ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የላትቪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤድጋርስ ሪንኬቪችስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የላትቪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤድጋርስ ሪንኬቪችስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ  (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከላትቪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የላትቪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤድጋርስ ሪንኬቪችስን በቫቲካን ተቀብለው አነጋገሩ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የላትቪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤድጋርስ ሪንኬቪችስ በቫቲካን በሚገኘው ሐዋርያዊ መንበራቸው ውስጥ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገልጿል። ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ከተገናኙ በኋላ ሚስተር ኤድጋርስ ሪንኬቪች ከቫቲካን ዋና ጸሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ጋር የተገናኙ ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል ስላለው ግንኙነት ውይይት አድርገዋል።

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት መግለጫ ከካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር የተደረገው ውይይት  “አክብሮት” የተሞላበት ነበር በማለት የገለጸ ሲሆን “በቅድስት መንበር እና በላትቪያ ሪፐብሊክ መካከል ስላለው መልካም ግንኙነት እርካታ የተገለፀ ሲሆን ይህም የክርስቲያን እምነት በላትቪያ ሕብረተሰብ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት አጉልቶ ያሳያል ብሏል።

ዩክሬን እ.አ.አ እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ የሶቪየት ኅብረት አካል ከነበረች ሲሆን ከላትቪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጋር በተደረገው ስብሰባ በተለይ በዩክሬን ውስጥ ለቀጠለው ግጭት ትኩረት ተሰጥቶ ነበር።

ሰላማዊ መፍትሄዎችን በመፈለግ ረገድ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሚና ተወስቷል።

በውይይቱ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ልማት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችም ተዳስሰዋል።

17 May 2024, 09:30