የማድሪድ የሰላም ጉባኤ አርማ፣ የማድሪድ የሰላም ጉባኤ አርማ፣ 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ: “የእግዚአብሄርን የሰላም ስጦታ አታባክኑ”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ለ 33 ኛው ጸሎት ለሰላም ስብሰባ ተሳታፊዎች መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ “ድንበር የሌለው ሰላም” እንዲሁም አንድነት እና መከባበር ፣ ለሁሉም ህዝቦች እና ለምድራችን ያስፈልጋል በማለት ጥሪ ማቀረባቸውን የቫቲካን ዜና ክፍል ባልደረባ የሆነው ፍራንቺስኮ መርሎ የላከልን ዘገባ አመልክቷል፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ለስብሰባው ተካፋዮች በላኩት መልእክታቸው፡ ይህ የሰላም ተጓዥነች… መቼም ቢሆን ሳይቋረጥ ማደግ መቀጠሉ ያስደስታል” በማለት ተናግረዋል። ይህንን መልእክታቸው ለማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ካርሎስ ኦሶሮ ሴራ እና ጸሎት ለሰላም ስብሰባ ተሳታፊዎች ነበር ያስተላለፉት።በሳንታ ጅዲኦ ማህበረሰብ የተዘጋጀው የሰላም ፀሎት ስብሰባ የተቋቋመው ከ 33 ዓመታት በፊት ሲሆን በዚህ ዓመትም “ድንበር የለሽ ሰላም” የሚል ጭብጥ በማንጸባረቅ በእስፔን ዋና ከተማ በማድሪድ እ.ኤ.አ.ከመስከረም 15 - 17 ድረስ ይካሄዳል፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ከ 30 ዓመታት በፊት የበርሊን ግንብን ውድቀት በማስታወስ ነበር መልዕክታቸውን የጀመሩት ፣ “ብዙ መከራ ያስከተለውን የአውሮፓ አህጉር ክፍፍልም አብቅቷል”፣ ያ ቀን በዓለም ዙሪያ “አዲስ ሰላምና ተስፋም” አምጥቷል ብለዋል ፡፡ ለዚህም፣ “ብዙ የእግዚአብሔር ልጆች ወንዶች እና ሴቶች የሰላም ፀሎትን በመጸለይ ለዚያ የመከፋፈል ግንብ ውድቀት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል በማለት ገልጸዋል።

በመቀጠልም፣ የጥል ግድግዳዎች የሚፈርሱት በጸሎት እንጂ በመሳርያ አይደለም፣ ለሰላም ዋጋ በመስጠት ወደፊት በሰላም መራመድ ያስፈልጋል በማለት ፣  በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ያለውን የኢያሪኮን ታሪክ አስታውሰዋል፡፡አስከትለውም“አምላክ የታማኝ ሕዝቦቹን ጸሎት ስለሚሰማ” ሁልጊዜ መጸለይ እና በሰላም መነጋገር አስፈላጊ ነው ”ብለዋል ፡፡

በዚህ ምዕተ-ዓመት በመጀመሪያዎቹ ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ “ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን ሰላም” በጦርነት እና “በአዳዲስ የጥላቻ ግድግዳዎች እና መሰናክሎች ግንባታ” ሲባክን ተመልክተናል ፣“መንገዶችን መዝጋት እና ሰዎችን በጥላቻ መለያየት” ሞኝነት ነው፣ ይህ ደግሞ ለሰዎችም ሆነ ለምድራችን በጎ ነገርን አያመጣም በማለት አስገንዝበዋል፡፡ የጋራ መኖሪያችን የሆነችው ምድራችን ፍቅርን ትሻለች፣ ልክ የሰው ልጅም “ ሰላምን ፣ ወንድማማችነትን፣ ፍቅርን ፣ እንክብካቤን ፣ አክብሮትን እንደሚፈልግ ሁሉ ምድራችንን መንከባከብ ይኖርብናል፣ “በሚለያዩን ግድግዳዎች” ፋንታ የጋራ መኖርያችን የሆነችው ይህች ምድራችን “በሰላም ለመግባባት፣ለመተጋገዝ ፣አብሮ ለመኖር የሚረዱ በሮች” ያስፈልጓታልም ብለዋል ፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችቼስኮስ በስብሰባው ላይ ለተሳተፉት ሁሉ ፣ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እና ከተለያዩ የዓለም ሃይማኖቶች ጋር ያላቸውን ቅርበት ገልጠዋል። ይህ ለሰላም የምናደርው ጸሎት “ያለ አንዳች ግራ መጋባት ሁላችንም አንድ ያደርገናል” ፣ ምክንያቱም ሰላም ለሁላችንም  የጋራ ፍላጎት ነውና በማለት ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር በአቡዳቢ ከተማ “ሰብአዊ ወንድማማችነት፣ ለአለም ሰላምና አብሮነትን በሚመለከት ሰነድ” መፈረማቸውን አስታውሰዋል ፡፡ ከታላቁ ኢማም አልዛሃር ጋር እንደተጋገሩት ፣ “ሃይማኖቶች ጦርነትን ፣ የጥላቻ አመለካከቶችን ፣ ጥላቻ እና አክራሪነት በጭራሽ ማነሳሳት የለባቸውም ፣ ዓመፅን ወይም የደም መፍሰስን ማነሳሳት የለባቸውም” ብለዋል ፡፡

በመጨረሻም ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በዚሁ መልእክታቸው ሁሉም ተሳታፊዎች “በአንድ ልብ እና በአንድ ድምጽ” “ሰላም ድንበር የለውም” በማለት ለሰላም መኖር እንዳለባቸው  አሳስበዋል ፡፡ አክለውም በአንድ ልብ ፣ ሰላምን እና ወንድማማችነት በመዝራት አንድ መሆን ያሻናል በማለት መልእክታቸው ደምድመዋል።

16 September 2019, 18:15