ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፖላንድ የሚገኘውን የአውሽ ቪዚ ቢንኬርናው  የናዚ የማጎሪያ ካፕ በጎበኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፖላንድ የሚገኘውን የአውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የናዚ የማጎሪያ ካፕ በጎበኙበት ወቅት  

ያ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ዝምታ በአውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የሥቃይ ማጎሪያ ካፕ ውስጥ!

ከአምስት ዓመት በፊት ማለትም እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም ነበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በክራኮቪያ የዓለም የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ወደ ፖላንድ ጉዞ ያደረጉት፣ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በእዚያው የሚገኘውን አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው በመባል የሚታወቀውን የናዚ ማጎሪያ ካምፕን መጎብኘታቸውም ይታወሳል። በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ወደ ተጨማሪ ዝምታ እና የጥሞና ጊዜ ሊያመሩ አስበው እና ይህንን ገቢራዊ ለማደረግ በመፈለጋቸው በሞት እና በስደት ሰቆቃ ውስጥ የነበረውን ስፍራ ለመጎብኘት በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ናዚዎች አማካይነት አይሁዳዊያን ታጉረው ይኖሩበት የነበረውን ስፍራ በመጎብኘት በእዚያው ስፍራ ውስጥ ከሁለት ሰዓታት በላይ በዝምታ እና በጥሞና አሳልፈው እንደ ነበረ ይታወሳል። በዚህም ዝምታ እና የጥሞና ጊዜ በእዚያ ስፍራ በግፍ ለተሰቃዩ እና ለመከራ የተዳረጉ ሰዎችን ጭንቀት እና ስቃይ ቅዱስነታቸው ተጋርተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከአምስት ዓመት በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚያ ወቅት የነበረውን እና አሁንም አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የማጎሪያ ካምፕን የሚወክለውን ጉብኝት ለማስታወስ በስፓኒሽ ቋንቋ “Señor tem piedad de tu pueblo. Señor, perdón por tanta crueldad!”በአማርኛው (ጌታ ሆይ ለሕዝብህን ምሕረትን አድርግ። ጌታ ሆይ ለፈጸምናቸው ለእነዚህ ብዙ ጭካኔዎች ይቅርታን አድርግልን!) የሚሉትን እነዚህ ጥቂት ቃላቶች ብቻ በክብር መጽሐፍ ላይ ማስፈራቸው ይታወሳል።  በክራኮቪያ ለዓለም የወጣቶች ቀን ወደ ፖላንድ ባቀኑበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ከዓለም ዙሪያ ከመጡ ወጣቶች ጋር በተገናኙበት ወቅት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም እ.አ.አ በሐምሌ 29/2016 ዓ.ም በናዚ ጭፍጨፋ ካምፕ ውስጥ ተገኝተው ፍጹም የሆነ የዝምታ እና የጥሞና  ጊዜ ለማሳለፍ ፈልገው ነበር።

ጸሎት በቅዱስ ማክስሚሊያን ኮልቤ ታስሮበት በነበረው ክፍል ውስጥ

እንደ እውነቱ ከሆነ የዚያን ቀን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጭንቅላታቸው ጀርባ በጥይት ተመትተው የሞቱት የእስረኞች ደም ነጠብጣቦች በአግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጠው በመግደያው ጣቢያ ግድግዳ አጠገብ ሆነው የእነዚያን ሰዎች ችንቀት በማስታወስ በዝምታ ጸሎት ማደረጋቸው ይታወሳል።  ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልቤ የታሰረበት “በረሃብ የመቅጫ ክፍል” ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ላይ ተገኝተው ለአሥራ አምስት ደቂቃዎች ያህል ዕይታቸውን ሳይነቅሉ ያንን ስፍራ በዝምታ መመልከታቸው ይታወሳል። ቅዱስ ማክስሚላን ኮልቤ ሕይወቱን መሥዋዕት ለማድረግ የመረጠው ናዚዎች ሞትን ከጫኑባቸው ከአስራ አንዱ እስረኞች መካከል የአንድ ቤተሰብ አባት የነበረ ሰው ነው።

በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ በጀርመን ናዚ በተገነባው እና ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ አይሁዳዊያን የታጎሩበት፣ የተጨፈጨፉበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 76ኛው አመት በቅርቡ በመላው ዓለም ተዘክሮ ማለፉ ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ይህ ቀን በተዘከረበት ወቅት ይህንን የጭፍጨፋ ቀን መዘከር ሰብዓዊ የሆነ ተግባር እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን የእዚህ ዓይነቱ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተሰምቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ግድያ ማስታወስ በወቅቱ የተከናወነው ዘግናኝ የሆነ ተግባር እንዳይደገም እንደ እንደ ሚረዳ አክለው ገልጸዋል። 

በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርው በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ በጀርመን ናዚ በተገነባው እና ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ አይሁዳዊያን የታጎሩበት፣ የተጨፈጨፉበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 76ኛው አመት እየተዘከረ እንደ ሚገኝ ቅዱስነታቸው ማናገራቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡ፣ በሁኔታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ማቀረባቸው የተገለጸ ሲሆን በክርስቶስ ቃል እንድንታመን፣ ራሳችንን ለአብ ምሕረት እንድንከፍት እና በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በመታገዝ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እንደ ሚገባ ገልጸው በዓለማችን ዙሪያ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ የሚባሉ ድርጊቶች ተመልሰው እንዳይፈጠሩ በትጋት መሥራት እና መጸለይ ይገባል ብለዋል።

በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙትን ዘግናኝ ነገሮች ማስታወስ ድርጊቱ ዳግም እንዳይከሰት ያደርጋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ዕለት ጥር 20/2013 ዓ.ም ካደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል የጀርመን ናዚ አይሁዳዊያን በማጎሪያ ካፖች ውስጥ ያጎረበት፣ የጨፈጨፈበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 76ኛው አመት እየተዘከረ እንደ ሚገኝ የገለጹ ሲሆን “ዛሬ በጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባዎች እና በናዚ አገዛዝ ለተሰደዱት እና የተገደሉ ሰዎችን ሁሉ እንዘክራለን” ብለዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሶቪዬት ቀይ ለበሽ ጦር ትልቁ የሆነውን የናዚ ማጎሪያ እና የሞት ካምፕ - ኦሽዊ ቪዚ-ቢንከርው - ነፃ ያወጣበት ቀን በተመለከተ ይህ ዘግናኝ የሆነ ድርጊት የተፈጸመበት እለት በአመቱ የሚዘከርበት ዓለም አቀፍ የመታሰቢያ ቀን እንደ ሆነ ይታወቃል።

መጻይ ጊዜ የተሻለ እንዲሆን የሚያደረግ መታሰቢያ ነው!

ይህንን ዘግናኝ የሆነ ጊዜ ማስታወሱ የሰው ልጅ መገለጫ ነው። ማስታወሱ የሥልጣኔ ምልክት ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዚህ ቀደም መናገራቸው ይታወሳል። ሁኔታውን ማስታወሱ ለተሻለ የወደፊት ሰላምና ወንድማማችነት ቅድመ ሁኔታ ነው በማለት እክለው መግለጻቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል “ማስታወስ ማለት እነዚህ ነገሮች እንደገና አንዳይከሰቱ ማደረግ ማለት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም “አንድን ህዝብ ለማዳን ከታሰቡ የርዕዮተ-ዓለም ሀሳቦች ጀምሮ አንድን ህዝብ እና ሰብአዊነትን ማጥፋት ተገቢ የሆነ ነገር እንዳልሆነ የምንረዳበትን አጋጣሚ ስለሚከፍትልን ነው” ብለዋል። “ይህ የሞት ፣ የመጥፋትና የጭካኔ መንገድ እንዴት እንደሚጀመር በትኩረት መከታተል አለብን” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

የርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ ቃል ባለፈው ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተዘከረበት ወቅት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ይህንን ሐሳብ ያስተጋባ ሲሆን “ለልባችን ይህ ተግባር ‘በጭራሽ! መደገም የለበትም ብለን በመናገር” አንድ ጊዜ የጸሎት እና የመታሰቢያ ጊዜ ወስደን ቀኑ እንዲዘከር ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስለእልቂቱ መታሰቢያ  “በዚህ እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ ወቅት ግድየለሽነት ተቀባይነት የለውም፣ እናም ይህንን ዘግናኝ የሆነ ተግባር የማስታወስ ችሎታ ሊኖረን የገባል” ማለታቸው ይታወሳል።

እ.አ.አ በ 2016 ወደ በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የተደረገው ጎብኝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ. በ 2016 ዓ.ም ወደ ፖላንድ ባደረጉት ጉብኝት በታዋቂው የናዚ የሞት ካምፕ ተገኝተው የአውሽ ቪዚ-ቢርኬናው መታሰቢያ እና ሙዚየም ጎብኝተው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ 2016 ዓ.ም ከእዚህ ቀደም የነበሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅደም ተከተል ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ቤኔዲክቶስ 16ኛ በመቀጠል ቦታውን የጎበኙ ሦስተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

በወቅቱ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጉብኝት በማጎሪያ ካፕ በር በኩል ወደ ውስጥ በመግባት የጀመረ ሲሆን በዝምታ “ሥራችሁ ነፃ ያወጣችኋል ”በሚል መሪ ቃል ጥልቅ የሆነ የጸጥታ አስተንትኖ ማደረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ የዛሬ 76 ዓመት ገደማ በካምፑ ውስጥ ለሚኖሩ አብረውት ለታሰሩ እስረኞች ሕይወቱን አሳልፎ በሰጠው በቅዱስ ማክሲሚልያን ኮልቤ የታሰረበት ክፍል ውስጥ ገብተው በዝምታ ቅዱስነታቸው የጸለዩ ሲሆን ከእዚያን በኋላ ደግሞ ከእዚህ ዘግናኝ እና ሰቃቂ ጥቃት በተአምር ከተረፉ ሰዎች ጋር ቅዱስነታቸው ተገናኝተው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል።

30 July 2021, 15:08