ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደቡብ ሱዳን ሁለት ደናግላን ላይ በተፈጸመው ግድያ ሀዘናቸውን ገለፁ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደቡብ ሱዳን ሁለት ደናግላን ላይ በተፈጸመው ግድያ ሀዘናቸውን ገለፁ! 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደቡብ ሱዳን ሁለት ደናግላን ላይ በተፈጸመው ግድያ ሀዘናቸውን ገለፁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው እሁድ ነሐሴ 09/2013 ዓ.ም በደቡብ ሱዳን በተፈጸመው ጥቃት የኢየሱስ ቅዱስ ልብ እህቶች ማኅበር አባል የነበሩት ሁለት ደናግላን መገደላቸውን በመስማታቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ እህቶች ማሕበር አባላት በነበሩት በሲስተር ማርያም አቡድ እና በሲስተር ሬጂና ሮባ ሞት ምክንያት በሆነው “ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት” በመስማታቸው ጥልቅ ሐዘናቸውን ገልጿል። ቅዱስነታቸው የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን በኩል በቴሌግራም ባስተላለፉት መልእክት ነበር ሐዘናቸውን የገለጹት። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ “ትርጉም የለሽ የጥቃት እርምጃ” ማዕበል ሰለባ ለሆኑ ደናግላን ለቤተሰቦቻቸው እና ለማሕበር አባላቶቻቸው “ልባዊ መጽናናትን” እንደ ተመኙ እና በጸሎት ከእነርሱ ጎን እንደ ሚሆኑ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

እነርሱ የከፈሉት “መስዋዕትነት በክልሉ ያለውን የሰላም ፣ የእርቅ እና የፀጥታ ጉዳይ ቀጣይነት ፍሬያማ እንዲሆን ያደርገዋል” የሚለውን ተስፋቸውን ገልፀው ለሟች ደናግላን “ዘላለማዊ ዕረፍትን እና ለዘመድ አዝማዶቻቸው ደግሞ መጽናናትን” ቅዱስነታቸው ተመኝተዋል።

ሁለቱ ደናግላን የተገደሉት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን ከኡጋንዳ ድንበር ጋር በሚያገናኘው አከባቢ በሚገኘው ኑሙሌ በሚባል ሥፍራ አድፍጠው በነበሩ ሰዎች አማካይነት ነበር አደጋው የተፈጸመው። መነኮሳቱ ከአንዳንድ የማሕበራቸው አባላት ከሆኑት ደናግላን እና ከበርካታ ምእመናን ጋር በመሆን እ.አ.አ. በነሐሴ 15/2021 ዓ.ም የተከበረውን የፍልሰታ ማርያም አመታዊ በዓል አክብረው ሲመለሱ ነበር ጥቃቱ የተፈጸመባቸው። የታጠቁ ሰዎች ይጓዙበት በነበረው አውቶብስ ላይ የጥይት እሩምታ በማዝንብ ነበር ጥቃቱን የፈጸሙት፣ በጥቃቱ ምክንያት ሲስተር ሜሪ ፣ ሲስተር ሬጂና እና ሌሎች ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ዘግበዋል።

18 August 2021, 10:06