Macerata: sit in rete antirazzista davanti prefettura Napoli Macerata: sit in rete antirazzista davanti prefettura Napoli  

“የሌላን ዜጋ ፍርሃት፣ ዘረኝነትና ወገንተኝነት በዓለም አቀፍ ስደተኝነት” በሚል ርእስ ስብሰባ ተካሄደ

ሁሉም ክርስቲያኖች እና ቤተክርስቲያኖች ሰው ሁሉ ክብርና ህጋዊ ከለላ እንድሚያስፈሊገው መስበክ ይገባቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን እውነታ ሁልጊዜ ይዛ መጓዝ እንዳለባትና ሰለ ሰዎች ሁሉ ደኅነነትና እኩልነት በመስበክ በየትኛውም መንገድ ያለውን መድልዎ ማውገዝና ሓዋርያዊ እንክብካቤ በተለያዩ ረገድ ትምህርትና ወንድማማችነትን በመስበክ በተለይም ወጣቶችን ለመርዳት በየትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ማሳተፍ አለባት።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ከመስከረም 18 እስከ 20 2018 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. የሌላን ሕብረተሰብ ፍርሃት ዘረኝነትና ኣገራዊ ወገንተኝነት በሚል ርእስ በጥምረት ማለትም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እድገትን ለማጎልበት ባቫቲካን ሥር በሚሠራ ኣንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም በዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ሕብረትና የቤተክርስቲያን ሕብረትን ከሚደግፍ ኣንድ ሌላ ሓዋርያዊ ተቋም በሮማ ከተማ ስብሰባ መካሄዱ ተገለፀ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታችንን እንናገራለን እናም እኛ የሰው ልጆች እንደሆንን በእግዚአብሔር እንደተፈጠርንና እና በእርሱም እንደምንወደድ እናምናለን። የሰው ልጆች ሁሉ እኩል ክብርን የተላበሱ ናቸው እኩል የሆነ መሰረታዊ የሰብአዊ መብትም አላቸው ትብሏል።

በአለም አቀፋዊ ሁኔታ በአገር ውስጥ እና በአገሮች መካከል ስደተኞችን በተመለከተ በተለይም የሌላን ሕብረተሰብ ፍርሃት ዘረኝነትና ኣገራዊ ወገንተኝነት በሚል ርእስ ከመስከረም 18-20 2018 ዓ.ም. እ.ኣ.ኣ. በጥምረት በተዘጋጀው ስብሰባ መወያየታቸው ተገለፀ ሲሆን ተሳታፊዎቹ በስደተኞች እና በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰውን የሌላን ሕብረተሰብ የፍርሃት የዘረኝነትና የኣገራዊ ወገንተኝነት ምላሽ ለመስጠት ለመግለጽ እና ለመተንተን በመቀጠልም ስደት ተፈናቃይነትና መገለል እንዴት ወንጀል ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር እንደሚያያዙ መነጋገሩና በችግሮቹም ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት ማድረጉ ታውቋል። በውይይቱ ወቅት ይህ በስደተኞች እና በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰው የፍርሃት የዘረኝነትና የኣገራዊ ወገንተኝነት ጉዳይ በቤተክርስቲያንም ውስጥ ኣልፎ ኣልፎ እንደሚከሰት ታውቋል።

ከተለያዩ የቤተክርስቲያን ክፍል ከተለያዩ ክልሎች የሲቪል ማህበራት እና መንግስታዊ ባልደረባዎች የተውጣጣን ብንሆንም የእኛ የጋራ መሰረት የሆነው መነጋገሪያች ሁሉም የሰው ልጅ እኩል ክብር እና መብት እኩል እና በሁሉም እኩል ዋጋ ያለው መሆኑን ማረጋገጥና ይህም መብቱ በየትኛውም ቦታ ተከብሮና ተጠብቆ እንዲኖር ማድረግ ሲሆን በውጤቱም በእግዚኣብሔር ለተጠራንበት ዓላማ ክፉን ሁሉ ከሰው ልጅ ለማራቅና በፍትህ ለመንቀሳቀስ እንዲሁም ስላምን በመጎልበት ዓለምን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሆነ አብራርተዋል። በመቀጠልም በዚሁ ስብሰባ የተለያዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚነሱትን ጥያቄዎችና የተለያዩ ልዩነቶችን ለማጥበብ የሚሰጡት መፍትሔ ሓሳቦች ቤቱ ከተስማማበትና ካፀደቀው ያ ስምምነት ኣንደ ቋሚና ቀጣይነት እንዳለው እንድሚወሰድ ተገልጿል።

