ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ አዲሱ የኢትዮጵያዊያን ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ጳጉሜ 3/2013 ዓ. ም. ያቀረቡትን ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ሲያጠቃልሉ፣ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ መስከረም 1/2014 ዓ. ም. የሚያከብሩት አዲሱ ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን በመመኘት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ መከሰቱን አስታውሰው፣ አዲሱ ዓመት፣ የተመኙትን ሰላም አግኝተው የወንድማማችነት እና የአንድነት ሕይወት የሚኖሩበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

08 September 2021, 17:30