ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የማልታን ፕሬዚደንት ተቀብለው ባነጋገሯቸው ወቅት፣  ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የማልታን ፕሬዚደንት ተቀብለው ባነጋገሯቸው ወቅት፣  

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የማልታን ፕሬዚደንት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት መስከረም 5/2012 ዓ. ም. የማልታን ፕሬዚደንት ክቡር ጆርጅ ቬላን በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸውን የቫቲካን ዜና ክፍል ባልደረባ ሊንዳ ቦርዶኒ የላከችልን ዘገባ አመልክቷል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት ጠዋት በቫቲካን ከፕሬዚደንት ጆርጅ ቬላ ጋር በተገናኙበት ወቅት በአውሮጳ ውስጥ በስፋት ውይይት የሚደረግበትን የስደተኞች ጉዳይ አንስተው መነጋገራቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል እንዳስታወቀው ሁለቱ አገሮች መካከላቸው ባለው የእስካሁን መልካም ግንኙነት የተደሰቱ መሆናችውን አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የሐይማኖት እሴቶን በማልታ ሕዝብ ባሕል እና የዕለተ ዕለት ሕይወት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን መነጋገራቸውን አስታውቆ፣ ለዚህም የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሚና የላቀ እንደሆነ ማስመራቸውን አስታውቋል። በማልታ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአገሩ በምታስተዳድራቸው የመጀመሪያ፣ መለስተኛ እና ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት አማካይነት የምታበረክተው እገዛ ከፍተኛ እንደሆነ ማስታወሳቸውን ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ ገልጿል።

የስደት ጉዳዮችን በተመለከተ፣

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማልታው ፕሬዚደትን ከክቡር ጆርጅ ቬላ ጋር ትኩረትን ሰጥተው የተወያዩበት ርዕሠ ጉዳይ ስደተኞችን የተመለከት እንደነበር አስታውቋል። ማልታ የሜዲቴራንያንን ባሕር አቋርጠው ወደ አውሮጳ ለመድረስ ለሚፈልጉ በርካታ የእስያ እና የአፍሪቃ ስደተኞች የመዳረሻ አገር መሆኗ ይታወቃል። የስደተኞች ጉዳይ ከሚመለከታቸው ሌሎች የሜዲቴራንያን አገሮች ለምሳሌ እንደ ጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን መካከል ማልታ አንዷ መሆኑ ይታወቃል። በአውሮጳ አገሮች መካከል ውይይት እየተደረገበት ያለው የስደተኞች ጉዳይ ማልታን በስፋት የሚመለከታት እና ሃላፊነትንም እንድትጋራ የሚያደርጋት መሆኑ ታውቋል።

ስደተኞችን መቀበል፣ ጥበቃን ማድረግ፣ ማሳደግ እና ወደ ማሕበረሰቡ እንዲገቡ ማድረግ፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዚህ በፊትም፣ በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች፣ መንግሥታት እና ድርጅቶች በሙሉ ይፋ ባደረጉት መልዕክታቸው፣ ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ፣ ከለላን መስጠት፣ የኑሮ ደረጃቸውን ማሳደግ እና በስደት ከሚኖሩበት አገር ማሕበረሰብ ጋር አብረው ተጎራብተው እና ተዋውቀው መኖር እንዲችሉ ማድረግ በሚሉ አራት ርዕሠ ጉዳዮች ላይ ከፕሬዚደንት ጆርጅ ጋር መወያየታቸውን ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ አክሎ አስታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት ጠዋት ከማልታው ፕሬዚደንት ከሆኑት ከክቡር ጆርጅ ቬላ ጋር የስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያውቂዎች ጉዳይ አንስተው በተወያዩበት ወቅት እንዳስገነዘቡት፣ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያውቂዎች ክስተት ቤተክርስቲያንን በጥብቅ የሚመለከት መሆኑን አስረድተው የአካባቢ ጥበቃ ከቤተክርስቲያን ተነጥሎ የሚታይ አለመሆኑንም ተናግረዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከማልታው ፕሬዚደትን ከክቡር ጆርጅ ቤላ ጋር ትኩረትን ሰጥተው ከተወያዩበት ከስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ በተጨማሪም በአካባቢው አገሮች በተለይም የሜዲቴራንያን አካባቢ አገሮችን አንስተው መወያየታቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ ክፍል አስታውቋል።    

17 September 2019, 17:26