ስደትን በተመለከተ ሽግግር ወይ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ የሰብዓዊ ሁኔታ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። እሱም ከሰው ዘር ታሪክ ያለፈውን የአሁኑን እና የወደፊቱን እንዲሁም መላውን መጽሐፍ ቅዱሳ ብንመለከት ተመሳሳይ ነው። ሁላችንም በዚች ምድር ላይ ስደተኞችና እንግዶች ነን ሁላችንም የአንድ ሰብአዊ ቤተሰብ ስብስብ ነን።

የግዳጅ የመፈናቀልና የስደት የጉዞ በውስጣቸው ያልተፈቱ የጭካኔ ድርጊቶች አካተዋል በዚህም ምክንያት የዓለም ኢኮኖሚ ቀውስ አስገዳጅ ፖሊሲዎች ከዚሁም ጋር በተያያዘ እንደ ድህነት የምግብ ዋስትና እጦት የሥራ ዕድል እጦት እና የመሳሰሉት ሌሎችም ችግሮች እንደሚያያዙ ተብራርቷል። ከዚሁ ጋር ኣብሮ የአየር ንብረት ለውጥ መጨመርና በየጊዜው መቀያየር ለዚህ ስደትና ፍልሰት የበኩሉን ኣስትዋፅኦ እንደሚያደርግ ተወስቷል።

ስደተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ወይም ደግሞ በዚያ ባሉበት ለመኖር መብት እንዳላቸው ቢገነዘቡም በተለይም በድህነት በጦር ግጭቶች ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች ለሚፈናቀሉ ሰዎች ከየትኛዉም የዓለማችን ክፍል ቢሆኑ እነዚህ የጥገኝነት ተቋሞች ተገቢውን እርዳታና ሰብኣዊ ክብር እንዲያሳዩኣቸው ይገባል የሚል ሓሳብም ተሰንዝሯል።

ስደት በአጠቃላይ በሁለቱም ሀገሮች ማለትም ወደሚሰደዱበትና የትውልድ ኣገራቸው ወይም መነሻ ኣገራቸው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተግዳሮቶች እንዳሉ ይታወቃል ቢሆንም ግን በተለይም የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ስደተኞች መብት ማክበርና መጠበቅ እንደሚያፈልግም ተብራርቷል።

በስደተኞችና ተፈናቃዮች ላይ የሚሰነዘሩትን ኣስከፊ ስድቦችና ኣሽሙሮች እንዲሁም የተለያዩ ክብረነክ ጉዳዮችን በሀገሮች መካከል በሶሻል በባህል ወይም በዓለም አቀፍ ፍልሰት አውድ ውስጥ ያሉ የሃይማኖት ማህበረሰቦች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት የተለያዩ ኣመለካከቶችና ተሞክሮዎችን ከተለያዩ ሃይማኖታዊ ባሕሎች የተወሰዱ ምስክርነቶችን በማዳመጥ የጦርነትን የድህነትን የጥገኝነት ህጋዊ ከለላና ሰብአዊ ክብርን በተመለከተ ተጋላጭ የሆኑት ሰዎች ምን ዓይነት ነገር በውስጣቸው እንደሚሰማቸው ለማወቅ ከምክንያቶቹ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ላይ ትኩረት በማድረግ እንደተወያዩባቸው ተገልጿል።

በመጀሪያ ደረጃ ስለ ባዕድ አገር ፍራቻ የሚለው ቃል በሌላው ሕብረተሰብ ዘንድ የሚያሳድረው ከፍተኛ የሆነ ተፅእኖ ኣለ። ከዚህም ውስጥ እነዚህ በተለያየ መልክ ለብዙ ችግሮችና ስደቶች ተጋላጭ የሆኑ ሕብረተሰቦች ተገቢ የሆነ እርዳታናና የመጀመሪያ ስብኣዊ እርዳታም ከሚሄዱበት ኣካባቢ ካሉ ሕብረተሰቦች የማግኘቱ ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ያለበት ሁኔታም አንዳለ ተብራርቶ በተለይም ስደተኞቹ ወይ ተፈናቃዮቹ ከሚሄዱበት ኣካባቢ ያሉ ሕብረተሰቦች ይህንን ነገር በሚገባ ማስተዋል እንዲችሉ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸውና ስደተኞቹ ወይ ተፈናቃዮቹ በዚህ ችግር ምክንያት ሰብኣዊ ክብር ጥሰትና መገለል እንዳይደርስባቸው ማድረግ እንድሚገባ ተብራርቷል።

