ር.ሊጳ. ፍራንቸስኮስ በሲሪላንካ የተቃጣውን የአሸባሪዎች ጥቃት አወገዙ ር.ሊጳ. ፍራንቸስኮስ በሲሪላንካ የተቃጣውን የአሸባሪዎች ጥቃት አወገዙ  

ር.ሊጳ. ፍራንቸስኮስ በሲሪላንካ የተቃጣውን የአሸባሪዎች ጥቃት አወገዙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘ መልእክክታቸውን አስተላፈው ካበቁ በኋላ እንደ ተለመደው ባስተላልፉት መልእክት እንደ ገለጹት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የትንሳሄ በዓል ዋዜማ በሚከበርበት ቅዳሜ ምሽት ላይ በሲሪላናካ በሚገኙ በተለያዩ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ላይ በአሸባሪዎች በተቃጣው የቦንብ ጥቃት በርካታ ምዕመናን ሕይወታቸውን ማጣቸው እንዳሳዘናቸው ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን ይህንን ጥቃት “በጭካኔ የተሞላ ጥቃት” በማለት ቅዱስነታቸው ማውገዛቸው ተገልጹዋል።

“በሲሪላንካ ከሚገኙ ክርስቲያኖች ጋር ያለኛን አጋርነት ለመግለጽ እወዳለሁ” ያሉት ቅዱሰናታቸው የዚህ ዓይንቱ ጥቃት በምንም ዓይነት መስፈር ተቀባይነት የለውም፣ የጥቃቱ ሰላብ የሆኑ ሰዎችን እግዚኣብሔር ነፍሳቸውን ይምር ዘንድ እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይሰጥ ዘንድ ጸሎቴ ነው ብለዋል።

21 April 2019, 17:10