የቅድስት ሥላሴ ሕላዌ የቅድስት ሥላሴ ሕላዌ  

አባ ካንታላሜሳ “የቅድስት ሥላሴን ኅብረት ማሰላሰል አለመስማማቶችን ለመቅረፍ ይረዳል!”

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በታላቅ መንፈሳዊነት ለማክበር ያስችለን ዘንድ የመዘጋጃ ወቅት የሚሆነን የስብከተ ገና ሳምንት በኅዳር 23/2011 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህንን የስብከተ ገና ሳምንት የዝግጅት ወቅት በማስመልከት በቫቲካን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፣ የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪ የሆኑት ብጹዕን ጳጳሳት እና ቀሳውስት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤት ሰባኪ የሆኑት አባ ራኔሮ ካንታላሜሳ ይህንን ሁለተኛ የስብከተ ገና ሳምንት በማስመልከት በቫቲካን በሚገኘው ሬደምቶሪስ ማተር በመባል በሚታወቀው የጸሎት ቤት በዛሬው እለት ማለትም በታኅሳስ 05/2011 ዓ.ም ያደርጉት አስተንትኖ ቅድስት ሥላሴ ዙሪያ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የቅድስት ስላሴን ምስጢር ማሰላሰል ማነኛውንም አለመግባባቶችን ይፈታል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

“እግዚኣብሔር አብ፣ እግዚኣብሔር ወልድ፣ እና እግዚኣብሔር መንፈስ ቅድስ” እርስበርሳቸው ከፍተኛ የሆነ ሕብረትና ፍቅር እንዳላቸው የገለጹት አባ ካንታላሜሳ በዓለም ውስጥ ካሉ ቦታዎች ሁሉ ከፈተኛ የሆነ ፍቅር ያለበት፣ ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ወደድ የሚለው ህግ የሚፈጸምበት አንድ ቦታ አለ፣ ይህም ቅድስት ሥላሴ ነው” ብለዋል።

ማነኛውንም የቅድስት ሥላሴ ምስል በምንመለከትበት ወቅት ሁሉ ሦስቱ አካላት አንድ ሆነው እንመለከታለን ይህም የሚያስያው በመካከላቸው ያለውን የጠበቀ ሕበረት እና ፍቅር የሚያሳይ መስታወት መሆኑን በመግለጽ” አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት አባ ካንታላሜሳ በዚህም መሰረት ነው ኢየሱስ “እኛ አንድ እንደ ሆንን እናንተም አንድ ትሆኑ ዘንድ ጸሎቴ ነው” ብሎ የተናገረውም በዚሁ ምክንያት እንደ ነበረ ጨምረው ገልጸዋል።

ቅድስት ስላሴ እና ሕብረት

ቅድስት ሥላሴ "ወደ አንድነት የሚወስደውን ጎዳና በማሳየት  ወደ አንድነት የሚያደርሰውን እውነተኛ መንገድ ያሳየናል፣ "አንዱ በአንዱ ውስጥ ሳይጠቃለሉ ሦስቱም አንድም ሦስትም ሆነው በሕበረት ይኖራሉ” በጣም ውብ የሆን አፍቅር በመካከላቸው አለ፣ አንዱ አንዱን አይጨቁንም ሦስቱም እኩል ናቸው” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት አባ ካንታላሜሳ ይህም ለእኛ ለክርስቲያኖች መልካም አብነት በመሆን ከልብ በመነጨ መልኩ እንድንዋደድ አብነት የሚሆነን ተግባር እንደ ሆነም ጨምረው ገልጸዋል። ሕብረትን መፍጠር ማለት ምንነታችንን ትተን የሌላን ሰው ማንነት መላበስ ማለት ሳይሆን ያለንን ማንነት እና አመላካከት ይዘን በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ሕብረት በመፍጠር መሥራት ማለት እንደ ሆነ ገልጸው ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን በአንድነት በማከናውን ሳይሆን የተለያዩ ተግባሮችን በተለያዩ ሰዎች አማካይነት ለአንድ ዓላማ ማከናወን ማለት ነው ብለዋል።

አለመግባባቶችን ለመፍታት

የቅድስት ሥላሴ ሕላዌ "ህያው እና መቼም የማያረጅ እውነታ" እንደ ሆነ በመግለጽ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት አባ ካንታላሜሳ የቅድስት ሳሌሴ ሕይወት የፍቅር መገለጫ መሆኑን ገልጸው በዚህ መሰረት አንድ ቅዱስ የሚባል ሰው ባልንጀራውን እንደ ራሱ አድርጎ ይወዳል ብለዋል። የቅድስት ሥላሴ ምጢር ላይ ማሰላሰል በዓለም ውስጥ የሚታዩትን አለመግባባቶችን ለመፍታት እንደ ምያስችለን የገለጹት አባ ካንታላሜሳ አስተሳሰባችን ሊለያይ ይችል ይሆናል ነገር ግን ክርስቲያን በመሆናችን የተነሳ የቅድስት ስላሴን አብነት በመከተል ልባችን አንድ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

14 December 2018, 15:54