የክርስትና እና የአይሁድ ዕምነት መሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲከፋፈል ጥሪ አቀረቡ የክርስትና እና የአይሁድ ዕምነት መሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲከፋፈል ጥሪ አቀረቡ 

የክርስትና እና የአይሁድ ዕምነት መሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲከፋፈል ጥሪ አቀረቡ!

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት እና የዓለም አይሁድ ምክር ቤት የኮቪድ-19 ክትባት ለሁሉም አገራት በፍትሐዊነት እንዲከፋፈል ለሐይማኖት መሪዎች የተቻላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።ይሕንን ፍትሐዊ ክፍፍልም ለማረጋገጥ እንዲያግዙም ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የቫቲካን ዜና

የሐይማኖት መሪዎች እና ተቋማት በማሕበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት አላቸው።ዓላማቸው እና መዋቅሮቻቸውም በመልካም እሴቶች የተዋቀረ ነው።በመሆኑም የኮቪድ-19 ክትባት ፍትሐዊ ክፍፍልን በተመለከተ ድርሻቸው እና ሐላፊነታቸው ትልቅ ነው። ስለሆነም የዚህን ክትባት ስርጭትን አስመልክቶ በሚደረጉ የመዋቅር ውይይቶች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር ይችላሉ በማለት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት እና የዓለም አይሁድ ኮንግረስ አሳስቧል።እንዲሁም እ᎐አ᎐አ᎐ ታህሳስ 22 በወጣው ጥናትም የዓለም ሐይማኖት መሪዎች ተገኝተው እንዲያሰላስሉ እና በሐሳብም እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።በተጨማሪም ይሕ ጥናት እንደሚያመለክተው ክትባቱ ለበሽታው ወይም ለወረርሽኙ ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥ አይደለም።የክትባቱ ፍላጎት ከእቅርቦት በላይ በመሆኑ የሐይማኖት መሪዎች እና ተቋማትም ፍትሐዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ተቆርቋሪነታቸውን ማሳየት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

አብሮነት እንጂ የክትባት ብሔርተኝነት አያስፈልግም

እንደ ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት አመለካከትም ቁልፉ ጉዳይ የተገኘው ክትባት ፍትሐዊ በሆነ ሁኔታ መከፋፈል ይኖርባታል የሚል ነው።በመሆኑም ደሐ አገራትም በዚሕ ሕይወት አድን ክትባት እንዲካተቱ ይሆናልና። 

ክትባቱን ለሁሉም ለማዳረስ በሚል መርሕ የተመሠረተው ዓለም አቀፍ ሕብረት (COVAX)-በGAVI (ዓለም አቀፍ የክትባት እና ኢሙናይዜሽን ሕብረት)፣በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) እና በወረርሽኝ ዝግጁነት ወይም መከላከል ጥምረት (CEPI) የተቋቋመ ነው።የወረርሽኙ አስከፊነትን ለመከላከል እና ክትባቱን ለማሰራጨት እየተደረግ ያለው የጋራ ርብርብም ዓለም አቀፋዊ ወንድማማችነትን ያመላክታል።   

ይሁን እንጂ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት እና የዓለም አይሁድ ኮንግረስ የክትባት ብሔርተኝነት እንዳይኖር ስጋታቸውን ገልጸዋል።በተጨማሪም ሐብታም አገራት ከፍተኛውን ድርሻ በመውሰድ ፍትሐዊነትን እንዳያጓድሉም ፍርኋታቸውን አሳውቀዋል። ይህ ጉዳይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስም የተነሳ ሐሳብ ነው።

አድሎአዊ ያልሆነ ስርጭት

በየአገሩም ስርጭቱ መሆን ያለበት ግልጽ እና መዋቅራዊ ይዘት ባለው መንገድ መሰራጨት ይኖርበታል።እንዲሁም ካለው የክትባት ውስንነት አንጻር አቅርቦት እና ፍላጎት ላይጣጣም ስለሚችል አገራትም በየቀያቸው ቅድሚያ ለሚሰጠው አካባቢ ቅድሚያ በመስጠት ማዳረስ ያሻል ተብሏል።

