ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ንጹህ ልብ ማኅበር አባላትን በቫቲካን በተቀበሏቸው ዕለት ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ንጹህ ልብ ማኅበር አባላትን በቫቲካን በተቀበሏቸው ዕለት 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ አገልግሎትን ወደ ሕዝብ ዘንድ ሄዶ ማቅረብ እንደሚያፈልግ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ጳጉሜ 4/2013 ዓ. ም. በቫቲካን ለተቀበሏቸው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጹህ ልብ ማኅበር አባላት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለተጠሩበት የአገልግሎት ተልዕኮ ታማኝ በመሆን አገልግሎታቸውን ሕዝብ መካከል ገብተው እንዲያቀርቡ እና እውነተኛ ደህንነታቸውም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን መርሳት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ የማኅበራቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ በሮም ለሚገኙት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጹህ ልብ ማኅበር አባላት ባስተላለፉት መልዕክት “ደፋር እና በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመ” የሚለውን የጉባኤውን መሪ ቃል በመጥቀስ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በጸሎት እና በጽሞና ሕይወት በመታገዝ፣ ለሌሎች መስታወት በመሆን፣ በአገልግሎታቸው የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌዎች ሆነው መታየት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ፍሬያማ ተልዕኮ

የማኅበሩን አባላት “የወንጌል መልዕክተኞች ናችሁ” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ “ተልዕኮአችሁ በእውነት ፍሬያማ እንዲሆን ከፈለጋችሁ፣ ከጽሞና ሕይወት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ካላችሁ የጠበቀ ግንኙነት ልትነጥሉት አትችሉም” ብለዋል። አክለውም፣ “የእርሱ ምስክሮች ለመሆን ከፈለጋችሁም፣ አምላኪዎቹ መሆናችሁን ልታቆሙ አትችሉም” ብለዋል። የማኅበራቸው መሥራች ቅዱስ አንቶኒ ሜሪ ክላሬት ለማኅበሩ ባዘጋጁት ጠቅላላ ደንብ፣ በቁ. 9 ላይ፥ “የማርያም ንጹህ ልብ ማኅበር ልጅ በጎ ሥራውን እያበረከተ እንደ እሳት የሚቀጣጠል፣ በሄደበት ሁሉ የሚቀጣጠል ሰው ነው” ማለቱን ቅዱስነታቸው አስታውሰው፣ የማኅበሩ አባላት በኢየሱስ ፍቅር እንዲቃጠሉ፣ ይህ መለኮታዊ ፍቅርም በሄዱበት ሁሉ ለሌሎች መብራት ሆኖ እንዲያገለግል አደራ ብለዋል። ይህ አቋማቸው፣ እንደ አባ ክላሬት እና እርሱን ከተቀላቀሉ የመጀመሪያዎቹ ሚስዮናውያንተልዕኮ ደፋር የሚያደርጋቸው መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አብራርተዋል። የምንኩስና ሕይወት ድፍረትን እና የዕድሜ ባለጸግነትን እንደሚፈልግ የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ የዕድሜ ባለጸጋዎች እርጅናን የሚቋቋሙ፣ ወጣቶችም ከሆኑ የነፍስ እርጅናን የሚቋቋሙ መሆን አለባቸው”ብለዋል።

አገልግሎት ከሩቅ ሳይሆን ከቅርብ መሆን አለበት

ወደ ፊት እንዲጓዙ የሚያስችል ይህ እምነት ያለ እንደሆነ ነው፣ ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ይህ እምነት ካለ፣ ማንም ሊሄድ ወደማይፈልግበት፣ የወንጌል ብርሃን እንዲበራ ወደሚፈለግበት፣ ወደ ሕዝብ ዘንድ መሄድ የሚቻል መሆኑን አስረድተዋል። የማኅበሩ አባላት ተልዕኮ ወደ ሕዝብ መቅረብ እና ከሕዝብ ጋር መሆንን ይጠይቃል ያሉት ቅዱስነታቸው፣ የሚሆነውን ሁሉ ከሩቅ ሆኖ መመልከት በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል። የአባ ክላርን ምሳሌ መከተል ማለት ፣ የእውነታ ተመልካቾች ብቻ መሆን ሳይሆን መሳተፍን እንደሚፈልግ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ገልጸው፣ በዚህ መንገድ የማኅበሩ አባላት በጉዞአቸው የሚያጋጥማቸውን የኃጢአት እውነታዎችን መለወት የሚችሉ መሆኑን አስረድተዋል። “ቅዱስ ቃሉ እና የዘመኑ ምልክቶች እኛን ከሚያስጨንቁን ብዙ ሁኔታዎች እንዲያወጣን፣ ሳንጠነቀቅ ቀርተን ሕይወትን በድፍረት የማንኖር ከሆነ፣ በነጻ የተገኘው የምንኩስና ሕይወት ከሚደርስብን አደጋ ሁሉ ነፃ ያወጣናል” ብለዋል።

አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማትኮር

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለማኅበሩ አባላት ያደረጉትን ንግግር ባጠቃለሉበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ዘንድሮ ያካሄዱት የማኅበራቸው ጠቅላላ ጉባኤ ውይይት፣ በሌላ ነገር ላይ እንዲያተኩሩ፣ ነገር ግን የሕይወት ከለላቸውን እና ደህንነትን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንዲያደርጉ፣ በዚህም የማኅበሩ አባላት በሙሉ በዛሬ ዘመን የምንኩስና ሕይወት ትርጉም በሚገባ ለማወቅ በሚያግዙ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን አንድነት የሚያሳድግ፣ ከሌሎች የማኅበሩ ወንድሞች ጋር እውነተኛ ግንኙነትን ለመመስረት የሚያስችል ቀዳሚ የወንድማማችነት የማኅበር ሕይወት፣ ሕዝቦችን በተለይም ድሆችን ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ ለማድረግ በሚግዝ በወንጌል ተልዕኮ ላይ እንደሚያተኩራ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። 

10 September 2021, 20:13