በቫቲካን የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቫቲካን የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር

“ክርስቶስ የአሕዛብ ብርሃን ነው። ስለዚህም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሰበሰበው ይህ ቅዱስ ጉባኤ ወንጌልን ለፍጥረት  ሁሉ ሲያውጅ (ማርቆስ ፲፮፥፲፭ ተመልከት) ባለችው ቤተ ክርስቲያን ፊት የሚያንፀባርቀው የክርስቶስ ስዎችን ሁሉ ያበራ ዘንድ ታላቅ ፍላጎት አለው::

ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር ባላት ግንኙነት አማካይነት ከእግዚአብሔርና ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር የሚያገናኝ ምሥጢር ወይም ቅርብ የሆነ የአንድነት ምልክት ሰለሆነች ይህ አንድነት የሚከናወንበት መሳሪያ ናት::

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ስለዚህ ይህ ጉባኤ ባለፉት ጉባኤዎች የተቀየሰ ጎዳናን በመከተል የቤተክርስቲያንን ማንነትና የተልእኮዋን አለማቀፋዊነት ለምእመናንና ለመላው ዓለም ሕዝቦች አብራርቶና ዘርዝሮ ለመግለጽ ያቅዳል። ዛሬ የሰው ልጅ በማኀበራዊ ኑሮ ፤ በቴክኒክና በባህል ከቀድሞ ዘመናት  ይልቅ በይበልጥ እርስ በርስ ተቀራርቦ ስላለ በአሁኑ ሁኔታዎች ሰዎችን ሁሉ ወደ ክርስቶስ አንድነት ማምጣት ለቤተክርስቲያን አሳሳቢና አስቸኳይ ስራ ሆኖባታል።

“ዘለዓለማዊው አብ ከጥበቡና ከደግነቱ በመነጨ ነፃና ምሥጢራዊ በሆነ ዕቅድ መላውን ዓለም ፈጠረ :: ዕቅዱም ሰዎች በመለኮታዊ ሕይወቱ ተሳታፉዎች ይሆኑ ዘንድ እነርሱን ከፍ ለማድረግ ነበረ። በአዳም ምክንያት ከወደቁ በኃላም አልተዋቸውም” ነገር ግን የማይታየውን የአምላክ አምሳልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ‘(ቆላ ፩፥፲፭—፲፯ ተመልከት) የሆነው የአዳኙ የክርስቶስ መምጣት አስቀድሞ እነርሱ የሚድኑባቸውን እርዳታዎች ከመስጠት አላቋረጠም። እግዚአብሔር አብ ” ልጁ በብዙ ወንድሞች መካክል በኩር ይሆን ዘንድ ከዘለዓለም ጀምሮ ያወቃቸው ” ምርጦችን ሁሉ ‘ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አሰቀድሞ ወስኖአል ‘ (ሮሜ 8፡19) አምላክ በክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውሥጥ ለመሰብሰብ ዓቀደ።ይህች ቤተክርስቲያን ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በምሳሌ ተነግራ ትገኛለች፣ ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ኪዳን አማካይነት በእስራኤል ታሪክ ሁሉ ድንቅ ለሆነ ነገር ሁሉ ተዘጋጅታለች። ቀጥሎም በአሁኑ በኃለኛው ዘመን የተቋቋመችው ቤተክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ በእርሰዋ ላይ ከወረደ በኃላ ተገለጠች። በዓለም መጨረሻም ሙሉ ክብርን ትጎናጸፋለች።እንግዲህ በአበው መጻሕፍት እንደሚነበብ ከአዳምና ከጸድቁ አቤል ዘመን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ምርጥ ሰው ድረስ ያሉ ጻድቃን ሰዎች አለማቀፋዊ በሆነችው ቤተክርስቲያን ውሥጥ በአብ ጎን ይሰበሰባሉ።

