የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት 

“ጸጋ የሞላሽ ማሪያም ሆይ!” ስንል ይህንን ታላቅ ነገር በሕይወቷ ያከናወነውን እግዚኣብሔርንም እናመሰግናለን!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ፣ መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

ዛሬ (እ.አ.አ በመጋቢት 25/2020) የጽንሰተ ማሪያምን ውበት እናሰላስላለን። በሉቃስ ወንጌል 1፡26-38 ውስጥ የተጠቀሰው የማርያም ብስራት ታሪክ ዛሬ እያከበርነው የሚንገኘው በዓል ምን እንደሆነ ለመገንዘብ እንድንችል ይረዳናል፣ በተለይም ደግሞ የመልአኩ ገብረኤል ሰላምታ ይህንን በዓል በላቀ ሁኔታ እንድንገነዘብ ያደርገናል። እርሱም በሰውኛ ቋንቋ ለመተርጎም የሚያዳግቱ ቃላትን በመጠቀም “ጸጋን የተሞላሽ” በማለት ይጀመራል። ማርያም ብሎ በስሟ ከመጥራቱ በፊት ጸጋን የተሞላሽ በማለት በመጀመር በዚህም በእግዚኣብሔር የተሰጣትን አዲስ ስም ይፋ አደረገ፣ ይህም ወላጆቿ ከሰጧት ስም የበለጠ ዋጋ እንዳለው አሳየ።  እኛም “ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ!” እያልን ነው የምንጠራት።

ታዲያ “ጸጋ የሞላሽ” ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ማርያም በእግዚኣብሔር ሕልውና የተሞላች ናት ማለት ነው። እግዚኣብሔር በምልአት በውስጧ ስላደረ ለኃጢአት ምንም ቦታ በውስጧ የለም ማለት ነው። ዓለማችን በተለያዩ ክፉ በሆኑ ነገሮች ተበክሎ ባለበት በሁኑ ወቅት ይህ በጣም ትልቅ የሆነ ነገር ነው። እያንዳንዳችን ውስጣችንን ብንመለከት የጨለሙ ጎኖቻችንን መመልከት እንችላለን። ከማርያም በስተቀር ሁሉም ታላላቅ ቅዱሳን የሚባሉ ሳይቀሩ ኃጢያተኞች ነበሩ። ሁል ጊዜ የሰው ልጆች የልምላሜ መገለጫ የሆነች፣ በኃጢኣት ያልተበከለች፣ ያለአዳም ኃጢኣት የተጸነሰች፣ ሙሉ በሙሉ “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” በማለት ወደ ዓለም በመምጣት እና ለዓለም አዲስ ታሪክ የፈጠረውን እግዚኣብሔርን በውስጧ በማኖር የታዘዘች እርሷ ብቻ ናት።

ሁል ጊዜ “ጸጋ የሞላሽ ማሪያም ሆይ!” በምንልበት ወቅቶች ሁሉ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ይህንን ታላቅ ነገር በሕይወቷ ያከናወነውን እግዚኣብሔርንም እናመሰግናለን። “ጸጋን የተሞላሽ ማሪያም ሆይ” በምንልበት ወቅት ይህንንም የምንለው ለየት ባለ እና ክብር በተሞላው መልኩ ነው። እርሷ ሁል ጊዜ ወጣት እንደ ሆነች አድርገን ነው የምንቆጥረው ምክንያቱ ኃጢኣት አላስረጃትምና ነው። እኛን ልያስረጀን የሚችል አንድ ነገር ብቻ ነው፣ ይህም የውስጥ እርጅና ነው፣ በእድሜ ማርጀት ሳይሆን ከኃጢኣት የሚመጣ እርጅና። እኛን የሚያስረጀን ኃጢኣት ነው፣ ምክንያቱም ኃጢአት ልባችንን ስለሚበክል ነው። ልባችንን ይዘጋል፣ ልባችንን ያፈርሳል፣ ልባችን እንዲሰቃይ ያደርጋል። ነገር ግን በጸጋ መሞላት ከኃጢአት ነጻ ያደርጋል። ማርያም ሁሌም ወጣት ናት የምላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው።

