በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ መንገድ፤     በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ መንገድ፤  

ስብዓዊ ክብርን ማስጠበቅ፣ መረጃን መለዋወጥ እና ወንድማማችነትን ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ።

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የዕርዳታ ሰጭ ድርጅት፣ ማክሰኛ ሰኔ 2/2012 ዓ. ም. በሮም የጋራ ስብሰባ ማካሄዳቸው ታውቋል። በቫቲካን ማኅበራዊ ሚዲያ በኩል በቀጥታ የተላለፈው ስብሰባ ዋና ዓላማ፣ ቤተክርስቲያን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ አገልግሎቶች ለማቅረብ በምታደርጋቸው ዝግጅቶች ላይ ለመምከር መሆኑ ታውቋል።

የቫቲካን ዜና፤

ቤተክርስቲያን ለምታበረክታቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የጋራ መድረክን መፍጠር እና በቂ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የስብሰባው ተካፋዮች አስታውቀው፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየወቅቱ እንደሚያስገነዝቡት፣ የሰው ልጅ ከተቀረው ዓለም ጋር በእጅጉ የሚገናኝ በመሆኑ አንድነትን ማጠናከር እና ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል። በቅድስት መንበር ውስጥ ይህን አንድነት የሚያስተባብር፣ የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የዕርዳታ ሰጭ ድርጅት መኖራቸው ይታወቃል። ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ኮዱዎ ታርክሰን፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ እና ምክትል ዋና ጸሐፊያቸው ብጹዕ አቡነ ሴጉንዶ ታያዶ ሙኞስ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የዕርዳታ ሰጭ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ክቡር አቶ አሎይስ ጆን ስብሰባውን መካፈላቸው ታውቋል።

ሦስት መሠረታዊ ርዕሠ ጉዳዮች፣

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ያዳረሰ፣ በሁሉም ማኅበራዊ ዘርፎች ከፍተኛ ቀውስን ያስከተለ መሆኑን ያስታወሰው ጉባኤው፣ በማኅበራዊ ቀውሱ ከፍተኛ ሐዘን የተሰማት ቤተክርስቲያን፣ በአምስቱም አህጉራት ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ድሃው ማኅበረሰብ መሆኑን ተመልክተዋል። በመሆኑም ቤተክርስቲያን በቁምስናዎች አማካይነት በወረርሽኙ የተጎዱት ቤተሰቦች ሰብዓዊ ክብራቸውን መመለስ እና እርዳታን ማቅረብ ቅድሚያ የሚሰጥባቸው ጉዳዮች መሆኑ ታውቃል። ከዚህም በተጨማሪ በቤተሰብ መካከል የወንድማማችነት መንፈስን እና አንድነት ማሳደግ አስፋላጊ መሆኑን ጉባኤው አስታውቋል።

የር. ሊ. ጳ. ቤነዲክቶስ 16ኛ ፈለግ፣

በቀድሞ ር. ሊ. ጳ. ቤነዲክቶስ 16ኛ ፈለግ እና በር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ተግባራት መካከል የጠበቀ ግንኙነት መኖሩን ተመልክቻለሁ ያሉት፣ በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ፣ ብጹዕ ካርዲናል ፒተር ኮዱዎ ታርክሰን፣ የቀድሞ ር. ሊ. ጳ ቤነዲክቶስ 16ኛ ስለ ተስፋ ሲናገሩ ስለመጪው ጊዜ እንደሚናገሩ፣ ስለመጪው ጊዜ ሲናገሩ ደግሞ ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩ መሆኑን አስረድተው፣ በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ሊነጣጠል የማይችል ግንኙነት እንዳለ መናገራቸውን አስታውሰዋል። በዚህ ግንኙነት በመመራት በአምስቱም አህጉራት የምትገኝ ቤተክርስቲያን ስብዓዊ ክብርን በማስጠበቅ፣ በመረጃዎችን በመለዋወጥ ሰብዓዊ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ምክር ቤት ስለመቋቋሙ፣

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተጎዱትን የዓለማችን ክፍሎች ለመርዳት በማሰብ ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስክሶስ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር መጋቢት 11/2012 ዓ. ም. በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ከሌሎች ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች ጋር በመተባበር ለኮሮና ቫይረስ ተጎጂዎች ዕርዳታን የሚያደርግ ምክር ቤት ማቋቋማቸው ይታወሳል።      

10 June 2020, 17:21