ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የእግዚአብሔር ትዕግሥት ልባችን በተስፋ እንዲከፈት ያደርጋል” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 12/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት አስተንትኖ በማቴዎስ ወንጌል  (ማቴ 13፡24-43)  ላይ በተጠቀሰው የእንክርዳዱ ምሳሌ ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የእግዚአብሔር ትዕግሥት ልባችን በተስፋ እንዲከፈት ያደርጋል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳቹ!

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል (ማቴዎስ 3፡24-43) ውስጥ አሁንም ቢሆን ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌዎችን ለሕዝቡ የመናገር ፍላጎት እንዳለው እንመለከታለን። በዛሬው አስተንትኖ ትኩረቴን የማደርገው ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ትዕግሥት እንድናውቅ አስቦ ልባችን ለተስፋ ክፍት እንዲሆን በማሰብ በተናገረው በእንክርዳዱ ምሳሌ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።

መልካሙ ስንዴ በተዘራበት ማሳ ውስጥ እንክርዳድ እንደበቀለ ይሚናግረው ይህ ቃል በአፈሩ ውስጥ ያሉትን ጎጂ እፅዋቶች በሙሉ የሚያጠቃልል መሆኑን ኢየሱስ ነግሮናል። በመካከላችን በአሁኑ ጊዜም ቢሆን አፈሩ በብዙ የእፅዋት አረም እና ፀረ-ተባዮች ጉዳት ደርሶበት በመጨረሻም ዕጽዋትን፣ መሬትን እና ጤናን እየጎዳ ይገኛል። ከዚያም አገልጋዮቹ እንክርዳዱ ከየት እንደመጣ ለማወቅ ወደ ጌታው ሄደው በጠየቁት ወቅት ጌታው “ይህንን ያደርገው ጠላት ነው!” (ማቴ 13፡28) በማለት ይመልስላቸዋል። ምክንያቱም እኛ ጥሩ ዘር ነበረ የዘራነው በማለት አክሎ ይገልጽላቸዋል። የሚገዳደረን ጠላት ይህንን ለማድረግ መጣ። እያደገ የመጣውን እንክርዳድ ወዲያውኑ ነቅሎ ለመጣል ይቻል ነበር። ይልቁንስ ባለቤቱ አይሆንም “ምክንያቱም እንክርዳዱን ስትነቅሉ መልካሙን ዘር አብሮ ሊነቀል ይችላል” በማለት ይከለክላቸዋል። እኛ የመከር ጊዜ እስኪደረስ ድረስ መጠበቅ አለብን፣ ከዚያም መልካሙን ፍሬ ከእንክርዳዱ በመለየት እንክርዳዱን ማቃጠል ይቻላል ብሎ የመልስላቸዋል። በመልካም መንፈስ የተተረከ ታሪክ ነው።

የታሪክ ራእይ በዚህ ምሳሌ ውስጥ ሊነበብ ይችላል። ሁልጊዜም ቢሆን መልካም ዘር ብቻ ከሚዘራው የማሳው ባለቤት ከሆነው ከእግዚአብሄር ቀጥሎ - የጥሩ ስንዴ እድገት ለመግታት እንክርዳዱን የሚዘራ ጣላት አለ። የማሳው ባለቤት የሆነው ጌታ በፀሐይ ብርሃን በግልጽ ይሠራል፣ ዓላማውም ጥሩ መከር እንዲበቅል ማደረግ ነው። ሌላኛው ተቃዋሚ በሌላው በኩል ደግሞ የሌሊቱን ጨለማ ይጠቀማል እናም በቅናት ፣ በጠላትነት ሁሉንም ነገር ያጠፋል። ኢየሱስ የጠራው የባላጋራው ስም ዲያብሎስ ነው፣ የእግዚአብሔር ተቃዋሚ ነው ዓላማውም የእግዚአብሔርን የደህንነት ሥራ ማደናቀፍ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ፍትሐዊ ባልሆኑ መሰናክሎችን በመደቀን የእግዚአብሔር መንግሥት መዘጋቱን ማረጋገጥ ነው። በእርግጥ የመልካሙ ዘር እና የእንክርዳዱ ምሳሌ በጥቅሉ መልካም እና መጥፎ የሆኑትን ነገሮች ብቻ የሚወክል ምሳሌ አይደለም፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን ወይም ዲያቢሎስን መከተል የምንችል እኛን የሰው ልጆችን የሚወክል ምሳሌ ነው። ብዙ ጊዜ ሰላም የሰፈነበት ቤተሰብ ውስጥ ጦርነት እና ምቀኝነት ሲፈጠር እንመለከታለን፣ ሰላም በሰፈነበት ሰፈር ውስጥ መጥፎ ነገሮች ሲከሰቱ ብዙ ጊዜ ሰምተናል። “አንድ ሰው እንክርዳድ ሊዘራ ወደ እዚያ ስፍራ እንደ ሄድ አድርገን እንናገራለን፣ ወይም “ይህ የቤተሰቡ አባል የሆነ ሰው በንግግሩ እንክርዳድ ዘራ” ብለን እንናገራለን። ሁልጊዜ አጥፊ የሆነ ክፉ ዘር እየዘራን ነው። ይህንን የሚያደርገው ደግሞ ሌሎችን ለማጥፋት በማሰብ ዲያቢሎስ ወይም እኛን የሚፈትኑ ነገሮች ግፊት የተነሳ በምናወራቸው ወሬዎች ሊሆን ይችላል።

