ጋብቻ የእግዚአብሔር ፍቅር ተምሳሌት ነው!

ከመጋቢት 10/2013 እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም ድረስ ለሚዘልቀው በላቲን ቋንቋ “Amoris Laetitia” በአማርኛው የፍቅር ሐሴት በሚል አርዕስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያፋ ያደረጉት ሐዋርያው ቃለ ምዕዳን ለመዘከር እና ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ ያለው ሚናን ለማጉላት ታስቦ የቤተሰብ ዓመት እንዲከበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መወሰኑ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት ይዘግጅቶቻችን ተከታታዮች በማስከተል አሞሪስ ላኤቲሲአ (Amoris Laetitia) የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምክር ወይ ቃለ ምዕዳን ላይ ከተጠቀሱት ሐሳቦች ከምዕራፍ አንድ እስከ 3 ያለውን በአጭሩ እንደ ሚከተለው እናስቃኛችኋለን፣ ተከታተሉን።

 

የፍቅር ሐሴት

አሞሪስ ላኤቲሲአ (Amoris Laetitia)

በመጋቢት 30/2008 ዓ.ም ለንባብ የበቃው እና በቅዱስ አባታች ፍራንቸስኮ የተፃፈ  ሐዋርያዊ ምክረ ሐሳብ

የአሞሪስ ላኤቲሲአ ሐዋርያዊ ምክረ ሐሳብ መዋቅር እና ትርጉም በአጭሩ በቫቲካን ሬድዮ እንደ ተዘጋጀው

ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ

“የፍቅር ሐሴት” ወይም በላቲን “አሞሪስ ላኤቲሲአ” የተሰኘው እና ትኩረቱን ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ ስላለው ሚና ላይ በማድረግ የምያወሳው ድሕረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምክረ ሐሳብ እ.አ.አ በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም በቅዱስ ዮሴፍ የንግሥ በዓል ዕለት በቅዱስ አባታችን ተፈርሞ ለንባብ እንዲበቃ መታዘዙ በአጋጣሚ የተፈጠር ጉዳይ አልነበረም።

ይህ ሐዋርያዊ ምክረ ሐሳብ ወይም ቃለ ምዕዳን ከእዚህ በፊት በቅዱስ አባታችን ተነሳሽነት፣ በቤተስብ ጉዳይ ላይ ትኩረትን በማድረግ እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም በተዘጋጀው ልዩ የጳጳሳት ሲኖዶስ እና በመቀጠልም እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ከ190 በላይ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ጳጳሳት የተሳተፉበት መደበኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ ድምር ውጤት ነው።

አሞሪስ ላኤቲሲአ (የፍቅር ሐሴት) የተሰኘው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት ሲኖዶሶች ባሻገር ከእዚህ በፊት የነበሩት የቤተክርስቲያን ሰነዶችን፣ ከቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ በፊት የነበሩ ጳጳሳት አስተምሮዎችን እንዲሁም በቤተሰብ ዙሪያ እርሳቸው እራሳቸው የሰጡትን አስተምሮ አጠቃሎ የያዘ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።

እንደ ተጨማሪ ግብሃት በዓለም ዙሪያ ለምሳሌም በኬንያ፣ በአውስትራሊያ፣ በአርጄንቲና . . . ወዘተ ተካሂደው ከነበሩ ጳጳሳዊ ጉባሄዎች የማጠናከሪያ ሐሳብ የወሰደ ሲሆን በተጨማሪም የጥቁሮች መብት ተሟጋች የነበረውና “I have adream” (ሕልም አለኝ) በሚለው አባባሉ የሚታወቀው አሜርካዊው የሰብሃዊ  መብት ተሟጋች የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ እና  የማሕበርሰብ ስነ-ልቦና አጥኝ የነበረው ጀርመናዊው ኤንሪክ ፍሮም ጉልህ ሊባል በሚችል መልኩ የተጠቀሱበት እና “ባቤትስ ፊስት” (Babette’s Feast) የተሰኘው እና በ1987 ለመጀመሪያ ጊዜ በዴንማርክ ለእይታ የቀረበ ድራማ ላይ በተጠቀሰው እና ትኩረቱን በ19ኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ በዴንማርክ ፓስተር ከነበረው አባታቸው ጋር ጭምት የሆነ ሕይወት ይኖሩ ስለ ነበር ሁለት እህተማማቾች የምተርከው ዋና ጽንሰ ሐሳብም በሐውሪያዊው ቃለ ምዕዳን ውስጥ ተጠቅሱኋል።

