በቫቲካን ውስጥ የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ መስጫ ማዕከል፣ በቫቲካን ውስጥ የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ መስጫ ማዕከል፣  

ቫቲካን በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ስምንት ሰራተኞቹ መካከል ሁለቱ መፈወሳቸውን አስታወቀ።

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ክቡር አቶ ማቴዎ ብሩኒ መጋቢት 30/2012 ዓ. ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  እንዳስታወቁት በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ስምንት ሰራተኞች መካከል ሁለቱ ሙሉ በሙሉ መፈወሳቸውን እና ምልክት የታየብተ አንድ ሰራተኛ መገኘቱን ገልጸዋል። ምልክቱ የታየበት ግለሰብ በቫይረሱ የተያዙ ወላጅ ቤተሰቦቹን ሊጠይቅ ከሮም ከተማ ወጦት የተመለሰ መሆኑን መግለጫው አስታውቋል። የቫይረሱ መጀመሪያ ምልክት እንደታየበት ወደ ሮም ሳይመለስ በአካባቢ በሚገኝ የሕክምና ማዕከል አስፈላጊው ክትትል እና የሕክምና ድጋፍ የተደረገለት መሆኑን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ማቴዎ ብሩኒ አስታውቀዋል።

የጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ ዳይሬክተር በቫቲካን እስካሁን በቫይረሱ የተያዙት ቁጥር ስምንት መሆናቸውን አረጋግጦ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ መሉ በሙሉ ተፈውሰው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን፣ አንዷ ከሆስፒታል ወጥታ በማገገም ላይ መሆኑን፣ ሁለቱ የሕክምና እርዳታ እየተስደረገላቸው መሆኑን ሌሎች ሦስቱ በለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ መገኘታቸውን አቶ ማቴዎ ብሩኒ በጋዜጣዊ መግለጫቸው አረጋግጠዋል።           

13 April 2020, 22:05