የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ችግሮች ለመፍታት ዓለም አቀፋዊ ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ ነው አሉ

Montreal Protocol በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ስምምነት የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደረሰ  ያለውን የመሳሳት አደጋ ለመከላከል ታስቦ የተደረገ ስምምነት ሲሆን ይህ ስምምነት የተፈረመው እ.አ.አ በነሐሴ 26/1987 ዓ.ም በቪዬና በተደረገ ስምምነት ነው፣ ይህ ስምምነት እ.አ.አ በመስከረም 16/1989 ዓ.ም ሥራ ላይ መዋሉ ይታወሳል። የኦዞን ንጣፍ ሽፋን እየደርሰበት ካለው የመሳሳት አደጋ ለመታደግ በማሰብ በእዚህ የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ አደጋ የሚያደርሱ እና ለመሳሳቱ ከፍተኛ አስተዋጾ እያዳረጉ የሚገኙ ዋና ዋና የሚባሉ ንጥረ ነገሮችን ለይቶ የማውጣት ግዴታ በስምምነቱ ውስጥ መካተቱ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት አራት ዋና ዋና ንጥረ ነገሮች ተለይተው በእነዚህ በኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ ከፍተኛ አደጋ በማስከተል ላይ የሚገኙ ዋና ዋና ተብለው የተፈረጁ የመጀመሪያዎቹ አራት ንጥረ ነገሮች ላይ ማሻሻያዎች ይደረጉ ዘንድ እ.አ.አ በየካቲት 09/2008 ዓ.ም የተደረጉትን ስምምነቶች በተመለከተ ተከታታይ ውይይቶች በመደረግ ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።

በእዚህ በኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን አደጋ በተመለከተ በተደጋጋሚ በአለም አቀፍ ደረጃ ውይይቶች እየተካሄዱ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን የእዚህ መረሃ ግብር አንዱ የሆነው 31ኛው በኦዞን ንጣፍ ሽፋን ዙሪያ የሚደርገው ስብሰባ ከጥቅምት 24-28/2012 ዓ.ም በሮም ከተማ በሚገኘው የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት መዐክል ውስጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእዚህ 31ኛው ዓለም አቀፍ ስብሰባ የሚሆን የጹሑፍ መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ የጹሁፍ መልእክት  የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አማካይነት ለስብሰባው ተካፋዮች ተነቡዋል። የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮን መልእክት ለተሳታፊዎች ባነበቡበት ወቅት እንደ ገለጹት በኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን አደጋ ለመከላከል ይችላ ዘንድ ዓለም አቀፍ ትብብር ያስፈልጋል ማለታቸው ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል ለአከባቢ ጥበቃ ማደረግ ብቻ በራሱ በቂ እንዳልሆነ በመልክእክቱ የገለጹ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰው ልጅ የተቀናጀ ልማት አስተዋጾ በማደረግ ላይ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት በተቀናጀ መልኩ ተግብራቸውን ማከናወን እንደ ሚጠበቅባቸው ገልጸው በእዚህ ረገድ የሞንትሪያል ስምምነት ዓለም አቀፍ ትብብር ለመፍጠር እያዳረገ ለሚገኘው ከፍተኛ አስተዋጾ ቅዱስነታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመልእክታቸው ጨምረው እንዳስታወቁት “በዓለም ውስጥ የሚገኙ አገራትን ሁሉ ባካተተ መልኩ አንድነት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ዓለም አቀፍ ድጋፍን ለማግኘት ጥረት ማደረግ እንደ ሚገባ ገልጸው አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ሀገሮች ይህንን የሞንትሪያል ስምምነት መፈረማቸው መልካም  አጋጣሚ እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል የዛሬ 35 ዓመት ገደማ በቪዬና ከተፈረመው አለም አቀፍ ስምምነት በኋላ በተከታታይ የተደረጉት ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደ ሚያሳዩት በኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደረሰ የሚገኘው ጉዳት የቪዬና ስምምነት ከተደረገ በኋላ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መምጣቱን እንደ ሚያሳይ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል በቪዬና ከተደርገው ስምምነት በኋላ የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደርሰ የሚገኘው አደጋ ቀስ በቀስ እየቅነሰ መምጣቱ ሦስት ዋና ዋና ቁምነገሮችን እንድንማር ያደርገናል በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በቅድሚያ በተለያዩ አገራት ውስጥ የሚገኙ ማኅበራዊ የሆኑ ተቋማት መካከል ከፍተኛ የሆነ ትብብር እንዲፈጠር ማደረጉን ገልጸው “ይህ ትብብር ምድራችንን ከውድመት ለመጠበቅ እና የሰው ሐብት ልማት ለማጎልበት የሚያስችሉ አስፈላጊ ውጤቶችን እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያሳያል” ብሏል።

ሁለተኛው የምንማረው ቁምነገር እኛ እየተጋፈጥነው የምንገኘው “ባህላዊ ተግዳሮት” “በነገሮች መካከል ያለውን ሚስጥራዊ የግንኙነት መረብ ችላ የሚል እና አንዳንድ ጊዜ አንድ ችግርን ለመፍታት ሌላ ችግር የሚፈጥረው ቴክኖሎጂ ለሁሉም ነገር መፍትሄ እንደ ማያመጣና በቴክኖሎጂ ላይ ተመስርተን ብቻ ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ ማምጣት አይቻልም የሚለውን ትምህርት ለመቅሰም ይችላል ብለዋል።

በመጨረሻም “ሁሉም ነገሮች እርስ በእርሳቸው የተገናኙ መሆናቸውን” ለመረዳት ችለናል በማለት የገለጹት ቅዱስነታቸው የምናስተላልፋቸው ማነኛውም ዓይነት ውሳኔዎቻችን የተለያዩ ግንኙነቶች በጥንቃቄ ማጤን እና ውጤታቸውም በርካታ የተወሳሰቡ ደረጃዎች ማልፈን እንደ ሚያካትት” ተምረናል ብለዋል።

Montreal Protocol በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ስምምነት የኦዞን ንጣፍ ሽፋን ላይ እየደረሰ  ያለውን የመሳሳት አደጋ ለመከላከል ታስቦ የተደረገ ስምምነት ሲሆን ይህ ስምምነት የተፈረመው እ.አ.አ በነሐሴ 26/1987 ዓ.ም በቪዬና በተደረገው ስምምነት መሰረት ሲሆን ይህ ስምምነት እ.አ.አ በመስከረም 16/1989 ዓ.ም ሥራ ላይ መዋሉ ይታወሳል።

08 November 2019, 12:31