መግቢያ (ከአንቀጽ 1-7)

ከምዕራፍ አንድ እስከ ሰባት በሐዋርያዊው ቃለ ምዕዳን ውስጥ የተጠቀሰው በመቀጠል በዝርዝር ለሚቀርቡት ሐሳቦች እንደ መንደርደሪያ የሚሆኑ ሐሳቦችን የያዘ ነው። ይህ 325 አንቀጾች ያሉት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን በዘጠኝ ምዕራፎች የተከፈለ ነው። የመጀምሪያዎቹ ሰባት የመግቢያ አንቀጾች የሐዋርያዊውን ቃለ ምዕዳን አርዕስት ውስብስብነት በግልጽ በማስቀመጥ በቀጣይነትም አስቸኳይ እና ጥልቅ የሆነ ጥናት እንዲደርግበት የምያሳስብ ነው።

በተጨማሪም ቀደም ብለው በተካሄዱት ሁለት ሲኖዶሶች ላይ ቅዱሳን አባቶች መልክ እንዲይዝ ያሳሰቡት የነፍሳት ዕንቁ “multifaceted gem” (አ.ላ. ቁ. 4)  የተሰኘው እና ወድ የሆኑ የሰው ልጅች የማንነት እሴቶች ተጠብቀው እንዲቀጥሉ የሚጋብዝ ሐሳቦችም ተጠቅሶበታል። ነገር ግን ቅዱስነታቸው ጥንቃቄ በተሞላው እና ውዝግብ በማይፈጥር መልኩ “ቀኖናዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ፣ የስነ- ምግባር ጉድለቶች ወይም ሐዋሪያዊ ተግዳሮቶች፣ ቤተክርስቲያን በተሰጣት ስልጣን በምትሰጠው ኦፊሴልያዊ  አስተምሮ ወይም (magisterium) ብቻ መፈታት የለባቸውም” የሚል ሐሳብ አንጸባርቋል።

 በእርግጥም “ለአንዳንድ ለሚነሱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች የእያንዳንዱ አገር ወይም ክልል. . . ወዘተ፣ ባህሉን እና ወጉን በጠበቀ መልኩ እና የማሕበረሰቡን ጥቅም ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ አንገብጋቢ ለሆኑ ችግሮቻቸው መፍትሄን መስጠት ይችላሉ። ‘ባህሎች አንዱ ከአንዱ የተለዩ በመሆናቸው አጠቃላይ ወይም ዓለማቀፋዊ የሆኑ መርዕዎች እንዲከበሩ እና ተጋባራዊ እንዲደረጉ ከተፈለገ እንደየባህሉ ሁኔታ መወሰድ ይኖርባቸዋል’” (አ.ላ. ቁ. 4)። “እነዚህ ዓለማቀፋዊ የሆኑ መርዕዎችን ‘በባህል ውስጥ ማስረጸ’ የሚለው መርዕ ሐሳብ የሚተገበረው የችግሮችን መንስሄ በማጥናት፣ እንዲሁም መፍትሄን በመንደፍ፣ በተጨማሪም የቤተክርስቲያን ቀኖናን እና ቤተክርስቲያን በተሰጣት መንፈሳዊ ስልጣን የምታስተምራቸውን አስተምሮዎችን ተመርኩዞ ለአንገብጋቢ ችግሮች ተገቢ በሆነ መልኩ ምልስ ሊሰጥ ይገባል። ነገር ግን በእዚህ ዓይነቱ ዘዴ የተፈታ ማንኛውም ዓይነት አንገብጋቢ ችግር ይዘቱ ‘ዓለማቀፋዊ’ ሊሆን አይችልም”።

እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም በተካሄደው ሲኖድ ላይ ቅዱስነታቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት “ለአንድ ጳጳስ ጤናማ ጉዳይ ሆኖ የሚታየው ጉዳይ፣ በሌላ አህጉር ወይም ሀገር ለሚኖር ጳጳስ ግን እንደእንግዳ እና አሳፋሪ ነገር ተደርጎ ሊቆጠር ይችል። በአንዱ ጳጳስ ማሕበርሰብ ውስጥ እንደየሰው ልጆች የመብት ጥሰት ተደርጎ የሚቆጠር ተግባር በሌላ አህጉር ወይም ሀገር ውስጥ ለሚኖር ጳጳስ ግን እንደ ግልጽ እና የማይጣሱ ትክክለኛ የሰው ልጆች መብትን የምያስከብር ደንብ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።  በአንዱ ማሕበረሰብ ውስጥ እንደ ሕሊና ነፃነት የሚቆጠሩ ተግባሮች በሌላው ማሕበርሰብ ውስጥ ግን እንደ ግራ መጋባት ይቆጠራሉ” ማለታቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው “በመገናኛ ብዙሃን የሚደርጉ ክርክሮች፣ አንድ አንድ አሳታሚዎች አልፎ ተርፎም በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መካከል ጉዳዩን በጥልቀት ሳይመረምሩ እና አንድ አቋም ላይ ሳይደርሱ ተመጣጣኝ ያልሆነ አጠቃላይ ለውጥ እንዲመጣ መፈለጋቸው እና ሁሉንም ዓይነት ጉዳዮች አጠቃላይ ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ ለመፍታት ዝንባሌ ማሳየታቸው እንዲሁም መለኮታዊ የሆኑ አስተምሮዎችን ከግምት በማስገባት ወደ አልተፈለገ ድምዳሜ ማምራት” (አ.ላ. ቁ. 2) ቅዱስነታቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት የለውጥ ጥያቄዎችን እና ውስብስብ የሆኑ ሕግጋትን አጠቅላይ ተግባራት ጎን ለጎን አስቀምጠን በግልጽ ከመፈርጅ መቆጠብ  እንደ ሚገባ ገልጸዏል።

ምዕራፍ አንድ “በብርሃነ ቃሉ” (ከአንቀጽ  8-30)

የመግብያ ጽሁፋቸውን ተከትሎ ቅዱስነታቸው ሐሳባቸውን በመጻሐፍ ቅዱስ ላይ መሰረት በማድረግ የመጀመሪያ የቃለ ምዕዳናቸውን ምዕራፍ የጀመሩት በመዝሙር 128 ላይ አስተንትኖ በማድረግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “በቤተሰብ፣ በልደት፣ በፍቅር ታሪኮች እና የቤተሰብ ቀውስ የተሞላ ነው" (አ.ላ. ቁ. 8)። “ይህ እውነታ እንድናጤን የሚገፋፋን የቤተሰብ ጉዳይ ውስብስብ አለመሆኑን እና ነገር ግን ዕለታዊ፣ ተጨባጭ እና ነባራዊ ተግባር መሆኑን ሲሆን (አ.ላ. 16) እንዲሁም  በርኅራኄ የሚተገበር (አ.ላ. 28) ነገር ግን ከጥንት ጀምሮ እንደሚታየው፣ በፍቅር ላይ የተመሰረት ግንኙነት በሚለወጥበት ጊዜ እና አንዱ ሌላውን በሚጫንበት ወቅት  የሚጋረጥበት ሕይወት ነው (አ.ላ. ቁ. 19)።