ቤተክርስቲያን ዛሬ (በኅዳር 28/2012 ዓ.ም) ይህንን የማርያም ውብት እና ንጽሕና በማሰላሰል ላይ ተገኛለች። የእርሷ ወጣትነት በእድሜዋ እንደ ማይለካ ሁሉ እንደዚህም የእርሷ ውበት በውጫዊ ገጽታዋ አይለካም። የሉቃስ ወንጌል 1፡26-28 ላይ የተጠቀሰው ቃል የሚገልጸው ይህንኑ ነው፣ በጣም ትሁት ከሆነ ቤተሰብ የተገኘች፣ በትህትና በናዝሬት ትኖር የነበረች፣ በሰዎች ዘንድ ብዙ የምትታወቅ ሴት እንዳልነበረችም ያስረዳናል። መልአኩ ገብርኤል ወደ እርሷ መምጣቱን እንኳን ማንም ሰው አያውቅም ነበረ፣ ምናልባትም በዚያን ወቅት ዘጋቢ ጋዜጠኞች ስላልነበሩ ይሆናል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያ የተደላደለ ኑሮ አልነበራትም ነበር፣ በአንጻሩ ግን ጭንቀትና በፍርሃት ተሞልታ ነበረ፣ በሉቃስ ወንጌል 1፡29 “ማሪያም በመልአኩ ንግግር በጣም ደንግጣ” እንደ ነበረ ይናገራል፣ መልአኩ ገብርኤል ከእርሷ ተለይቶ በሄደበት ወቅት ችግሮቹዋም ተባብሰው ነበር።

ነገር ግን ይቺህ “ጸጋ የተሞላች” ሴት ውብ የሆነ ሕያወት ኖራላች። ታዲያ የእዚህ ምስጢር ምን ይሆን? ይህንንም ለመረዳት አሁን ለአንድ አፍታ መልአኩ ገብርኤል ያበሰራትን ብስራት መመልከት ያስፈጋል። ብዙ ሰዓሊያን የመልአኩ ገብርኤልን እና የማርያምን ግንኙነት በስዕል ስያስፍሩ ማርያም ከመልአኩ ፊት ለፊት ቁጭ ብላ ትንሽዬ መጽሐፍ በእጃ እንደ ያዘች የሚያሳይ ስዕል ስለዋል። ይህ መጽሐፍ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዚህም ማርያም እግዚኣብሔርን ማዳመጥ ተለማምዳ ነበር፣ ከእርሱም ጋር ትተዋወቅ ነበር። ታዲያ የማርያም ሕይወት ምስጢር ይህ የእግዚኣብሔር ቃል ነው፣ ለእርሱ ልብ ቅርብ ነበረች፣ የእርሱን ሥጋ በማህጸኑዋ አሳደረች። ከእግዚኣብሔር ጋር አብሮ በመኖር፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከእርሱ ጋር ትወያይ ነበረ፣ ይህ ድርጊቷ የማርያም ሕይወት ያማረ እንዲሆን አድርጎታል። የምያልፈው ውጫዊ ውበት ሳይሆን ወደ እግዚኣብሔር የሚጠቁም ልብ ሁልጊዜ ሕይወትን ውብ ያደርጋል። ዛሬ በደስታ ይችህን “ጸጋ የተሞላች” እንመልከት። ሁልጊዜ ወጣት ሁነን መኖር እንድንችል ትረዳን ዘንድ “ኃጢአትን እብየው አልፈልግህም!”በማለት በአንጻሩም ለእግዚኣብሔር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ውብ የሆነ ሕይወት እንድንኖር እርሷ በአማላጅነቷ ሁላችንንም ትርዳን አሜን።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ሀ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
25 March 2020, 16:49