ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፥ “እያንዳንዳችን የበኩላችንን አስተዋጽዖ ማበርከት ይጠበቅብናል”

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13/2013 ዓ. ም. ያቀረቡትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው በቅዱስ ዳማሶ ቅጥር ግቢ ለተሰበሰቡት የተለያዩ አካባቢዎች ምዕመናን፣ በተለይም ከፖላንድ ለመጡት ምዕመናን ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። 

ቅዱስነታቸው በማስከተልም ለአረጋዊያን፣ ለሕጻናት፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙት ምስጋናን ማቅረብ ይገባል ካሉ በኋላ፣ ምስጋናን በማቅረብ ብቻ ሳንወሰን እያንዳንዳችን የበኩላችንን አስተዋጽዖ ማበርከት ይጠበቅብናል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዕለቱን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት በሥፍራው ለተገኙት ምዕመናን በሙሉ ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ሰጥተዋል።    

23 September 2020, 19:04