በሕክምና ድጋፍ ነፍስን ማጥፋት፣ ስቃይን ለማስወገድ መፍትሄ እንደማይሆን ተገለጸ በሕክምና ድጋፍ ነፍስን ማጥፋት፣ ስቃይን ለማስወገድ መፍትሄ እንደማይሆን ተገለጸ 

በሕክምና ድጋፍ ነፍስን ማጥፋት፣ ስቃይን ለማስወገድ መፍትሄ እንደማይሆን ተገለጸ

በቫቲካን የስነ ሕይወት ጥናት ጳጳሳዊ አካዳሚ፣ በጣሊያን ውስጥ በሕክምና ድጋፍ ነፍስን የማጥፋት ሕጋዊነት ምን ሊመስል እንደሚችል ባቀረበው አተያየቱ፣ በሕክምና ድጋፍ ነፍስን የማጥፋት ተግባር የሕሙማንን ስቃይ ለማስወገድ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ማርዮ” በሚል የሐሰት ስም የቀረበው ግለሰብ በመኪና አደጋ፣ ጉዳት ደርሶበት ላለፉት አሥራ አንድ ዓመታት ያህል በትከሻ መደንዘዝ ሲሰቃይ መቆየቱ ታውቋል። ግለሰቡ በሕክምና ድጋፍ አማካይነት ነፍሱ እንድታርፍ በሚኖርበት ማርኬ ግዛት ለሚገኝ የክልሉ የሕዝብ ጤና ባለስልጣን ለአንድ አመት ጥያቄን ሲያቀርብ ቆይቶ መልስ ያገኘ መሆኑ ታውቋል።

ከባድ ስቃይን የሚያስከትል ሥር የሰደደ ህመምን ጨምሮ አንዳንድ ሁኔታዎች በሕክምና እርዳታ ነፍስን ማጥፋት እንዲቻል የጣሊያን ፍርድ ቤት ውሳኔ ካስተላለፈበት እ. አ. አ. ከ2019 ዓ. ም. ወዲህ መልስ ሲያገኝ ማርዮ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ ሰው መሆኑ ታውቋል። ለፍርድ ቤቱ የቀረበው የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ ከተደረገ በኋላ፣ የክልሉ ጤና ባለስልጣን በሰጠው ፍቃድ እንዳስታወቀው፣ ማሪዮ በነፃነት ፈቅዶ የራሱን ውሳኔ ካደረገ  በሕክምና ድጋፍ የሚሰጥ የነፍስ ማሳረፍ አገልግሎት ማግኘት የሚችል መሆኑን ገልጿል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ፣ በቫቲካን የስነ ሕይወት ጥናት ጳጳሳዊ አካዳሚ ማክሰኞ ኅዳር 14/2014 ዓ. ም. ይፋ ባደረገው መግለጫው፣ "የራስን ነፍስ በግል ምርጫ ለማሳረፍ የሚደረግ የመጨረሻ ውሳኔን የሚመለከት ርዕሠ ጉዳይ ውስብስብ እና አከራካሪ ነው" ብሎ፣ “የክፍለ አገሩ የሥነ-ምግባር ኮሚቴ የሰጠውን አስተያየት ተከትሎ ሕመምተኛው ራሱን በፍላጎት ማጥፋት እንደሚችል የተሰማው ዜና አንዳንድ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ የሚያስገባ ነው” ብሏል። ጳጳሳዊ አካዳሚው አክሎም፣ የታካሚውን የሕክምና ሁኔታ የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ አለመኖሩ "በአንዳንድ አጠቃላይ ምልከታዎች" ላይ ውስንነት መኖሩን ያመለክታል ብሏል።

25 November 2021, 16:45