ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በብራዚል የሚገኙ የካቶሊክ የሚዲያ ተቋማት እርቅን እንዲያበረታቱ ጠየቁ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በብራዚል የሚገኙ የካቶሊክ የሚዲያ ተቋማት እርቅን እንዲያበረታቱ ጠየቁ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በብራዚል የሚገኙ የካቶሊክ የሚዲያ ተቋማት እርቅን እንዲያበረታቱ ጠየቁ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የብራዚል የካቶሊክ የሚዲያ ተቋማት በተለያዩ ምክንያቶች በመከፋፈል ላይ በምትገኘው በብራዚል ሀገር ውስጥ “የእርቅ እና የአንድነት መሳሪያዎች” እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ። የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብራዚል ውስጥ የሚገኙ የካቶሊክ የሚዲያ ተቋማት በእዚህ አስቸጋሪ የወረርሽኝ ጊዜዎች አገሪቱ እየተመታች በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት የሚዲያ ተቋማት “የዕርቅና የአንድነት መሣሪያዎች” እንዲሆኑ አበረታታለሁኝ ብለዋል።

ድልድዮችን በመገንባት የተስፋ እና የአብሮነት ምልክት እንዲሆኑ የቀረበ ጥሪ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብራዚል ጳጳሳት ጉባኤ ሥር የሚተዳደረው የተባበረው የካቶሊክ ኮሚኒኬሽን ተቋማት 12ኛውን አመታዊ ስብሰባ አስመልክተው ቅዱስነታቸው ለተሳታፊዎች በላኩት መልእክት ክርስቲያኖች “የተስፋ እና የአንድነት ምልክት” እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። በብራዚል ህብረተሰብ ውስጥ “አንድነት” አስፈላጊ መሆኑን እና ሕዝቡ በእምነታቸው ተነሳስተው የትንሣኤው ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ አብሮ እንደሚሄድ በማመን (ማቴ 28፣20) አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ እንደ ሚገባ ገልጸዋል። ይህ “ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በብራዚል የቤተክርስቲያኗ ተልእኮ የሆነውን የአንድነትና የዕርቅ መሣሪያዎች” መሆንን የሚያመለክት ነው በማለት ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ቀውስ ውስጥ ሀገሪቱን እየከፋፈሉ ያሉትን ወቅታዊ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ውጥረቶችን በመጥቀስ አፅንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት ውጥረቶችን እና ፖሌቲካዊ የሆኑ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደ ሚገባ አክለው ገልጸዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ሁኔታ  “የክርስቲያን የሚዲያ ተቋማትድልድዮችን የሚገነቡ፣ የውይይት አስፈላጊነትን የሚገልጹ እና የርዕዮተ ዓለም ተቃርኖዎችን የሚያሸንፍ ግንኙነትን በማስተዋወቅ በግንባር ቀደምትነት ሊሳተፉ ይገባል” ማለታቸው ተገልጿል።

የእውነት ምስክሮች መሆን እና የሐሰት ዜናዎችን መቃወም

የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት ካርዲናል ፒኤትሮ ፓሮሊን ተፈርሞ የወጣው ይህ መልእክት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥራ የሚተዳደሩ የሚዲያ ተቋማት “የእውነት ምስክሮች የመሆን” ተቀዳሚ ግዴታቸውን እንዲወጡ አፅንዖት በመስጠት የገለጹ ሲሆን ለሚያወጧቸው ዜናዎች፣ ለሚያካፍሏቸው መረጃዎችና ቁጥጥር ማድረግ እና ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ማስታወሳቸው የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ቀድም 54ኛው አለም አቀፍ የኮሚንኬሽን ቀን ላይ የሐሰት ዜና ማጋለጥ በሚል የቀረበውን መልእክት በዋቢነት ጠቅሰዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት የተነበበው በበይነ መረብ በተደርገው ስብሰባ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በብራዚል የሚገኙ የካቶሊክ የሚዲያ ተቋማት ሕብረት ዋና ፕሬዝዳንት የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ዋልሞር ኦሊቬራ ዴ በስብሰባው መከፈቻ ላይ ከቅዱስነታቸው መልእክት በመቀጠል ባደረጉት ንግግር በበኩላቸው እንደገለጹት ለተግባራዊነቱ ተልዕኮ ውጤታማ እና ቀልጣፋ ግንኙነት አስፈላጊነትን በድጋሚ የገለጹ ሲሆን ይህ ደግሞ በብራዚል ለምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የስብሰባው ዋና መሪ ጭብጥ “ሕብረትን የሚፈጥር ኮሙኒኬሽን ማጠናከር” የሚለው ነው!

በብራዚሉ የካቶሊክ ሬዲዮ ኔትወርክ እና የብራዚል የዓለም ካቶሊክ የግንኙነት ማህበር የብራዚል ቅርንጫፍ ክፍል በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ዓመት ስብሰባ “ኮሙኒኬሽን በጋራ ጥረት” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በዚህ በበይነ መረብ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ 5,600 ተሳታፊዎች እየተካፈሉ መሆናቸው ተገልጿል። ይህ ስብሰባ ያተኮረው “ለተቀናጀ የሰው ልጆች ግንኙነት የአዲሱ የመገናኛ ብዙኃን ሚና” በሚል ጭብጥ ዙሪያ እየተከናወነ የሚገኝ ስብሰባ ሲሆን ስብሰባው በስድስት ክፍሎች ተከፍሎ እየተደረገ እንደ ሚገኝ ተገልጿል። ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው የሚገኙ ርዕሰ ጉዳዮች በእውነተኛ ህይወት እና በዲጂታል ሕይወት መካከል ያለውን ግንኙነት እና በብራዚል ውስጥ ለነበረው የቤተክርስቲያን ፈተናዎችን ፣ ሐሰተኛ የሆኑ ዜናዎችን የተመለከቱ ጉዳዮች፣ ሰላምን በመገንባት ሂደት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ሚና፣ አዲሶቹ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በኅብረተሰብ እና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያላቸው ተጽዕኖዎች ፣ የአዲሱን የመገናኛ ብዙሃን አውድ ችግሮች ያካተቱ ሐሳቦች፣ በድህረ-ወረርሽኝ ዘመን ውስጥ የካቶሊክን ኮሙኒኬሽን ለማደስ በጣሊያነኛ ቋንቋ “ፍራቴሊ ቱቲ” (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) በሚለው አርዕስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይፋ ካደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት  ስልቶች አንፃር ለቤተክርስቲያኒቱ ማህበረሰቦች የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዴት ማከናወን ይቻላል በሚሉ ጭብጦች ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎች እየተካሄዱ እንደ ሚገኝ ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳ ሲሆን  በብራዚል ለቤተክርስቲያኗ ተልእኮ ጥራት ያለው ግንኙነትን የካቶሊክ ሚዲያዎች ወሳኝ የሆነ ሚና እንደ ሚጫወቱ ገልጿል።

28 July 2021, 15:29