ስለዚህ የእግዚኣብሔር ቃል ‘በተወሳሰቡ ሐሳቦች የተሞላ ሳይሆን ነገር ግን በችግር ወይም በመከራ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦችን የምያግዝ  እና የመጽናናት ሁሉ ምንጭ ነው፣ ምክንያቱም ወደ የሕይወታቸው ግብ ስለ ሚመራቸው” (አ.ላ. 22) በማለት በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ በጣም ብዙ ሊባሉ ስለሚችሉ መልካም ነገሮች እና ተግዳሮቶች በማውሳት ለችግሮቻቸው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመርኩዘው መፍትሄን እንድያበጁ ያሳሰቡበት ምዕራፍ ነው።

ምዕራፍ ሁለት “የቤተሰብ ተመኩሮዎች እና ተግዳሮቶች” (ከአንቀጽ 31-57)

በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ቅዱስነታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ላይ በመመርኮዝ አሁን ባለንበት ዘመን ያለውን የቤተሰብ ሁኔታ ያብራራሉ። “ነባራዊ እውነታ ላይ በመመርኮዝ”(አ.ላ. 6) የቤተሰብ ተሞክሮን የገመገመ እና በተለይም ከዚህ በፊት ተካሄደው የነበሩ ሁለቱ ሲኖዶሶች ጠቅላላ ሪፖርት ላይ መሰረቱን ያደረገ ነው።

ከሰዎች ፍልሰት አንስቶ እስከ በጾታዎች መካከል ስላለው ልዩነት የምያወሳው “ስነ-ጾታዊ ርዮተ ዓለም” (አ.ላ 56)፣ እንዲሁም አዲስ ከሆነ ባሕል እስከ ውልጃን የሚከለክል አስተሳሰብ (ማስወረድ፣ abortion) እንዲሁም ከእርግዝና ጋር በተያያዘ መልኩ አሁን እየታየ ያለው የባዮቴክኖሎጂ ተጽዕኖ፣ ከመኖሪያ ቤት እጥረት እስከ በዝሙት ሥራ ላይ እስከ ተሰማሩ ሰዎች የሚያወሳ፣ ለአካለ መጠን ያልደርሱ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለውን አካላዊ እና ሞራላዊ ጥቃቶችን የሚዳስስ፣ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎች ትኩረት መንፈጋቸውን የሚገልጽ፣ መእድሜ የገፉ ሰዎችን ክብር መነፍጋቸውን የምያብራራ፣ ቤተሰብን ሕጋዊ በሆነ መልኩ ማለያየት እና በሴቶች ላይ በሚደርሰውን ጥቃት ምክንያት ቤተሰብ ውስጥ ብዙ ተግዳሮቶች እየደረሰ መሆኑን ይተነትናል። ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ትኩረታቸውን ያደረጉት ተጨባጭ በሆኑ እውነታዎች ላይ ነው። 

ለተቀባይነት እና ለነባርዊ እውነታ ትርጓሜ በሚሰጠው “ንድፈ ሐሳብ” እና አጣራጣሪ በሆነው “ርዕዮተ ዓለም” መካከል ያለውን ልዩነት ጉልህ በሆነ መልኩ መለየት የሚቻለው በሕይወት ውስጥ የሚታዩትን ተጨባጭ እና እውነተኛውን የሕይወት ተሞክሮዎች እንዲሁም ዕለት ተዕለ በሕይወት ውስጥ የሚታዩትን ፈታንዎች መገንዘብ ስቻል ብቻ ነው።