“ሰለዚህም ወልድ ከአብ ዘንድ ተልኮ መጣ:: አብ በክርስቶስ ምክንያት ዓለም ሳይፈጠር ልጆቹ እንሆን ዘንድ መረጠን ፤ ለእርሱም ወሰነን ፤ እርሱ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ፈለገ(ኤፌ 1፡4)።  ክርስቶስ የአብን ፈቃድ ይፈጽም ዘንድ የሰማይን መንግስት በምድር ላይ በመክፈቱ የአብን ምሥጢር ገለጠልን። በመታዘዙም ምሕረትን አመጣልን። አሁን በምሥጢራዊ ሁኔታ ያለችው ቤተክርስቲያን ወይም በሌላ ቃል ” የክርስቶስ መንግሥት ‘ በእግዚአብሔር ኃይል በሚታይ አኳኃን በምድር ላይ ታድጋለች::

ይህ የቤተ ክርስቲያን አጀማመርና እድገት ከተሰቀለው ከኢየሱስ ጎን በወጡት በደምና በውኃ የተመሰሉ ናቸው (ዩሐንስ 19፡34) ጌታ በመስቀል ላይ ስለራሱ ሞት በተናገረው ቃል ” እኔ ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደሆነ ሁሉንም ወደ እኔ እስባለሁ ‘ ብሎ የተነበየው ነው (ዩሐንስ 12፥ ቆሮ 5፡6) የመስቀል መሥዋዕት በታቦት ላይ በተከናወነ መጠን የደህንነታችን ስራ ይቀጥላል። እንዲሁም በቁርባን ኀብስት ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል ብቻ የሚሆኑ ሁሉም ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ይህን አንድነት ለማድረግ ተጠርተዋል። እርሱ እኛ የምንወጣበት የምንኖርበትና ወደ እርሱ የምናመራበት የዓለም ብርሃን ነው።

 “ወልድ የአብ ልጅ ፤ የተሰጠውን ስራ በፈጸመ ጊዜ (ዩሐንስ 16፡4) ቤተክርስቲያን ያለማቋረጥ ትቀደስ ዘንድና ምእመናንንም  በእርሱ አማካይነት በአንድ መንፈስ ወደ አብ ይገቡ ዘንድ ( ኤፌ 2፡18) መንፈስ ቅዱስ በጰራቅሊጦስ ቀን ተላከ። ይህም መንፈስ ሕይወትን የሚሰጥ ለዘለዓለም የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ነው (ዩሐንስ 4፡14)። ሟች የሆነ ሰውነታችን በመጨረሻው ቀን  በክርስቶስ ይነሣ ዘንድ (ሮሜ 8፡10) አብ በዚሁ መንፈስ አማካይነት በኃጢአት ምክንያት ለሞቱ ሰዎች ሕይወትን ይሰጣል።

መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያንና እንደ ቤተ መቅደስ በሆነው በምእመናን  ልብ ውስጥ ያድርባቸዋል (1ኛ ቆሮ 3፡17)፤ በውሥጣቸውም ሆኖ ይጸልያል፤ በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውንም ይመሰክራል (ገላ  4፡6 ሮሜ 8፡15)። ይህ መንፈስ ቤተክርስቲያንን ወደ እውነት ምላት እየመራ (ዩሐንስ 17፡13) የስምምነትንና የአገልግሎትን አንድነት ይሰጣታል፤ ያስተምራታል፤ ለመንፈሳዊ ሥልጠናና ለተፈጥሮአዊ ችሎታ የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እያደለ ይመራታል፤ በጸጋው ፍሬዎችም ያስጌጣታል (ኤፌ 11፡12፤ 1ኛ ቆሮ 12፡4፣ ገላ 5፡22 ተመልከት):: በወንጌል ኃይል ያሳድጋታል፤ ሁል ጊዜም ያድሳታል፤ ከሙሽራዋ ጋር ወደ ፍጹም ውሕደት ያደርሳታል።  መንፈስና ሙሽራይቱ አብረው ጌታ ኢየሱስን” ና  (የየሐንስ ራእይ 22፡16) ይሉታል። ስለዚህም አለማቀፋዊት የሆነች ቤተክርስቲያን የአብና የወልድ የመንፈስ ቅዱስም ከሆነ አንድነት ጋር በመዋሐድ አንድ ላይ ተሰብስቦ የሚኖር ሕዝብ ሆና ትታያለች።

28 October 2020, 15:22