በእስፔን በመካሄድ ላይ ባለው ዓለም አቀፍ የምዕመናን ጉባሄ መሪ ቃል በእስፔን በመካሄድ ላይ ባለው ዓለም አቀፍ የምዕመናን ጉባሄ መሪ ቃል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሕዝቡን የልብ ምት እያዳመጣችሁ ሰዎችን ለመገናኘት መውጣት ይኖርባችኋል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእስፔን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ለካርዲናል ብላዝቈዝ ፔሬዝ በየካቲት 06/2012 ዓ.ም በላኩት መልእክት እንደ ገለጹት የሕዝቡን የልብ ምት እያዳመጣችሁ ሰዎችን ለመገናኘት መውጣት ይኖርባችኋል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት በአሁኑ ወቅት  “በጉዞ ላይ የሚገኝ የእግዚኣብሔር ሕዝብ” በሚል መሪ ቃል በእስፔን በመካሄድ ላይ ባለው ዓለም አቀፍ የምዕመናን ጉባሄ አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት መሆኑን ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“የሚለያዩን እና አግላይ የሆኑ ግድግዳዎችን እንኳ ሳይቀር ለማፍረስ ሕያው የሆነው የእግዚአብሔር ቃል በክርስቲያናዊ ምስክርነት፣ በስሜትና በደስታ መሰበክ አለበት” በማለት በመልእክታቸው የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ጠመዝማዛ የሆኑ ጎዳናዎችን በመጓዝ፣ የከተማውን ወሰን ለማዳረስ፣ የከተማችንን አደባባዮች ሳይቀር ለማዳረስ እና የሕዝባችንን ቁስል ለመንካት” መፍራት የለባችሁም ብለዋል።

ሲኖዶስ ማድረግ አስፈላጊነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእስፔን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ለካርዲናል ብላዝቈዝ ፔሬዝ በሁኑ ወቅት በእስፔን በመካሄድ ላይ ላለው የምዕመናን ዓለም አቀፍ ጉባሄን አስመልክተው በላኩት መእልክት ጨምረው እንደ ገለጹት ይህ “በጉዞ ላይ የሚገኝ የእግዚኣብሔር ሕዝብ” በሚል መሪ ቃል ይፋ የሆነው ሰነድ እ.አ.አ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥናቱ የተጀመረ መሆኑን ገልጸው በእዚህ አራት አመት ጥናት ውስጥ የሐዋርያዊ ሥራዎች ክንውን በተመለከተ ጥልቅ ጥናት ከተደረገ በኋላ ይፋ የሆነ ሰንድ መሆንን ቅዱስነታቸው በመልክታቸው ጨምረው ገልጸዋል። “ረዘም ያለ የዝግጅት ጉዞ” መደረጉን አክለው በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ምዕመናንን በተመለከተ ከተለያዩ እውነታዎች በመጀመር ሐሳቦችን እና መልካም የሆኑ ልምዶችን በማካፈል ከዳበረ በኋላ “የምንኖርበትን ማኅበርሰብ ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል ምልኩ የተዘጋጀ ሰንድ መሆኑን” ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በእርግጥ “ሄዳችሁ ወንጌልን ስበኩ” የሚለው የቅዱስ ወንጌል ቃል በእውነቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሕዝቡ እና  ምዕመናኑ እውን ሊያደርጉት እንደ ሚችሉ ተስፋ እንዳላቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “በዓለም ውስጥ በመግባት በእግዚአብሔርና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ በዘመናችሁ ውስጥ፣ በሕዝቦች ውስጥ፣ በዓለም ውስጥ ” ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ተደራሽ ማድረግ ይኖርባችኋል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ምዕመናን የፉክክር፣ የግድዬለሽነት ፈተናዎችን በማስወገድ ቅዱስ ወንጌልን የማብሰር ተግባር ለካህናት ብቻ የተተው ተግባር ስላልሆነ በእዚህ ረገድ ምዕመኑ በንቃት መሳተፍ እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።  እግዚአብሔር ቤተሰብ

በእርግጥ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን "ሳትፈርድ እና ሳትወቅስ እጆቿን ዘርግታ ሌሎች ሰዎችን ለመደገፍ እና ለማበረታታት ወይም በቀላሉ በሕይወታቸው ውስጥ አብሮዋቸው ለመጓዝ መጠራቷን” በመግለጽ መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ለማድረግ እና በምስጢረ ጥምቀት የተቀበልነው ጸጋ ለመተግበር ይቻል ዘንድ በመተባበር ለመኖር “የክርስቲያን ማህበረሰብ አካል መሆናችንን ማወቃችን መሠረታዊ የሆነ ነገር ነው” ብለዋል። ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት “እኛ አንድ ቡድን ወይም መንግስታዊ ያልሆነ የግብረ ሰናይ ድርጅ አይደለንም” በማለት አጽኖት ሰጥተው በድጋሚ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ነገር ግን እኛ “የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ ከጌታ ጋር በአንድነት የተሰበሰብን የእርሱ ወዳጆች ነን” ብለዋል።

ወንጌል በአውሮፓ እንዲያንሰራራ ለማድረግ

ቤተክርስቲያናችን ዛሬ (የካቲት 06/2012 ዓ.ም) የአውሮፓ አህጉር ጠባቂ ቅዱሳን በመባል የሚታወቁትን የቅዱሳን ቂሪሊዮስ እና ሜቶዲዮስ አመታዊ በዓል በማክበር ላይ እንደ ምትገኝ የገለጹት ቅዱስነታቸው “የሚስዮናዊነት ተልእኮ ሁሌም ቢሆን ወቅታዊ እና በምንኖርበት ዓለም ውስጥ የቅዱስ ወንጌል ድምጽ በአዲስ መልክ የምናስተጋባ ሁል ጊዜም አዎንታዊ በሆነ ኃይል ተሞልቶ የሚደረግ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ የምስራችሁን ቃል ብዙ የሞት እና ተስፋ መቁረጥ ድምጾች በሚስተዋሉበት የአውሮፓ አህጉር ውስጥ በአዲስ መልክ ሊሰበክ እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው በመልእካትቸው አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

14 February 2020, 16:00