እ᎐አ᎐አ᎐ በታህሳስ 22/2020 የቀረበው ጥናት የሚከተሉተን ሶስት ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት ዘርዝሯል፦ወረርሽኙን ማስቆም፣ተጋላጭ የሆኑትን መጠበቅ እና የጤና ባለሙያዎች መጠበቃቸውን ዋስትና መስጠት ናቸው።እንዲሁም የጤና ተቋማት እንዳይጨናነቁ ማድርግንም አካቷል።በተጨማሪም ጥናቱ ቅድሚያ ከሰጣቸው ቁም ነገሮች መካከልም ወረርሽኙ በኢኮኖሚ፣በትምህርት ዘርፉ እና በወጣቶች ላይም ጉዳት እንዳያመጣ መከላክለንም እስቀምጧል።

እንደ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት እና የዓለም አይሁድ ኮንግረስ አመለካከት ከላይ የተቀመጠው ፍትሐዊ የክትባት ክፍፍል ቅድመ ሁኔታዎች ለማሕበረሰቡ በታማኝነት ሊነገሩ ይገባል የሚል ነው።በቋሚነትም አድሏዊ ባልሆነ መልኩ መሰራጨት እንዳለበትም የሚያትት ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎች

በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት እና በዓለም አቀፍ አይሁድ ኮንግረስ የጋራ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በመነሳት እርሱም ስለ ሰው ልጅ ክቡርነት፥እራስህን እንደምትወድ ሁሉ ጎረቤትሕን ውደድ በሚሉት ትዕዛዛት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የጋራ መርሕ አማካይነት አገራት በሚከተሉት መርሆች መመራት ይኖርባቸዋል በማለት ጥናቱ ያትታል።

ከላይ እንደተጠቀሰው የመጀመሪያው መርሕ እኩልነት ነው።አድሎነት የሌለበት አብሮነት ማለት ነው።ይሕም ማለት ያለው ሐብት መከፋፈል ያለበት ዘርን፣ሐይማኖትን፣ቀለምን፣የገንዘብ አቅምን፣ጾታን፣ዕድሜን እና ዜግነትን ቅድመ ሁኔታው ያላደረገ መሆን ይኖርበታል የሚል ነው።ሁለተኛው መርሕ ደግሞ የሰዎች የጤና መብታቸው መጠበቅ የሚል ነው።

የሴራ ፅንሰ-ሀሳቦችን መጋፈጥ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት እና ዓለም አቀፍ የአይሁድ ኮንግረስ ለሁሉም ቤተ-ዕምነት መሪዎች እና ተቋማቶቻቸው ያልተገቡ ወሬዎች፣ያልተረጋገጡ እንዲሁም የማይጠቅሙ አስትሳሰቦችን አደባባይ ላይ በመውጣት መቃወም ይኖርባቹኃል በማለት ጥሪ አቅርበዋል።እነዚህ መረጃ እና ማስረጃ የሌላቸው ጉዳዮች ማሕበረሰቡ በጤና አገልግሎት ዘርፉ ላይ ያለውን ዕምነት ይሸረሽራል።እንዲሁም እነዚህ የሚነዙ አሉባልታዎች በተረጋገጠው ክትባት ላይም ማሕበረሰቡ ያልተገባ ጥርጣሬ እንዲኖረው እያደረጉት ነው።በመሆኑም ወረርሽኙን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመከላከል ያግዳልም ብለዋል።ስለዚህም የሁሉም ቤተ-ዕምነቶች እና መሪዎቻቸው ይሕንን አሉታዊ ሁኔታን መቃወም ይኖርባቸዋል በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ክትባቱን ግዲታ እንዲወሰድ ማድረግን በሚመለከትም ሁለቱም ተቋማት ወረርሽኙን ለመግታት በሚደረግ ትግል እና የማሕበረሰብ ጤናን ለማረጋገጥ በሚደረግ ርብርብ ሕጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ተስማምተዋል።

28 December 2020, 10:39