ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቡላጋሪያ ቤተ መንግሥት ያደርጉት ንግግር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቡልጋሪያ እና ሰሜን መቀዶኒያ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመጀመር በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጀመርያ መዳረሻ ወደ ሆነችው ወደ ቡላጋሪያ አቅንተዋል። ቅዱስነታቸው በእዚያ በቡልጋሪያ ዋና ከተማ በሶፊያ በአገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚያ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 04፡50 ላይ በእዚያው በብሔራዊ ቤተ መንገሥት ለተገኙ የአገሪቷን ርዕሰ ብሔርን ጨምሮ በእዚያው ለተገኙ የምንግሥት ባለስልጣናት እና የተለያዩ አገራት ልዑካን ንግግር ማድረጋቸው ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትን ንግግር ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የተከበሩ ፕሬዚዳንት

የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር

የተከበራችሁ የተለያዩ አገራት የዲፕሎማሲ አካላት እና ልዑካን

ልዩ  ልዩ ባለስልጣናት

የተለያዩ የእመነት ተቋማት ተወካዮች

የተከበራቸው ወንድሞቼ እና እህቶቼ

የብዙ ባህሎች እና ስልጣኔቶች መገናኛ ሥፍራ የሆነችውን፣ የምስራቃዊ እና ደቡባዊ አውሮፓ መካከል የሚደረገውን ግንኙነት እንደ ድልድይ ሆና የምታገናኝ አገር፣ ቅርብ ለሆኑት የምስርቅ አገራት በሮቿን የከፈተች አገር፣ ጥንታዊ የሆነ የክርስትና እምነት ሥር መሰረት ያላት እና ይህንን እሴት ተጠቅማ በአከባቢው እና በአጠቃላይ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ደረጃም ሳይቀር ግንኙነት እንዲፈጥር ወደ አደረገችው ቡልጋሪያ በመምጣቴ ደስታ ይሰማኛል። እዚህ የተለያዩ ዓይነት ልዩነቶች በሚስተዋሉባት አገር፣ ለእያንዳንዱ ልዩነት በተጣመረ መልኩ ክብር በመስጠት ልዩነቶችን እንደ እድል ወይም እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የብልጽግናችው ምንጭ እንጂ የግጭቶች ምንጭ በማይሆን መልኩ እድሉን ተጠቅምችሁበታል።

ለሪፖብሊካ ባለ ሥልጣኖች ሞቅ ያለ ሰላምታዬን አቀርባለሁ; እንዲሁም ቡልጋሪያን እንድጎበኝ ሐሳብ ስላቀረቡልኝ አመሰግናለሁኝ። ክቡር ፕሬዚዳንቱ የመናገር ነጻነትን በእጅጉ ገድቦ የነበረውን ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ በመቃወሙ የተነሳ ከፍተኛ ስቃይ የደረሰበት በዚህ በአታናስ ቡሮቭ ስም በተሰየመው ታሪካዊ በሆነው አደባባይ ላይ ንግግር እንዳደርግ ስለጋበዙኝ አመሰግናለሁ።

ከትንሽ ግዜ ቆይታ በኋላ ለማገኛቸው ብጽዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ኔዎፊት እና ለሲኖዶሱ በተጨማሪም በቡላጋሪያ ለሚገኙ የኦሮዶክስ እምነት ተከታይ ምዕመናን ሁሉ የተከበረ ሰላምታዬ ይድረሳቸው። በቡላጋሪያ የሚገኙትን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበር አባል ለሆኑት ገዳማዊያን ገዳማዊያት በእየቀኑ በሕይወታቸው የክርስትና ሕይወት መንገድ በመከተል እና በመመስከር ላይ የሚገኙትን ሁሉ ከልብ የመነጨ ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ።

በተጨማሪም የተለያዩ የክርትና እምነት አብያተ ክርስቲያናት አባላትን፣ የአይሁድ ማኅበረሰብን እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን በሙሉ ሰላምታዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። ከእናንተ ጋር በጋራ በመሆን "ትክክለኛ ሐይማኖታዊ ትምህርቶች በሰላም እሴቶች ውስጥ ሥር መሰረታችንን አድርገን እንድንኖር እንደ ሚያበረታቱን፣ የሰው ልጆች ተግባብተው እንዲኖሩ፣ ሰብዓዊ የሆነ የወንድማማችነት መንፈስ እንዲፈጠር እንዲሚያደርጉ፣ አብሮ በጋራ የመኖር እሴቶች እንዲበረታቱ እንደ ሚያደርጉ ያለኝን እውነተኛ እና ጽኑ የሆነ እምነት ላረጋግጥላቹ እወዳለሁ። ከቡልጋሪያውያን እንግዶችን የመቀበል ባሕል በመማር እያንዳንዱ ሃይማኖት፣ ስምምነትን እና መግባባትን ለማምጣት ይችላ ዘንድ ለማበረታታት እንዲጠቅም፣ ለባሕል እድገት እና የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር ተጠብቆ እንዲቀጥል እና እንዲዳብር የሚያስችሉ ባሕሪያት እንዲዳብሩ፣ የበኩሉን ሚና መጫወት ይችል ዘንድ፣ ወሳኝ የሆኑ ግንኙነቶችን በተለያዩ ስልጣኔዎች፣ ልዩነት እና ልምዶች ውስጥ እንዲፈጠሩ በማደርግ  እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት የኃይል እና የጭቆና አሻራዎችን በመቃወም ለሰላም እና ለአንድነት ይሰሩ ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ። በዚህ መንገድ ሃይማኖትን ለአልተገባ አገልግሎት ለመጠቀም እና ከሐይማኖት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚፈልጉ ኃይሎች ይሸነፋሉ።

