ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ባለው ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ሆነው መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ባለው ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ሆነው መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያበቃ ዘንድ በጋራ እንድንጸልይ ጥሪ አቀረቡ!

ክቡራን እና ክቡራት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ባለፈው እሁድ መጋቢት 13/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” የተሰኘውን ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት መልእክ በአሁኑ ወቅት መላውን የዓለማችን ሕዝብ ስጋት ላይ ጥሎ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እግዚአብሔር በምሕረቱ ያስወግድልን ዘንድ “የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያበቃ ዘንድ በዓለምአቀፍ ደረጃ ጸሎት በማደረግ በበሽታው ለተጎዱ ሰዎች ርህሕራሄ በማሳየት ምላሽ ለመስጠት እንፈልጋለን” በማለት ባለፈው እሁድ እለት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 16/2012 ዓ.ም እኩለ ቀን በሮም የሰዓት አቆጣጠር 12፡00 AM ላይ “አባታችን ሆይ!” የተሰኘውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን ጸሎት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሁሉ ከእርሳቸው ጋር በመሆን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት በያሉበት ቦታ ሆነው ይጸልዩ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ይህንን የቅዱስነታቸውን ጥሪ ተቀብለን እያንዳንዳችን በያልንበት ስፍራ ሆነን ይህ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያበቃ ዘንድ ከቅዱስነታቸው ጋር በጋራ በመሆን ጸሎታችንን አባት ወደ ሆነው እግዚአብሔር እንድናቀርብ መልእክታችንን በትህትና እናስተላለፋለን።

የእዚህ ዜና አቅራቢ እና አዘጋጅ መብራቱ ሀ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዚሁ ተመሳሳይ ዓላማ በቀጣዩ ዓርብ መጋቢት 18/2012 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት (በሮም የሰዓት አቆጣጠር ደግሞ ከምሽቱ 18፡00) ላይ ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ደጃፍ ላይ ሆነው ፊታቸውን ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በማድረግ ጸሎት እንደሚያደርጉ ተገልጹዋል። በእዚህ መሰረት “ሁላችሁም በያላችሁበት ስፍራ ሆናቸው በመገናኛ ብዙሃን አውታሮች አማካይነት በቀጥታ በሚተላለፈውን ዝግጅት ከእኔ ጋር በመንፈስ በመሆን አብራችሁኝ በጸሎት መንፈስ ትተጉ ዘንድ እጠይቃለሁ፣ በወቅቱ  የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን፣ ጸሎታችንን ከፍ አድርገን ወደ እግዚአብሔር እናቀርባለን፣ በቅዱስ ቁርባን ፊት ለፊት ሆነን እናመልካለን፣ በመጨረሻም ቡራኬ እንቀበላለን”” በማለት ቅዱስነታቸው ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እኛም ይህ የብዙ ሰዎችን ሕይወት በመቅጠፍ ላይ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ማብቂያ ያገኝ ዘንድ እግዚአብሔር በምሕረቱ እንዲጎበኘን ከቅዱስነታቸው ጋር በያለንበት ቦታ ሆነን በመንፈስ ከቅዱስነታቸው ጋር በመሆን የጸሎት ስነ-ስረዓቱ ተካፋይ እንሆን ዘንድ በትህትና እንጋብዛለን። የሰማ ላልሰማ ያሰማ!

 

25 March 2020, 10:35