ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ የፎቶ ግራፍ ምስል በስጦታ ሲቀበሉ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ የፎቶ ግራፍ ምስል በስጦታ ሲቀበሉ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ጦርነትን የሚቃወም የፎቶ ምስል በስጦታ ተበረከተላቸው

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ረቡዕ ግንቦት 3/2014 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት ምዕመናን ካቀረቡላቸው ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ከእውቁ ቪዬትናማዊ ፎቶ ዘጋቢ ኒክ ኡት ጋር ተገናኝተው ሰላምታ የተለዋወጡ ሲሆን፣ ፎቶ ዘጋቢው እ. አ. አ በ1972 ዓ. ም. ያነሳውን እና የቪዬትናምን ጦርነት አስከፊነት የሚገልጽ የፎቶ ግራፍ ምስል ለቅዱስነታቸው በስጦታ አበርክቶላቸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

እ. አ. አ ስኔ 8/1972 ዓ. ም. ታንግ ባንግ በተባለች የቪዬትናም መንደር የታየውን የጦርነት አደጋን በሚገባ የሚያታውሱት ሁለቱ የቬትናም ተወላጆች፣ ወ/ሮ ኪም እና ኒክ ኡት ከቅዱስነታቸው ጋር በተገናኙበት ወቅት ጦርነቱ በቪዬትናም ውስጥ በቀሰቀሰበት ወቅት በአንዲት ሕጻን ላይ ያስከተለውን ጉዳት እና ከፍተኛ ድንጋጤን የሚያስታውስ የፎቶ ግራፍ ምስል ለቅዱስነታቸው በስጦታ ያበረከተላቸው ሲሆን፣ የፎቶ ግራፍ ምስሉ በሃያኛው ክፍለ ዘመን ታሪክ ውስጥ እውቅና ከተሰጣቸው ምስሎች መካከል አንዱ እንደሆነ ታውቋል። 

ዛሬ ከግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በኋላ ወ/ሮ ኪም እና አቶ ኒክ ረቡዕ ግንቦት 3/2014 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ጦርነትን በመቃወም፣ የጦርነትን አስከፊነት የሚገልጽ ፎቶ ግራፍ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ለር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በስጦታነት አቅርበውላቸዋል። ጦርነት እንዲቆም የሚያሳስብ ፎቶግራፍ ከቪዬትናም ከመጡ እንግዶች የየተቀበሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ተመሳሳይ ጦርነት በርካታ የሰውን ሕይወት እየቀጠፈ ከሚገኝበት ከምስራቅ አውሮፓ አገር ዩክሬን የመጡ ሁለት ወጣት ሴቶችን ቅዱስነታቸው በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተቀብለዋቸዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተቀበሏቸው ሁለቱ ሴቶች፣ በዩክሬን ውስጥ የማሪፖል ከተማን ከጥቃት ለመከላከል የተሰለፉ የዩክሬን ወታደሮች ሚስቶች ሲሆኑ፣ ቅዱስነታቸው ለሁለቱ ነጋዲያት ቡራኬያቸውን በመስጠት ሰላምታ ተለዋውጠዋል።

ዛሬ የ59 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ወ/ሮ ኪም “ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በኋላ ሕይወታቸው ከጦርነት አደጋ መትረፉን በማስታወስ ባቀረቡት አስተያየት፣ ዓለም የሚያስፈልገው ሰላም እንጂ ጦርነት አለመሆኑን በነጻነት እናገራለሁ ብለው፣ በዚህ የሰላም ቁርጠኝነት “የናፓልም ልጅ” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቪዬትናም ውስጥ ኃይለኛ ጦርነት በተካሄደበት አካባቢ ዝናብ ይዘንብ እንደነበር የሚያስታውሱት የ71 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ፎቶ ግራፍ ዘጋቢ ኒክ፣ በአካባቢው ቦምቦች ይዘንቡ እንደናበር እና ሰዎችም ከአደጋው ለማምለጥ ሲሰሹ መመልከታቸውን አስታውሰዋል። ይህን ትዕይንት ፎቶ ግራፍ ያነሳው ኒክ፣ ፎቶ ግራፍ ማንሳቱን አቋርጦ በከባድ የጦር መሣሪያ የተጎዱትን በመኪና አሳፍሮ ወደ ሆስፒታል ማድረስ መጀመሩን አስታውሷል። 

ፎቶ ግራፍ ዘጋቢ ኒክ በዕለቱ ያነሳው ፍቶ ግራፍ በቪዬትናም የነበረውን የጦርነት አስከፊነት በትክክል እንደሚገልጽ ተመስክሮለት ዓለም አቀፍ የፑሊትዘር ሽልማትንም ማሸነፉ ይታወሳል። ፎቶ ጋዜጠኛው ኒክ ስለ ፎቶግራፉ በሰጠው አስተያየት፣ የልጅነት ጊዜው በከንቱ እንደባከነ የሚያስታውስ በመሆኑ መጀመሪያ ላይ እንደጠላው፣ ነገር ግን በጊዜ ሂደት ዋጋው ከፍተኛ እንደሆነ መረዳቱን ገልጿል። ተስፋን በመቁረጥ ራቁቷን የምትሮጥ ሴት ልጅ መላው ዓለም እንዲያያት ሲያደርግ የተሰማውን ውርደት ገልጾ፣ ሕጻኗ በጦርነቱ የደረሰባትን ቁስል ለመታከም 17 ጊዜ ነጻ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ማግኘቷን እና በኋላም መፈወሷን አስታውሷል።    

12 May 2022, 16:36