የአውሮፓ አህጉር ጠባቂ የሆኑት ቅዱሳን ቀሬሊዮስ እና መቶዲዮስ የተባረኩ ይሁኑ! በጸሎታቸው፣ በችሎታዎቻቸው እና የጋራ በሆኑ ሐዋርያዊ ጥረታቸው ለእኛ ምሳሌ ሆነው ያገለግላሉ፣ ይህንን አብነት በቀጣይነት የሚያሳዩን፣ ከአንድ ሺህ አመት በኋላ እንኳን ሳይቀር በአብያተ ክርስቲያናት፣ መንግስታትና ህዝቦች መካከል ፍሬያማ ውይይት፣ ስምምነት እና የወንድማማችነት መንፈስ እንዲነሳሳ አድረገዋል። የእነርሱ ብርቱ ምሳሌዎች በእኛ ዘመን ውስጥ ብዙ ተከታዮች እንዲኖሩ የሚያነሳሱ እና ለሰላም እና ለመግባባት አዲስ መንገድ ይከፈቱ።

በአሁኑ ወቅት በእንደዚህ ዓይነቱ አዲስ የታሪክ ዘመን፣ ነጻነት የጠየቁ ሰዎችን በእስር ቤት ውስጥ ያጎረውን ጨቋኝ ከሆነው የመንግሥት ስርዓት ከተላቀቀች ከሰላሳ አመታት በኋላ ቡልጋሪያ ከ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ አዲስ የስራ እድል ፍለጋ በመሰደድ ላይ ናቸው። በተመሳሳይ ወቅት ቡልጋሪያ - ልክ እንደ ብዙ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት - አዲስ ክረምት ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ነገር - ይህንን እውነታ መጋፈጥ ይኖርባታል በተለያዩ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የሚገኙ ሕዝቦች በመጪው ጊዜ ላይ ተስፋ እየቆረጡ በመምጣቸው የተነሳ ተስፋቸው ተመልሶ ያብብ ዘንድ በትጋት መሥራት ይኖርባታል። ከሕዝብ ቁጥር መቀነስ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የአገር ውስጥ የስደተኞች ፍልሰት ጋር ተዳምሮ በርካታ መንደሮችና ከተማቸውን ጥለው እንዲሄዱ አስገድዱዋል። በተጨማሪም በቡልጋሪያ ጦርነትን፣ ግጭቶችን ወይም አስቸጋሪ የሆነ ከፍተኛ ድኽነትን ሸስተው አብታም ወደ ሆኑ የአውሮፓ አገራት በመሻገር አዲስ የሕይወት እድል እና ድህንነት ለማግኘት አስበው ድንበሮችን አቋርጠው ለመሻገር የሚፈልጉት ስደተኞች ሁኔታ እይተጋፈጠች ትገኛለች።

የተከቡር ፕሬዚዳንት

የአገሪቷ መሪዎች ወጣቶችን በተለይም ለስደት እንዳይዳረጉ ለማድረግ ለብዙ አመታት ጥረት ማድረጋቸውን  አውቃለሁ። በዚህ ጎዳና ላይ እንድትቀጥሉ፣ ወጣቶች በወጣትነት ጉልበታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እና የወደፊት እቅድ እንዲኖሯቸው እና በአገራቸው ውስጥ፣ በአከባቢው ውስጥ፣ ክብር ያለው ህይወት የመኖር እድል እንደሚኖራቸው በማወቅ፣ የወደፊት እቅዳቸውን እንዲያሳድጉ ያበረታቱ ዘንድ እጠይቃለሁ። የስደተኞችን ፍልሰት ሁኔታ በደንብ ለምታውቁ የቡልጋሪያ ዜጎች ሁሉ፣ ዓይኖቻችሁን አትጨፍኑ፣ ልቦቻችሁን አታደንድኑ ወይም እጆቻችሁን አትሰብስቡ ለየት ያለውን ባሕላችሁን ተጠቅማችሁ በራችሁን ለሚያንኳኩ ሰዎች በር ክፈቱ።

ሀገራችሁ በምስራቅ እና ምዕራብ መካከል ድልድይ እንደሆነች አድርጋ እርሷን ትገልፃለች፣ ለብዙ መቶ አመታት በሰላም የሚኖሩበት በተለያየ ባህሎች፣ ጎሳዎች፣ ሥልጣኔዎች እና ሃይማኖቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ማራመድ የቻለች አገር ናት። የቡልጋሪያ ልማት የአገሪቷ የኢኮኖሚ እና የሲቪል ልማት ጨምሮ ለዚህ ልዩ ለሆነ ተግባራችሁ እውቅና መስጠትን ያካትታል። በታላቁ ድናብ ወንዝ እና በጥቁር ባህር አዋሳኝ ድንበር ውስጥ የምትገኘው ይችህ ምድር ለበርካታ ትውልዶች ትሁት በሆነው የሰዎች ጥረት የተገነባች አገር፣ ለባህልና ለንግድ ልውውጥ ራሷን ክፍት ያደረገች አገር፣ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተዋሃደች እና ከራሻ እና ከቱርክ ጠንካራ ግንኙነት ያላት አገር፣ ለሁሉም ወንዶችና ሴቶች ልጆቿ መጻይ ተስፋ ትሁናቸው።

እግዚአብሔር ቡልጋሪያን ይባርክ! በሰላም ይጠብቃት! ሁል ጊዜ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እንዲኖራት፣ ብልጽግና እና ደስታ ይስጣት!

05 May 2019, 17:51