሳይ ግዛት ከሆነችው ከማርሲሊያ ወደብ እንዳትንቀሳቀስ መከልከሏንም ገልጸዋል።

ሕይወትን ማዳን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ያሉት የዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች፣ አኳረስ የተሰኘው መርከባቸው ለአንድ ወር ያህል ከቆመበት ከማርሲሊያ ወደብ ተነስቶ ስደተኞች ወደሚገኙበት ስፍራ ዕርዳታ ሊሰጥ እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ በኢጣሊያ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ጽሕፈት ቤት ሮም ላይ ከሚገኘው መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ድርጅቱ በሰኔ ወር ብቻ በተለያዩ ቀናት ውስጥ ባደረገው ነፍስ አድን አገልግሎቱ በአንድ መርከብ ላይ የተጫኑ 630 ስደተኞች ከሞት አፋፍ ላይ እንዳዳነ ገልጿል። እነዚህን ስደተኞች የጫነው መርከብ የስፔን ግዛት የሆነውን ቫለንሲያን ወደብ ሊደርስ 1500 ኪሎ ሜትር ሲቀረው እንዲቆም መገደዱንና አኳረስ የዕርዳታ ሰጭ መርከብ ደርሶ አንድ ሳምንት በወሰደው ነፍስ የማዳን አገልግሎት መሰማራቱን የስደተኞችን ሕይወት ከሞት አደጋ ማትረፉን ገልጸዋል።

አኳረስ የነፍስ አድን መርከብ በቫለንሲያ ለአንድ ወር ያህል እንዲቆም በተገደደበት ወቅት እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ሌላ የዕርዳታ እሰጣጥ መንገድ ሲከተሉ እንደነበር ገልጸዋል። ማልታ ኢጣሊያ እና ሊቢያ የባሕር በሮቻቸውን ለስደተኞች እንዲዘጉ ከዓለም አቀፉ የባሕር ሃይል ማህበር ጥሪ ቢቀርብላቸውም ጥሪውን ባለማክበራቸው ወደባቸው አስታማማኝ አስተማማኝ አይደለም ተብሏል።

በዚህ ምክንያት አኳረስ ነፍስ አድን መርከብ ከሊቢያ የሚነሱት ስደተኞች አደጋ ቢያጋጥማቸው የእርዳታ እጁን ከመዘርጋት ወደ ኋላ አይልም ያሉት የኤስ ኦ ኤስ ሜዲተራኒያን እርዳታ ሰጭ ድርጅት ተወካይ አቶ አሌሳንድሮ ፖሮ፣ ይህ ደግሞ የጀነቫውን ስምምነት መጣስ ሳይሆን የስደተኞች ሕይወት አደጋ ላይ ሲወድቅ በዝምታ መመልከት አይሆነን ብለዋል።

በኢጣሊያ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ፕሬዚደንት የሆኑት ክላውዲያ ሎደሳኒ በገለጻቸው እንደተናገሩት በሊቢያ ለስደተኞች የሚሰጥ ምንም ዓይነት የሕይወት ዋስትናና ጥበቃ የለም ብለው፣ ስደተኞች እንደሚገረፉ በትክክል እናውቃለን ብለዋል።  

03 August 2018, 18:01