ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ  በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ  

እግዚኣብሔር “በኃጢያታችን መጠን አልቀጣንም፣ በበደላችን ልክ አልከፈለንም” የሚለውን ማሰብ ተገቢ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በየካቲት 04/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደርጉት የክፍል ሦስት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀድም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ውስጥ በተጠቀሰው ኢየሱስ በተራራው ላይ በሰበከው ስብከት ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተምህሮ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ “የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፣ ምጽናናትን ያገኛሉና” (ማቴ 5፡4) በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን እግዚኣብሔር “በኃጢያታችን መጠን አልቀጣንም፣ በበደላችን ልክ አልከፈለንም” (መዝ 103፣10) የሚለውን በአእምሮዋችን የምናስብ ከሆነ በእርሱ ምህረት እና ርህራሄ ውስጥ እንኖራለን ፣ እናም ፍቅር በውስጣችን ይገለጣል፣ ጌታ አብዝተን እንድንወድ ያደርገናል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 04/2012 ዓ.ም ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ከእዚህ ቀደም ብጽዕናን ያስገኛሉ ብሎ ኢየሱስ በታራራው ላይ በሰበከው ስብከት ላይ መሰረቱን አድርጎ የነበረውን አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ የእዚህ የተራራው ስብከት ሁለተኛ ክፍል በሆነው “የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፣ ምጽናናትን ያገኛሉና” በሚለው በሁለተኛው ክፍል ላይ የምናደርገውን አስተምህሮ እንጀምራለን።

ይህ ቅዱስ ወንጌል በተጻፈበት የግሪክ ቋንቋ ላይ መሰረቱን ያደርገው የተራራው ላይ ስብከት ውስጥ  በተጠቀሱት ግሶች ውስጥ በእውነቱ የተባረኩ ሰዎች ናቸው የሚላቸው ሰዎች የተገለጹበት መንገድ በመልካም ሁኔታ ላይ ያሉ ሰዎች ሳይሆኑ መከራን የሚቀበሉ ሰዎች መሆናቸውን ይገልጻል። የአንድ ክርስቲያን መንፈሳዊነት ማዕከላዊ እሴቱ የሚገለጽበት እና በበረሃ የኖሩ የቀድሞ አባቶች በግሪክ ቋንቋ “ፔንቶስ” የሚል ዝንባሌ ያለው እና ይህም ማለት ከጌታ እና ከባልንጀሮቻችን ጋር እውነተኛ የሆነ ግንኙነት መመስረት የሚያስችል ውስጣዊ ህመም መሰማት ማለት ነው።

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ይህ ለቅሶ ሁለት ገጽታዎች ሊኖሩት ይችላል - አንደኛው ምክንያት በአንድ ሰው ሞት ወይም መከራ ምክንያት የሚከሰት ለቅሶ ነው። ሌላኛው ገጽታ እግዚአብሔርን እና ባልንጀራን በመበደላችን ምክንያት በሚሰማን ስቃይ የተነሳ ልብ በሚያለቅስበት ጊዜ የኃጢያት እንባ ያነባል። አንድ ሰው ለእኛ ውድ ሲሆን በእዚህም የተነሳ እርሱ በሚሰቃይበት ወቅት ወይም በሚታመምበት ወቅት በእዚህ የተነሳ ለእዚህ ስቃይ መንገዱን የከፈትን እኛ በመሆናችን የተነሳ እናዝናለን።

ስለሆነም ህመሙን ተጋርተን ከእርሱ ጋር መቆራኘት ሌላውን የመውደድ ጉዳይ ነው። በሩቅ ቆመው መመልከት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፣ ነገር ግን ለሌሎች ሰዎች በልባችን ውስጥ እረፍት ያገኙ ዘንድ ቦታ መስጠት አስፈላጊ ነው የሚሉ ሰዎችም አሉ።

ስለ እንባዎች ስጦታ ብዙ ጊዜ ተናግሪያለሁ፣ እናም እንባ ምን ያህል ውድ እንደ ሆነ እንገነዘባለን። ቀዝቃዛ በሆነ መንገድ መውደድ ትችላለሁ ወይ? በግድ ወይም እንዲያው ለይስሙላ ልንወድ እንችል ይሆናል። መጽናናት የሚፈልጉ እጅግ በጣም የተጎዱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የተጎዱ ሰዎችን ለማጽናናት፣ ለማነቃቃት የማይፈልጉ ድንጋይ የሆነ ልብ ያላቸው ማልቀስ የረሱ የሌሎች ሰዎችን ቁስል የዘነጉ ሰዎች አሉ።

