ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ ቤት ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ሳምንታዊውን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ባደረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ ቤት ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ሳምንታዊውን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራነችስኮስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያበቃ ዘንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸሎት ሊደረግ የገባል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 13/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ላይ ተንትርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት “ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደረሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ስማንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በእሁኑ ወቅት በጣሊያን እነ እንዲሁም በመላው ዓለም እየተከሰተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሰው ልጅ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደ ገባ የገለጹ ሲሆን በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሁሉም ክርስቲያኖች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ሊማጸኑት ይገባል ብለዋል።  የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት መሪዎችን ከክርስቲያን ማኅበረሰብ ጋር በጋራ በመሆን ጸሎታቸውን ወደ ልዑል እግዚአብሄርን እንዲያቀርቡ ቅዱስነታቸው ጥሪ ማቅረባቸው የተገለስጸ ሲሆን ይህ መከራ እና ስቃይ ያበቃ ዘንድ ሁሉም የክርስቲያን ማሕበርሰብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንን ጸሎት በጋራ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርቡ እንደ ሚገባ ገልጸዋል። ስለሆነም አባታችን ሆይ የሚለውን ጸሎት “ሁሉም ክርስቲያኖች በያሉበት ቦታ ሆነው በእየለቱ እንዲደግሙ እጠይቃለሁ” ያሉት ቅዱስነታቸው በመጪው ረቡዕ መጋቢት 16/2012 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ ሁላችንም በጋራ በያልንበት ቦታ ሆነን “አባታችን ሆይ” የሚለውን ጸሎት እንድንጸልይ እጋብዛለሁ ብለዋል። በመጪው ረቡዕ መጋቢት 16/2012 ዓ.ም ብዙ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን እለት እንደ ሚያክብሩ በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር አባት የልጆቹን ሁሉ ጸሎት ይሰማ ዘንድ ልንማጸን ይገባል ብለዋል።

የቫቲካን ዜና

በዚሁ ተመሳሳይ ዓላማ በቀጣዩ ዓርብ መጋቢት 18/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ደጃፍ ላይ ሆነው ባዶ የሆነውን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እየተመለከቱ ጸሎት እንደሚያድርጉ የገለጹት ቅዱስነታቸው ሁላችሁም በያላችሁበት ስፍራ ሆናቸው በመገናኛ አውታሮች አማካይነት ከእኔ ጋር በመንፈስ በመሆን አብራችሁኝ በጸሎት መንፈስ ትተጉ ዘንድ እጠይቃለሁ ብለዋል። “በወቅቱ  የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን ፣ ጸሎታችንን ከፍ አድርገን ወደ እግዚአብሔር እናቀርባለን፣ በቅዱስ ቁርባን ፊት ለፊት ሆነን እናመልካለን፣ በመጨረሻም ቡራኬ እንቀበላለን” ብለዋል።

“ለቫይረሱ ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸሎት በማደረግ በበሽታው ለተጎዱ ሰዎች ርህራሄ በማሳየት ምላሽ ለመስጠት እንፈልጋለን” ያሉት ቅዱስነታቸው ሕብረታችንን አጠናክረን በአሁኑ ወቅት በብቸኝነት መንፈስ ውስጥ ለገቡ ሰዎች ቅርብ መሆናችንን በመግለጽ ለሕክምና ባለሙያዎች እና በበጎ ተግባር ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ሁሉ ጸሎት ማደረጋችንን መቀጠል ይጠበቅብናል ብለው ለኛ ደህንነት ሲባል ወሳኝ እና ከባድ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ለሚገኙ ባለስልጣናት ጭምር ልንጸልይ ይገባል ብለዋል፣  መንግስት ሁላችንም እንድንተገብረው የሚጠይቀንን ነገሮች ተፈጽሚ እንዲሆን በማደረግ ላይ ለሚገኙት ፖሊሶች እና በየመንገዱ ላይ ሆነው ስርዓት ለማስጠበቅ ለሚሞክሩ ወታደሮች ያለን አጋርነት ልንገልጽ ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሳምንታዊውን መልእክት አጠናቀዋል።

22 March 2020, 17:17