ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በግድብ መደርመስ አደጋ የሞቱትን በጸሎታቸው አስታውሰዋል።

በብራዚል፣ ብሩማንዲኞ በሚባል ከተማ በደረሰው የግድብ መደርመስ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ፣ በቁጥር 272 ዜጎችን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጸሎታቸው አስታውሰዋል። አደጋው የደረሰበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ ጥር 16/2012 ዓ. ም. ባስተላለፉት የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት፣ የአደጋው ሰለባ የሆኑት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ወላጆች እና ቤተሰቦች፣ መላውን የሀገረ ስብከቱ ምዕመናን እና በአደጋው ምክንያት ስቃይ የደረሰባቸውን በጸሎታችን እንድናስታውሳቸው አደራ ብለው በጸሎታቸውም ያስታወሷቸው መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል። የጋራ መኖሪያ ምድራችንን መልሰን የምንገነባበት ኃይል እና ጥበብ እግዚአብሔር እንዲሰጠን በማለት ጸሎታቸውን ያቀረቡት ቅዱስነታቸው በጸሎታቸው የቅዱስ ጳውሎስን አማላጅነት ተማጽነዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ያለፈው ዓመት፣ ጥር 16/2012 ዓ. ም. በብራዚል ውስጥ በተከሰተው የግድብ መደርመስ በበርካታ የብሩማዲኞ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የሕይወት እና የንብረት መጥፋት የደረሰ መሆኑ ይታወሳል። የውሃ ግድቡ ቫሌ የተባለ የአንድ ግዙፍ የብራዚል ኩባንያ ንብረት መሆኑ ታውቋል።  

25 January 2020, 17:15