“Familiaris consortio” ከተሰኘው እና በቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ከተጻፈው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በመጥቀስ “የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ እና ፍላጎት ‘በታሪክ ክስተቶች ውስጥ ስለ ምያስተጋባ’ ተጨባጭ የሆኑ እውነታዎች ላይ ማትኮር አለብን’ ይህም ደግሞ ‘ቤተ ክርስቲያንን ይበልጥ ጥልቅ ወደ ሆነ የማይነጥፍ የጋብቻ ምሥጢርን እና ስለ ቤተሰብ ግንዛቤ እንዲኖራት ይረዳል’” (አ.ላ. 31) የሚለው ሀርግ በሰፋት ይተነተንበታል። በሌላ በኩል እውነታን መረዳት ካልቻልን አሁን ያለውን ፍላጎት ወይም የመንፍስ ቅዱስን እንቅስቃሴ መረዳት አንችልም ማለት ነው። ቅዱስነታቸው ስያብራሩም “አንድ ሰው እራሱን ለሌላ አሳልፎ እንዳይሰጥ በአሁኑ ጊዜ እየተሰፋፋ ያለው እራስ ወዳድነት (Egoism) ሁኔታዎችን አስቸጋሪ እንደ ምያደርግ” (አ.ላ. 33) አስገንዝቧል። አስገራሚው ነገር አሉ ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው “ብቸኝነትን መፍራት፣ መረጋጋትን መፈለግ እና ታማኝነትን ለማግኘት ፍላጎትን ማሳየት ጋር አብሮ ጎን ለጎን የሚጓዝው እነዚህ ነግሮች አንድ ሰው የግል ግቦችን ለማሳካት የምያደርገውን ጥረት የምያሰናክል ወጥመድ ተደርጎ መወሰዱ ነው” (አ.ላ. 34) በማለት የራስ ወዳድነት አስተሳሰብ የፈጠርውን ውስብስብነት ገልጸዋል።

እውነታን የተከተለ ትህትና እና “ከተጨባጭ እውነታ የራቀ ጋብቻን የተመልከተ በጣም ረቂቅ፣ ሰው ሠራሽ ሥነ-መለኮታዊ ሐሳብ፣  እውነተኛ እና በቤተሰብ ውስጥ ተጋባርዊ ሊሆኑ የማይችሉ ሐሳቦችን” (አ.ላ. 36) እንድናስወግድ ይረዳናል። ምናባዊነት በእራሱ ትዳርን በቅጡ እንድንረዳ አያደርገንም። ያም ማለት “የሰው ልጅ ግላዊ እድገት ተለዋዋጭ መንገድን የተከተለ” መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ይህም  “የእግዚአብሔርን ጸጋ በግልጽ እንዲቀበሉ ሳናበረታታ ዶክትሪንን፣ የስነ-ሕይወት እና የስነ-ምግባር ጉዳዮችን” (አ.ላ. 37) ቤተሰብን ይደግፋሉ ብሎ ማሰብ የማይመስል እና ከእውነት እና ከተጨባጭ ሁኔታ የራቀ ሐሳብ ነው።

የጋብቻን እና የቤተሰብ ተሞክሮን ያላማከለ “ትችት” እና በቂ ያልሆነ አቀራረብ እንዲኖር የምያደረግ ተግባር ተወግዶ በአንጻሩም ቅዱስነታቸው በቃል ምዕዳናቸው እንዳሳሰቡት ምዕመናን ሕሊናቸውን እንዲጠቀሙ እድል መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አስረግጠው አሳስበው “የተጠራነው ሕሊናን ለማነጽ እንጂ ሕሊናን ለመቀየር አይደለም” (አ.ላ. 37) በማለት ትችትን እና ችኩል የሆነ ውሳኔን ከመውሰድ መታቀብ እንዳለብን አሳስቧል።  ኢየሱስ የሚጠይቀን ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችን እንድንከተል ነው እንጂ “ልክ ስታመነዝር እንደተያዘችው ሳምራዊት ሴት ያሉ ግለሰቦችን መቼም ቢሆን ምሕረቱን እና አለኝታነቱን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ነፍጎ አያውቅም” (አ.ላ. 38) በማለት ፍርደ ገምድል መሆን እንደ ሌለብን እና ሁኔታዎችን አንድ በአንድ መመርመር እንደ ሚገባን አሳስቧል።

ምዕራፍ ሦስት “የቤተሰብ ጥሪ ኢየሱስን መፈለግ ነው” (ከአንቀጽ 58-88)