እንደተሳታፊዎቹ ኣገላለፅ ይህ ፍርሃት ከእራሱ ጋር ውስብስብ የግል ወይም ኅብረት ግንኙነት ካለፈው ከአሁኑና ወደፊት ከሚመጡት ጊዜኣት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በራስ ማንነት በደኅነነት እንዲሁም ወደፊት የሚመጡትን ተግዳሮቶች ሁሉ በብቃት ለመዋጋት ድፍረትና ኃይል ሊያጠፋ እንደሚችል ተብራርቷል።

ኣንድ ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም በጦር መሣሪያ ግጭት በተበላሹ ብሔራዊ እና ክልላዊ መምሪያዎች በከፋ የድህነት አደጋ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌሎች ክስተቶች የሚፈጠር ፍርሃትን መቀበል ወይም እውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው።

ዘር ማለት በማህበራዊ ግንባታ መካከል ያለውን ልዩነት ሰብአዊ ቡድኖችን አካላዊ ማህበራዊ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ መስፈርቶችን ለማስፋፋት ለማብራራት እና ለማስረዳት የቀረበ ነው። ዘረኝነት ማለት በተወሰኑ ሰዎች ወይም ቡድኖች ላይ በቆዳቸው ቀለም ምክንያት የሚፈጠሩ ስልታዊ እና ስልታዊ ያልሆኑ ተፅእኖዎች ናቸው። በቆዳው ቀለም ኣማካኝነት ብቻ ሰብአዊ አካላዊ ማህበራዊ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ መስፈርቶችን ማስፋፋት ዘረኝነት ነው። ይህም ዘረኝነት ሰዎችን እርስ በእርስ ይለያያል። በተለያየ የሓሰት ሁኔታ ኣንዱ ከፍ ያለ ኣንድ ዝቅ ያለ ኣንዱ ጥቁር ኣንዱ ነጭ ኣንዱ የበላይ ኣንዱ የበታችች በማለት በሰዎች መሓል መለያየትን እንደሚፈጥር ተብራርቷል።

በዓለም አቀፋዊ ድንጋጌ የዘር መድልዎ በተመለከተ ያወጣው ኣንቅፅ 11 እንዲህ ይላል ማንኛውንም ልዩነት ወይም ማግለል ወይ የበላይነት በዘር በቀለም ወይም በብሔር ማንነት ላይ የተመሠረተ ገደብ ወይም ምርጫ ወይም ዕውቅና ወይም መዝናኛ ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የላቸውም።

ዘረኝነት በአንዳንድ ወገኖች የተለያዩ ተጋላጭነትን ይፈጥራል ይከፋፍላልም። የተወሰነ ቡድን ብቻ የሌላውን መብት በመንፈግ የእሱን ሓሳቢና ኣስተሳሰብ ብቻ እንድትከተል ያስገድዳል። ከዚህ አኳያ ዘረኝነት ፍጹም የሆነ ኃጢአት ነው በተለይም ከክርስትና እምነት የማይቻል ነው። ይህ ነገር በሁለቱም በተፈናቃዮችም ሆነ በሚሰደዱበት ኣገር የሚከሰት ተግባር ነው። ሁሉም ሰው ዘረኝነትን መቃወምና መዋጋት ኣለበት ምክንያቱም ሰብአዊ ክብርን ያጎላል ሰው ሁሉ የኣንድ ሰብአዊ ቤተሰብ እንዳይሆን ያደርጋል በሰዎች ውስጥ ያለውን የእግዚኣብሔር መልክ ያጠፋል።

ብሔራዊ ወገንተኝነት በኣንድ በተወሰነ ክልል ላይ የኣንድ የፖለቲካ ተቋም ወይም ኣንድ ቡድን የራሱን ዓላማና ግብ ለማስፈፀም ሲል በኣንድ ሕብረተሰብ ላይ የሚጭነው ተፅእኖና ፍርሃት ነው። በተለይም ይህ ዓይነቱ ኣሰራር በሰላማዊ ከለላ ሥም ኣንድን ሕብረተሰብ ከሌላ ሕዝብ ጋር በምንም መልኩ እንዳይገናኝ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ ውርርስ እንዳይኖረው እነዚህ ብሔራዊ ወገንተኝነት ላይ የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች የሚያደርጉት ተፅእኖ መሆኑም ተገልጿል። በሌላ መልኩ የተቸግሩትን ኣለመርዳት ከጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ትምሕርት ውጭ ነው ስለዚህ ሁሉም ክርስቲያኖችና ለሰብአዊ መብት የቆሙ ሁሉ ይህንን ብሔራዊ ወገንተኝነት ማዉገዝ እንደሚያስፈልግም ተብራርቷል።

በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን መድረኮች የመከፋፈልን ሰብአዊ ክብርን የሚነቅፉ ድርጊቶችን ከማስተባበር እንዲቆጠቡ ማድረግ እንድሚገባ እንዲሁም ይህ የስደት ታሪክ ገና በኣብርሃም ዘመንም እንደነበረና እንግዶችን ከሚስቱ ሳራ ጋር በመሆን በቤታቸው እንደተቀበሉ በኦሪት ዘፍጥረት 18, 1-16 መጠቀሱን እንዲሁም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 25, 35-40 ላይ እንግዳን በመቀበል የፍቅር ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ማብራራቱ ተወስቷል።

ሁሉም ክርስቲያኖች እና ቤተክርስቲያኖች ሰው ሁሉ ክብርና ህጋዊ ከለላ እንድሚያስፈሊገው መስበክ ይገባቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን እውነታ ሁልጊዜ ይዛ መጓዝ እንዳለባትና ሰለ ሰዎች ሁሉ ደኅነነትና እኩልነት በመስበክ በየትኛውም መንገድ ያለውን መድልዎ ማውገዝና ሓዋርያዊ እንክብካቤ በተለያዩ ረገድ ትምህርትና ወንድማማችነትን በመስበክ በተለይም ወጣቶችን ለመርዳት በየትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ማሳተፍ እንዳለባት ተነስቷል።

እኛ የተጠራነው ኃይልን የሚጠቀሙ እና ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ እና በወደፊት ሰብዓዊ ማህበረሰብ ላይ ተፅእኖ ያላቸውን ውሳኔዎች በሃገራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ለማጣራት ነው። ሁሉም አማኞች ሊያቀርቡት የሚችሉት ምክር በወርቃማው አገዛዝ ማለትም ሰዎች ለኣንተ ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን ኣንተም እንዲሁ ለሌሎች ኣድርግ ያሚለውን በማቴዎስ ወንጌል 7፡12 ላይ ያለው የሰዎችን መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ለመጠበቅና ማግለልን ለመዋጋት ወሳኝ መሆኑ ተወስቷል።

የተባበሩት መንግስታት እና አባል ሀገራት ልዩነትነና መገለልን እንዲያወግዙ ተጨማሪ ጥረቶችን ማበረታታት እንደሚያስፈልግና ሁሉም ዓይነት የመድልዎ ዓይነቶች የተፃፉ መግለጫዎች ድርጊቶች እና የዘር መድልዎ ሁከት እና ተያያዥነት ያላቸው አለመቻቻል ሁሉ ሊወገዙ እንደሚገባ ተጠቅሷል። ሁሉንም ዓይነት የመድልዎ ዓይነቶች ለማጥፋትና እና ሰላማዊ ኑሮን ለማስፈን አብያተ ክርስቲያናት የሲቪል ማህበረሰብ የትምህርት ተቋማት የግሉ ዘርፍ እና መንግስታት ሁሉ ተባብረው መሥራትና መደጋገፍ ሓሳብንም በጋራ ማንሸራሸር እንድሚያፈልግ ተጠቅሷል።

አብያተ ክርስቲያናት በሲቪል ማህበረሰብ እና ፖለቲካ ሕይወት ውስጥ አስፈላጊ ተዋንያን ናቸው። በፖለቲካ በሃይማኖት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች የሁላችን ቤት የሆነችውን ፕላኔታችንን ለመንከባከብ እየተጎዱ ላሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ ጥበቃ መረብን ለመገንባት ማስተባበር እና በመሳሰሉት ህግን እና የስነ-ምግባር እሴቶችን ለማዳበር መርሆዎችን ለመተግበር የእምነት ማኅበረሰቦች ኣቅማቸውን ለማጎልበት በሲቪል ማኅበራ እና በምሁራን መካከል የሚደረገው ውይይትና ሓሳብ መለዋወጥ ዘረኝነትን ለመዋጋት አስፈላጊና ወሳኝ መሆናቸው ተብራርቷል።

በመጨረሻም የስብሰባው ተሳታፊዎች ዘረኝነትን ማግለልን የሌላን ዘር ፍራቻን ስደትንና ከራስ ቦታ መፈናቀልን አጥብቀው እንድሚዋጉና በክርስቶስና በቤተክርስቲያን በኩል ሁሌ የሚሰበከውን ተስፋና ፍቅር ለሁሉም የሰው ልጆች በተለይም በችግር ላይ ላሉ ሁሉ በማድረስ ጠንክረው እንደሚሰሩ ኣስታውቀው ከሞት መንገድ ይልቅ የሕይወት መንገድ ጠንካራ መሆኗን ተነጋግረው ስብሰባውን ደምድመዋል።

20 September 2018, 16:53