ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰሜን መቀዶኒያ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ካቴድራል ውስጥ ከቄሳውስት፣ ገዳማዊያን እና ምዕመናን ጋር በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰሜን መቀዶኒያ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ካቴድራል ውስጥ ከቄሳውስት፣ ገዳማዊያን እና ምዕመናን ጋር በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ራሳችሁን ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ክፍት አድርጉ” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰሜን መቀዶኒያ በሚያዝያ 29/2011 ዓ.ም ያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል በአገሪቷ ከሚኖሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት እና ደናግላን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት መንፈስ ቅዱስን አፍነን መያዝ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በሚገባ ተግባሩን ይወጣ ዘንድ ልንፈቅድለት የገባል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ማነኛውንም ሐዋርያው ተግባር በሚያከናውኑበት ወቅት ሁሉ በእግዚኣብሔር በመተማመን ተልዕኮዋቸውን ሊወጡ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በሰሜን መቀዶኒያ አድርገውት የነበረውን የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ያጠናቀቁት በአገሪቷ ከሚኖሩ ቄሳውስት እና ደናግላን ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በዚህች የባላክን አገር በሆነችው በሰሜን መቀዶኒያ ውስጥ የላቲን እና የባዛንታይን ስርዓተ አምልኮ የሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመና በመኖራቸው እግዚኣብሔርን አመሰግናለሁ ብለዋል።

“ቤተ ክርስቲያን ሁለቱንም ሳንባዎቹዋን ተጠቅማ ሙሉ በሙሉ በመተንፈስ ላይ ተገኛለች- እነዚህም ሳንባዎቿ የላቲን እና የባዛንታይን ስርዓተ አምልኮዎች ናቸው- በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የታደሰ አዲስ አየር በመተንፈስ ላይ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን” መሆኑዋን በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ሁለቱም ሳንባዎች "የጌታን ውበት ለመመልከት እንድንችል የሚረዱን" በመሆናቸው ሁለቱም አስፈላጊ እና የተሟሉ ናቸው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች ተልዕኳቸውን በሚገባ ለመወጣት ያስችላቸው ዘንድ “ከፍተኛ የሆነ ዝግጅት ማደረግ እንደ ሚገባቸው” ገልጸው በጣም ጥቂት የሆኑ ቄሳውስት እና ገዳማዊያን እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ቤተሰቦችን እና ሕዝቦችን ለማገልገል መጠራታቸው ደግሞ የዚህ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ተግዳሮት ነው ብለዋል።

በዚህ አግባብ የሚገጥመን ተግዳሮት ደግሞ በጌታ ላይ ያለንን መተማመን ከማሳደግ ይልቅ በራሳችን ላይ ብቻ የመተማመን ፈተና ውስጥ እንወድቃለን ያሉት ቅዱስነታቸው በከፍተኛ ደረጃ እኛን ለማገዝ ዝግጁ ሆኖ የተቀመጠውን የጌታ ኃይል በመጠቀም ብዙ ቄሳውስት እና ገዳማዊያን ወደ አገልግሎቱ ውስጥ እንዲቀላቀሉ በማደርግ እና ወደ ሕዝባቸው ይበልጡን እንዲቀርቡ በማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ቤተሰቦች፣ የታሙትን፣ አረጋዊያንን፣ መጭው ጊዜ የጨለመባቸው ወጣቶችን እና ድሆችን ጭምር በሚገባ እና ተገቢ በሆነ መልኩ ለመርዳት መነሳሳት ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ ሕዝቦች ደግሞ “የእግዚኣብሔርን ምሕረት የምትጠይቅ ቤተ ክርስቲያን አባላት እንደ ሆኑ እንዲረዱ ያደርጋል” ብለዋል።

የጥንካሬ ምስጢር

“ብዙውን ጊዜ እኛ ሰዎች ጠንካራ፣ ኃይለኛ እና ተፅዕኖ መፍጠር ከቻልን ነገሮች የተለየ ደረጃ ላይ ይደርሱ ነበር ብለን እናስባለን” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን እውነታው ከዚህ እጅግ የተለየ ነው የእኛ ጥንካሬ የመነጨው ከእኛው ከእራሳችን ሳይሆን ከመንፈስ ቅዱስ መሆኑን መረዳት እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው "የእዚህ ተልዕኮ ዋነኛው አካል ራሳችንን እንደ ሆንን አድርገን ላለመቁጠር እንጠንቀቅ፣ የመንፈስ ቅዱስን የልብ ትርታ ልንጠብቅ ይገባናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በሰሜን መቀዶኒያ ለሚገኙ ካህናትና ገዳማዊያን ያደርጉትን ንግግር በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት እምንት ከዓለም እንድንሸሽ ሳይሆን በእግዚኣብሔር ገድብ የለሽ ፍቅር በመተማመን በጥልቀት ወደ ዓለም ውስጥ እንድንገባ እንደ ሚያደርግ መገንዘብ ተገቢ እንደ ሆነ ገልጸው እያበረከታችሁት ስለምትገኙት አገልግሎት እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናችኋለሁ "የአምላክን የፊት ገጽታ በምድር ላይ ለማንጸባረቅ እያደረጋችሁት የምታደርጉትን ጥረት ለማንድነቅ እወዳለሁ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው በሰሜን መቀዶኒያ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ገድማዊያን ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀዋል።

07 May 2019, 16:18