ሥስተኛው ምዕራፍ ትኩረቱን ያደረገው ጋብቻን እና የቤተሰብ ጉዳይን የተመለከቱ የቤተክርስቲያን አስተምሮዎች ላይ ነው። ይህ 30 አንቀጾች ያሉት ምዕራፍ በጣም አስፈላጊ እና ወቅታዊ ሊባል የምችል ምዕራፍ ነው። ምክንያቱም የቤተሰብ ጥሪ በቅዱስ ወንጌል ላይ ተመስርቶ እና ቤተክርስቲያን በጊዜ ሂደት ያረጋገጠችው እና ምን መሆን እንዳለበት የምናገር እና የምያሳይ በመሆኑ ነው።

ከሁሉም በላይ ትዳር እስከ ሕይወት ፍጻሜ የሚጸና መሆኑን የተሰመረበት ሲሆን፣ የትዳር ሚስጢራዊ የተፈጥሮ ገጽታ እና ሕይወትን ቀጣይ እንዲሆን የማድረግ ተግባሩ እንዲሁም ለሕጻናት ስለሚሰጠው መሰራታዊ ትምሕርት አስፈላጊነትን ይገልጻል። “Gaudium et Spes” (ደስታ እና ተስፋ) ከተሰኘው የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ፣ “Humanae Vitae” (የሰው ሕይወት)  ከተሰኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አወዲ መልዕክት እና “Familiaris Consortio”  (ቤተሰብ አሁን ባለንበት ዘመን) ከተሰኘው የቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን በሰፊው የተጠቀሱበት ምዕራፍ ነው።

ይህ ምዕራፍ “ፍፁም ያልሆኑ ሁኔታዎችን” በሰፊው የሚመለከት እና የሚዳስስ ምዕራፍ ጭምር ነው። “በሌሎች ባሕሎች ውስጥ ‘ፍሬማ የሆኑ ዘሮች’” መኖራቸውን የተገለጸ ሲሆን ይህም ደግሞ ከጋብቻ እና ከቤተስብ ነባራዊ እውነታ ጋር በማጣመር መገለጹ በእዚህ ምዕራፍ ውስጥ መመልከት ይቻላል።

“ተፈጥሮአዊ እና እውነተኛ ከሆነው ጋብቻ በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ ድንግዝግዝ ሆኖ ቢታይም አዎንታዊ የሆኑ ግንቢ ነገሮች በሐይማኖታዊ ወግ የተፈጸመ ጋብቻ ውስጥ ይገኛሉ” (አ.ላ. 77)። “በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦች” በማለት ቅዱስነታቸው እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም በተካሄደው ሲኖድስ የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደገለጹት እና በትዳር ሕይወት ውስጥ በገጠማቸው ችግር የምሰቃዩ ሰዎችን ሁኔታን የሚዘረዝር ሐሳብ በእዚህ ምዕራፍ በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን “’የቤተክርስቲያን አባቶች ማወቅ ያለባቸው ነገር ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ስለእውነት ሲባል በጥንቃቄ ሁኔታዎችን የመመርመር ግዴታ እንዳለባቸው የምያስገድዳቸውን አጠቃላይ መርዕ ማስታወስ ምንጊዜም አስፈላጊ ነው” (Familiaris Consortio. 84) በማለት በውሳኔ አሰጣጥ ወቅት ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበዏል። “ኋላፊነትን መሰረት ያደርጉ ውሳኔዎች በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ተመሳሳይነት ባለው መልኩ ሊተገበር እንደ ማይገባ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች የሚደረጉ ውሳኔዎችን የመገደብ አጋጣሚ ልያስከስቱ ይችላሉ። ስለ እዚህ የቤተክርስቲያንን አስተምሮ በግልጽ መተግበር አስፈላጊ ቢሆንም መጋቢው ወይም እረኛው የነባሪዊ እውነታውን ውስብስብነት ሳያጤን፣ በትኩረት ሳይመልከት፣ ሰዎች ተመኩሮ እና  በችግራቸው ምክንያት እያሳለፉ ያለውን ስቃይ ሳያገናዝብ ውሳኔ ከመውሰን ልቆጠቡ የገባቸዏል” (አ.ላ.79)በማለት አሳስበዏል።

01 August 2021, 13:10