የአገልጋዮች ዓላማ ክፋ የሆነውን የእንክርዳዱን ዘር ወዲያውኑ ማስወገድ ነበር፣ ይህ ማለት ክፉ ሰዎች ማስወገድ ነው፣ ነገር ግን ጌታው ብልህ የሆነ ሰው ነበር፣ አርቆ ይመለከታል፣- እንዴት በትዕግስት መጠባበቅ እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው ፣ ምክንያቱም ስደት እና ጥላቻ የክርስቲያን ሕይወት አካል ናቸውና። በእርግጥ ክፋት ውድቅ መደረግ አለበት ፣ ነገር ግን ክፉ የሚያደርጉ ሰዎች በመሆናቸው የተነሳ በትዕግስት መጠባበቅ ያስፈልጋል። ይህ ትዕግስት አሻሚ በሆነ መልኩ ያሰብነውን ነገር ደብቀን በግብዝነት መንፈስ የመቻቻል ጥያቄ አይደለም ፣ ነገር ግን በምሕረት መንፈስ የሚደረግ የፍትህ ተግባር ነው። ኢየሱስ ከጻድቃን ይልቅ ኃጢአተኞችን ለመፈለግ ፣ ከጤናማ ይልቅ የታመሙትን ለመፈወስ ( ማቴዎስ 9፣12-13) እንደ መጣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገር ሲሆን፣ እኛ የእርሱ ደቀመዛሙር የሆንን ሰዎች ተግባር ክፉዎችን ማጥፋት ሳይሆን ክፉዎችን መገሰፅ እና ማዳን ሊሆን ይገባል። እዚያ ላይ ነው እንግዲህ ትዕግስት የሚያስፈልገው።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል የአሰራር እና የሕይወት ታሪክ ሁለት መንገዶችን ያቀርባል ፣ በአንድ በኩል አርቆ ማየት የሚችለውን የጌታውን ታሪክ እንመለከታለን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ችግሩን የሚያዩ የአገልጋዮቹን እይታ እናገኛለን። በአገልጋዮቹ ልብ ውስጥ እንክርዳድ የሌለበት እርሻ የመንከባከብ መንፈስ አለ፣ በጌታው ልብ ውስጥ ደግሞ መልካም የሆነ የስንዴ ዘር አለ። ጌታ በጥሩ የስንዴ ዘር ላይ ትኩረቱን በማደረግ በእንክርዳድ መካከል ያለውን መልካም ዘር እንዴት መንከባከብ እንደሚቻል እንድንማር ይገብዘናል። የሌሎችን ውስን መሆን እና ጉድለት የሚሹ ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሄር ጋር በጥሩ ሁኔታ አይተባበሩም፣ ነገር ግን በቤተክርስቲያን እና በታሪክ መስክ በጸጥታ የሚያድጉትን መልካምነት እንዴት እንደሚገነዘቡ የሚያውቁ እነዚያ ሰዎች መልካሙ ዘር እስከ መከር ጊዜ ድረስ እንዲያድግ ማደረግ ይችላሉ። ያኔ ለመልካሙ ወሮታ የሚከፍል ክፉዎችንም የሚቀጣው እግዚአብሔር እና እርሱ ብቻ ይሆናል ማለት ነው። በአባትነት ፍቅር ከሚወዳቸው ልጆቹ ማንም እንዳይጎድል የሚፈልገው የእግዚአብሔርን ትዕግሥት እንድንረዳ እና ያንን ትዕግስት እንድንላበስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትረዳን አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል።

19 July 2020, 11:47