ሐዘን መራራ የሆነ መንገድ ነው፣ ነገር ግን ዓይኖቻችንን መንፈሳዊ ለሆኑ እሴቶች እና መተኪያ ለሌላቸው ለእያንዳንዱ ሰው ዓይኖቻችንን እንድንከፍት ያደርገናል፣ በዚያን ጊዜ ደግሞ ጊዜው አጭር መሆኑን እንገነዘባለን።

ለዚህ ግራ የተጋባ ለሚመስለው የተራራው ላይ ስብከት ሁለተኛ ትርጉም አለ- ይህም በኃጢያት ላይ ማልቀስ የሚለው ነው።

እዚህ መለየት አለብን ነገር አለ - ስህተት በሚሰሩበት ወቅት የሚናደዱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ይህ ኩራት ነው። ይልቁኑ ለተፈጠረው መጥፎ ነገር ወይም ስህተት፣ ጥሩውን ነገር ትተው እና ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመካዳቸው የተነሳ የሚያልቅሱ ሰዎች አሉ። ይህ ሌሎችን ባለመውደዳችን የተነሳ በመጨነቅ የምናለቅሰው ለቅሶ ነው፣ ከልብ የመነጨ ፍቅር ማጣት ነው። እዚህ ጋር የምናለቅሰው ሕይወታችን ከጌታ ጋር የተሳሰረ ባለመሆኑ ነው፣ መልካም ነገሮችን ባለማከናወናችን ይተነሳ እናዝናለን፣ እናለቅሳለን፣ ይህ የኃጢያት ስሜት ነው። እነሱ "እኔ የምወደውን ሰው ጎድቻለሁ" ይላሉ እናም ይህ በእንባ ተሞልተው እንዲያለቅሱ ያደርጋቸዋል። እነዚህ እንባዎች በሚወጡበት ወቅት እግዚአብሔር ይባረካል!

ይህ ፊት ለፊት የሚታይ ከባድ የሆነ፣ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ የሆነ የአንድን ሰው ስህተቶችን የሚያሳይ ገጽታ ነው። ስህተት በመፈጸሙ የተነሳ በደሉ ተሰምቶት እጅግ በጣም ተማሮ ያለቀሰውን ሐዋርያው ጴጥሮስን እንመልከት፣ በተቃራኒው ደግም በሰራው ስህተት ተማሮ ራሱን የገደለውን ይሁዳን እንመልከት። ወደ አዲስ እና እጅግ ውብ ወደ ሆነ መንገድ በፍቅር ላይ ተመርኩዞ እንዲጓዝ ያደርገው የጴጥሮስ ለቅሶ ነው። ኃጢአቱን መረዳቱ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው፣ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው ፡፡

በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ሐዋርያው ጴጥሮስ የኢየሱስን ትንሣኤ አብስሩዋል እናም እሱን ያዳምጡ የነበሩ ሰዎች ልባቸው በጥፊ እንደተመታ ይሰማቸዋል፣ በእዚህም የተነሳ “ምን ማድረግ ይገባናል በማለት” ይጠይቁታል። ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲመልስላቸው ለኃጢያት ስርየት የሚሆን ጥምቀት እንዲቀበሉ እና መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ይመክራቸዋል።

ሶሪያዊው ኤፍሬም እንደተናገረው በእንባ የታጠበ ፊት በሚያስገርም ሁኔታ ቆኖጆ ይሆናል ይል ነበር። እንደ ሁሌም  የክርስቲያን ሕይወት በምሕረት ውስጥ ምርጥ መገለጫ አለው። ከፍቅር ጋር የተዛመደ ሥቃይን የሚቀበል ሰው ጥበበኛ እና የተባረከ ነው ፣ እርሱም ይቅርታን የሚያደርግ እና ለሰራው ስህተት እርማት የሚሰጠን የእግዚአብሔር ርህራሄ መንፈስ ቅዱስ ነው።

ሁል ጊዜ እግዚአብሔር “በኃጢያታችን መጠን አልቀጣንም፣ በበደላችን ልክ አልከፈለንም” (መዝ 103፣10) የሚለውን በአእምሮዋችን የምናስብ ከሆነ በእርሱ ምህረት እና ርህራሄ ውስጥ እንኖራለን ፣ እናም ፍቅር በውስጣችን ይገለጣል። ጌታ አብዝተን እንድንወድ ያደርገናል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
12 February 2020, 11:17